Get Mystery Box with random crypto!

..ልጄ ፍፀም ልዩ ሰው ሆኖ ነበር የመጣው.ያው ታውቃለህ የእምሮ በሽተኛ ስለሆነ ሁኔታው ሁሉ ወሰ | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

..ልጄ ፍፀም ልዩ ሰው ሆኖ ነበር የመጣው.ያው ታውቃለህ የእምሮ በሽተኛ ስለሆነ ሁኔታው ሁሉ ወሰድ መለስ ነበር የሚያደርገው...በዛን ቀን ግን እንደዛ አልነበረም….መልኩ ጥርት ያለ …አለባበሱ ጠርት ያለ…ንግግሩ ጥርት ያለ ነበር…፡፡ተደሰትኩ፤ተስፋ አደረኩ፤ጓጓው…በውስጤ ለአንድ ሺ ጊዜ ደጋግሜ ፈጣሪን አመሰገንኩ…ልጄ ሙሉ በሙሉ እየዳነልኝ ነው አልኩ….በደስታ እየተጫወተንና እየተቃለድን ቁርስ በላን..እማዬ ጸጉርሽ ተንጨብርሯል አለና ፀጉሬን ፈቶ ሲያበጥርልኝ ..መልሶ እየጎነጎነ ሲሰራልኝ …አቤት የተደሰትኩት መደሰት.ለካ እሱ እየተሰናናተኝ ነበር.ለመቸረrሻ ጊዘዜ ሰውነቴን እዳበሰኝ ነበር…የልጅ እጅ ሰውነትህ ላይ ሲያርፍ የሚሰማህን ስሜት ታውቀዋለህ…?በምንም ሊገለፅ የማይችል ልዩ ነው....እንደዚህ እንደዚህ እያልን አምስት ሰዓት ተኩል ሆነ፡፡
‹‹.ከዛ በቃ እማዬ ክፍሌ ናፍቆኛል ››አለኝ
‹‹እሺ ግባ እኔም እስከዛ ቆንጆ ምሳ በራሴ እጅ ሰራልሀለው›› አልኩና እሱን ወደክፈሉ ሸኝቼ ወደኪችን ገባው፡፡ ከዛ ሚወደውን ምግብ ሁሉ አንድ ሳላስቀር ሰርቼ ጠረጳዛውን ሞላውና ወደክፍሉ ሄጄ አንኳኳው መልስ የለም…እስኪደክመኝ አንኳኳው ‹እንቅልፍ ወስዷት ይሆን?› የሚል ጥርጣሬ ገባኝ…‹‹እንደለመደው ወጥቶ በመሄድ ጠፈቶብኝ ይሆን? ›ስልም ተጠራጠረርኩ…ቁልፍ አስመጣውና ከፍተን ስንገባ ..ልጄ በሰማያዊ ሲባጎ እራሱን አንጠልጥሎ በድኑ በአየር ላይ እየተሸከረከረ ነበር፡፡
ማንኛዋም እናት በእኔ የደረሰው ሀዘን አይድረስባት…ያው አሁን እኔም በህይወት መኖሬን እርግጠኛ አይደለውም…ውስጤ ደክሟል..ተስፋዬ መክኗል…ለህይወት ያለኝ ጉጉተት ጠፍቷል..የምበላው ምግብ ጨው ይኑረው አይኑረው እራሱ መለየት ትቼያለው…የምጠጣው ውሀ ይሁን በረኪና ግድ አይሰጠኝም…የዩኒቨርሲተ አስተማሪ ልሁን የፅዳት ሰራተኛ እርግጠኛ አይደለውም…ፕሮፌሰር ብለው ሲጠሩኝ እራሱ ማንነው? ብዬ መደንገጥ ጀምሬያለው..እኔ ይሄ ሁሉ ቀርቶብኝ እናት ብቻ ነበር መሆን የምፈልገው… የቢላል እናት መሆን…፡የቢላል እናት በሚል በፀጋ በተሞላ አስደናቂ ስም መጠራት.፡፡

ፖሊሱ ራሱ የሁሉቱ ሴቶች ሀዘን በጥልቀት ተጋባበት….ምንአይነት የተለየ ሰው ቢሆን ነው በዚህ መጠን ይወዱት የነበረ…?ሲል በውስጡ አሰበ….ከመሳቢያው ኪስ ውስጥ አንድ ወረቀት አወጣና ጠረጳዛ ላይ አሰቀመጠ….እና በሁለቱ መካከል ገፋ አደረገና አስጠጋላቸው.ሁለቱም እርስ በርስ ተያዩ
‹‹…ምንድነው ኢንስፔክተር?›ሲፈን ነች ጠያቂዋ
የቢላልን ክፍል ስንመረምር ያገኘነው ነው…ለሁለታችሁ ከመሞቱ በፊተ የተወላቸሁ መልዕክት ነው.፡
ሲፈን በፍጥነት አፈፍ አድርጋ አነሳችው….ድምፃን ከፍ አድርጋ ማንበብ ጀመረች፡፡

I hope you are blessed
With a heart like a wildflower
Strong enough to rise again
After being trampled on
Tough enough to weather
The worst of the summer
and even able to grow and flowrish
In the most broken of places
//
ማን ነበር እነዚህን የሀዘንና የተሰፍ እንጉርጉሮ ያንጎራጎረው.?.እኔ እንጃ ተረሳኝ/እማዬ….አንቺ የአለሞ ቁጥር አንድ እናት ነሽ...በጣም ነው የምወድሸ….ጤነኛም ስሆንም እዕምሮዬም በተቃወሰ ጊዜም ጭመር አንቺን ባለመቋረጥ እወድሻለው…እናም ደግሞ ከሞትኩ ቡኃላም እንደምወድሽ እንዳትጠራጠሪ፡፡ደምፅሽ እያወራሽኝ ሁሉ ይናፍቀኝ ነበር፤.ጠረንሽ ጉያሽ ተሸጉጬ እራሱ እራበዋለው…እማዬ ጥዬሽ ስለሞትኩ በጣም አዝናለው….ግን የግድ ማድረግ ስላላብኝ ነው፡፡አዎ በፍጥነት ውሳኔ ወስኜ እራሴን ካላጠፋው የምወዳትን ልጅ አጠፋለው….እሷን ገድዬም ደግሞ ብተርፍ አንድ ነገር ነበር …..ከገደልኮት ቡኃላ ደግሞ እራሴን ማጥፋቴ የማይቀር ነው..ሁለት ኪሳራ.፡፡..እና እማዬ ይቅር በይኝ…
ሲፈን ….አንቺ በነፍሴ የማፈቅራት ልዩ ሴት ነሽ….በጣም ልዩ ሴት..፡፡በንግግርሽ በጣም ከመደንዜ የተነሳ የእውነትም አንቺን ስለማግባት እያሰብኩ ነበር…ቃል እንደገባሽልኝ ገነት መሳይ በተፈጥሮ ያሸበረቀች ልዩ የብቻችን ቦታ ወስደሺኝ .እዛ ጎጆችንን ቀልሰን ..ልጆቻችንን ወልደን….ብርቱካንና መንጎ ከጎሮ እየቀነጠስና…ጥልል ባለ የወንዝ ውሀ ገላችንን እየታጠብን …በዝሆንና ቀጪኔ ጀርባ ላይ ሰርከስ እየሰራን..ብዙ ብዙ ነገር እንዳልም አድርገሺኛል….
ግን አንዳንዴ መራር ቢሆን እውነታን መጋፈጥ የጀግኖች ባህሪ ነው.እና እኔም ጀግና መሆን ወሰንኩ…፡፡ለአንቺ ህይወት የሚበጀውን ዘላቂ ነገር ማስብ እንዳለብኝ ወሰንኩ…አንቺን አንቄ ከመግደሌ በፊት እራሴን ማንጠልጠል እንዳብኝ ወሰንኩ…፡፡.እንደዛ ያደረኩት ለአንቺ አስቤ አይደለም፡፡.ጥዬሽም ለመሄድ አንጀቴ ጨካኝ ሆኖ አይደለም…አብረን ብንሞት እና አንድ መቃብር ብንቀበር ደስ ይለኝ ነበር…ግን እንደዛ ማደርረግ አልቻልኩም .፡፡ለምን? ለልጃችን ስል፡››
.ማንበቧን አቋረጠችና አንዴ ፕሮፌሰሯን አንዴ ኢንስፔክሩን እያፈራረቀች ተመለከተች‹‹..የምን ልጁ?››
ፕሮፌሰሯ ትከሻዋን በመነቅነቅ ‹እኔ ምን አውቄ ›የሚል መልስ ሰጠች..
እንስፔክተሩ ‹‹ማንበብሽን ቀጥይ ›› አለት
ማንበብ ቀጠለች…
‹እማዬ እና ሲፈን…እድለኛ ከሆንኩ አንድ የምስራች ልንገራችሁ…ማለቴ ይሄን ደብዳቤ ከማንባችሁ በፊት በሌላ መንገድ ዜናውን ካልሰማችሁ ማለቴ ነው፤እማዬ ልጅ ትቼልሽ ነው የሞትኩት…የልጅ ልጅ ሊኖርሽ ነው..ሲፈን እርጉዝ ነች የእኔ .ል..ጅ…..አርግዛ..ለች.›
ሲፈን ከመቀመጫዋ ተነሳች..ሆዷን በእጆቾ ዳበሰች..
‹‹ምን ማለት ነው.?››ማርገዜን እንዴት ነው ያወቀው…?እንዴት እንደዛ ሊሆን ይችላል?››
‹‹ምነው? ግንኘነት አልፈፀማችሁም እንዴ…?››ኢንስፔክሩ ነው የጠየቃት
‹‹አይ.. እሱማ ፈፅመናል..አዎ በደንብ ፈፅመናል..ግን ያልገባኝ እኔ ማርገዜን ሳላውቅ እሱ እንዴት..?ደሞ እኮ ምንም አይነነት የእርግዝና ምልክት እየታየብኝ አይደለም››
‹ኢንስፔክተር ይቅርታ አድርግልን ከፈለከን በሚመችህ ሰዓት ተመልሰን መምጣት እንችላለን ..አሁን ሆስፒታል ሄደን ይህንን ተአምር ማረጋገጥ አለብን.››ከመቀመጫዋ ተነስታ ሲፈንን እየጎተተች የኢንስፔክተሩንም ይሁንታ ሳትጠብቅ ይዛት ወጣች፡፡ወደ ሆስፒታል፡
///
አለም በምንም ጉዳይ ላይ ሚዛን የምትጠብቅበት የራስዋ የሆነ ስውር ቀመር አላት…፡፡ገፍትራ ከገደል አፍፍ ላይ ብትጥለንም ስንወድቅ ግን አስከመጨረሻው ተሰባብረን እንዳንደቅ ማረፊያችንን በተደላደለ የሰንበሌጥ ሳር አልብሰሳ ትጠብቀናለች ፡፡ድንገት ሳናስበው በአስፈሪ የአዞ አፍ ተሰልቅጠን ብንዋጥም ሆዱን ሰንጥቀን አረሳችን ነፃ የምናወጣበት ጩቤ ከጎናቸን እናገኛለን፡፡
ቢላለ በምን አይነት ተአምር እንዳወቀ ለሁለቱም እንቆቅልሽ ቢሆንባቸውም በምርመራ እንዳረጋገጡት ሲፈን የሶስት ሳምንት እርጉዝ ነች፡፡አዎ ከጭለማ ቡኃላ ብርሀን ይፈነጥቃል..ከምሽት ብሃል ንጊት አይቀሬ ነው….ከስቅለት ቡኃላ ትንሳኤም የሚጠበቅ ነው…በሁለቱ ሴቶች በሀዘን የደቀቀ ልብ ውስጥ የሆነች ብጣቂ ተስፋ ለመነቃቃት ስትንፈራገጥ ትታያለች፡፡

ሊያልቅ አንድ ክፍል ብቻ ይቀረዋል

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj