Get Mystery Box with random crypto!

ነፍስ ስታፈቅር ምዕራፍ-23 ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ /// ፀሀይ በደመቀ ብርሀኗ እና ለብ ባለው | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

ነፍስ ስታፈቅር
ምዕራፍ-23

ደራሲ ዘሪሁን ገመቹ

///
ፀሀይ በደመቀ ብርሀኗ እና ለብ ባለው ሙቀቷ በፈገግታሽ ብትወጣም ሰዓቷን ጠብቃ መክሰሟና መጥለቋ አይቀሬ የተፈጥሮ ግዴታ ነው..ጨረቃም ምሽቱን ጠብቃ በዝግታ እየተሳበች በመውጣት ሰማዩ ላይ በመገማሸር ብርሀኗንም ውበቷንም ብተረጭም ንጊት ሲቃረብ መጥፋቷ የሚጠበቅና የግድ የሆነ የተፈጥሮ ግዴታ ነው፡፡ደጅ ላይ የተተከለ አበባም ፈንድቶ በማዓዛውም በውበቱም አካባቢውን አድምቆ ለንቦችም ለቢራቢሮዎችም የሚገባቸውን ምግብ ያለስስት ለግሶ የማታ ማታ ወይ በአንድ አድናቂው ተቀንጥሶ ወይ ደግሞ በራሱ የተፈጥሮ ኡደት ጊዜው ደርሶ መድረቁና መርገፉ የማይቀር ነው፡፡
ሰውም እንደዛ ነው፡፡ከተወለደ..መቼም ይሁን መቼ የሞት ዕጣ እንዳለበተ ቅንጣት የማያጠራጥር ንፅህ እውነት ነው፡፡እንደውም ለሰው መለቀስ ካለበት ተክክለኛው ወቅት ሲወለድ ነው፡፡ብልሁ ሰው ለሞት ቀለብነት እየተፈጠረ ነውና፡፡ዳሩ ሰው ሰው የሚሆነው ምንአልባት ለእናት ካልሆነ በስተቀር ለሌላው ሰው ቅርፅ የሚመዘን ውበት የሚኖረው ከተወለደ ብኃላ በእድገቱ እና በኑሮ ውጣ ውረዱ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር በሚፈጥረው መስተጋብር ፤በእያንዳንዱ ነጠላ ገጠመኝ በየግለሰቦቹ ልብ ውስጥ ባለው ግዛት የሚገነባቸው የትዝታ ግንባታዎች አይነት ነው ፡፡
አንዳንዱ እድሜ ልክ አጠገባችን ኖሮ በውስጣችን ያለው ትዝታ ከእጅ መዳፍ የማይበልጥ ይሆናል...ሌላው ደግሞ ሶስት ቀን ስራችን ቆይቶ ሀገር የሚያህል ግዛት በልባችን ተመርቶ በደግነት ጡብ የታነፁ በፍቅር ልስን ያማሩ ለዘመነት የሚበቁ የትዝታ ግንብ ገንብቶ እናገኘዋለን፡፡
ቢላል በሲፈን ልብ ውስጥ የፈጠረው እንደዛ አይነት ታአምር ነው፡፡እንደውም ከዛም በላይ ነው.፡፡ለሰው ሊያስረድት ከሚችሉት በላይ...ለራስም አስበው ሀሳቡን ለመቋቋም ከሚችሉት በላይ…በመኖር እና ባለመኖር መካከል ያለች የሳሳች በጣም ቀጭን የህይወት ክር ላይ አንጠልጠሎ የሚያላጋ ስሜት ላይ የሚያስቀምጥ፡፡
ሙሉ በሙሉ ጥቁር ለብሳለች….ከለቅሶ ብዛት አይኗቹ ከተገቢው በላይ ማበጣቸው ካደረገችው ግዙፍ ጥቁር መነፅር እንኳን ሙሉ በሙሉ ሊከልላቸው አልቻለም፡፡ከሁለት ቀን እራስን የመሳትና የሆስፒታል ቆይታ ቡኃላ ነው እንደምንም ተደግፋ ቀብር ላይ የተገኘችው፡፡የፕሮፈሰሯ ሆነ የእሷ ቤተሰቦችና ወዳጇች በብዛት ተገኝተዋል፡፡ከዛም በላይ ወሬ ቃራሚ የሚዲያ ሰዎች ከለቀስተኛው ጋር በመመሳሰል ፤ አንዳንዱ መንነታቸውን የሚለይ ባጅ አንገታቸውን አንጠልጥለው በግልጽም ተገኝተዋል፡፡
የቀብር ፕሮግራሙ ብዙ ሀሜቶችና ጉረምርማተዎች የታጀበ ነበር....የአልቃሹ ቁጥር የአንድ ሰው የእጅ ጣት አይበልጥም…በሀዛን የተሰበሩት ፤.ከልባቸው በመንሰፍሰፍ የሚያለቅሱት ደግሞ ፕሮፌሰሯና ሲፈን ብቻ ናቸው….እርስ በርስ የእየተቃቀፉ..እርስ በርስ እየተደጋገፉ…እርስ በርስ እየተፅናኑ ይህንን የጨለማ ቀን ግዙፍ ተራራን ለመግፋት እየጣሩ ነው….ከገቡበት ጥቅጥ የብቸኝነት ጨለማ ዋሻ በእንዴት አይት ፅናት ገብተው ሳይፈራርሱና ማንነታቸውን ሳያጡ ከዚህ ክፉ ፈተና እንዴት ማገገም እንደሚችሉ በየልባቸው እየተማከሩ ነው፡፡
ቀብሩ ከተጠናቀ ብኃላ ያው በደንቡ መሰረት ቀጥታ ወደፕሮፌሰሯ ቤት ነው ያመሩት ፡፡ቤተሰቦቾም ሆኑ ሄኖክ ከሚከታተሏት ሰዎች ጋር የነበራቸውን ውል ሙሉ በሙሉ አቋርጠዋል፡፡እናም አሷ ግድ ባይኖራትም አሁን በየሄደችበት እየሄደ የሚከታተላት ሰው ከጀርባዋም ሆነ ከፊቷ የለም፡፡
///
..ቀብሩ ከተጠናቀ በሶስተኛው ቀን ቡኃላ ፕሮፌሰሯ እና ሲፈን ፖሊስ ጣቢያ ተጠሩና ሁለቱም በአንድላይ መርማሪ ፖሊስ ፊት ለፊት ቀረቡ፡፡
‹‹ከቢላል ጋር ያላችሁን ዝምድና ወይም ግንኙነት?››የፖሊሱ ጥያቄ ነበር
‹‹ሁለቱም ተራ በተራ አብራሩ››
‹‹ሲፈን ..ቢላልን ለመጨረሻ ጊዜ ያየሽው መቼ ነው?››
‹‹ከሞቱ ከስድሰት ወይም ከሰባት ሰዓት በፊት››
‹‹የት ?››
‹‹እቤቴ ማለት አባቴ ቤት እኔ ክፍል››
‹‹ምን ሊሰራ ነበር የመጣው ..?››
‹‹ያው እደነገርኩህ ቤላል ጓደኛዬ ነው…ድንገት ከተሰወረ ከ22 ቀን ቡኃላ ለሊት ላይ የቤታችን ጣሪያ ቀዶ ነበር የገባው…እና ያንን በማደረጉ በነፍሴ ጭምር ነበር የተደሰትኩት፡፡ ከዛ ቡኃላ በተከታታይ ሀያ ለሚሆኑ ቀናት ከዛ ክፍል አልወጣም ነበር.››
‹‹ሀያ ቀን ሙሉ››
አዎ …ብዙ ነው እንዴ …?.ለእኛ ግን የሁለት ቀን ያህልም ርዝመት አልነበረውም….እንዴት መሽቶ እንዴት እንደሚነጋ አናውቅም ነበር…ዋናው ጭንቀታችን የእሱን እዛ መኖር እቤተሰቦቼ ወይም ሌላ ሰው እናዳያውቅ ማማረግ ነበር.ያም ተሳክቶልና.፡፡.በህይወቴ ትልቅ ትርጉም ያለው የሚገርም ጊዜ ነበር ያሳለፍነው….እድሜ ልኬን ከእዛ ክፍል የመውጣት እቅዱም ፍላጎቱም አልነበረኝም…የውጩን አለም ጠቅላላ ዘንግቼው ነበር..ምንም የሚናፍቀኝ ነገር አልነበረም…ስራዬ..ሀብቴ ሰሜ ..በእቅፌ ከነበረው ቢላል ጋ ሲነፃፀሩ ምንም ትርጉም አልነበራቸውም፡፡››ረጅም ትንፋሽ ወሰደችና በጉንጮቾ ላይ ያለከልካይ የሚፈሰውን እንባ በሶፍት መጠራረግ ጀመረች…ከዛ ፀጥ አለች
‹‹ቀጥይ ..እየሰማውሽ ነው››አንስፔክተሩ ነው በገለፃዋ እንድትቀጥላ ያበረታታት.ፕሮፌሰሯ በእንባ ከማገዝ ውጭ በዝምታ እንደተዋጠች ነው፡
‹‹ወደዋናው ነጥብ ልምጣልህና የሞተ ቀን ማለቴ አሁድ አብረን በደስታ አደርን ጥወታ በማለዳ ነቃንና ….ብዙ የደስታ ወሬዎች አወራን...ሳቅን.. .ተላፋን…..የምንወደውን ሙዚቃ በአንድ ኤሮፎን አዳመጠን….ሁለት ሰዓት ተኩል አካባቢ ልክ እንደሌሎቹ ቀናት የምንበላውን ቁርስ ለማምጣት በውጭ ቆለፍኩበትና ወደኪችን ሄድኩ፡፡ ብዙም አልቆየውም .. ከ10 ወይም ከ12 ደቂቃ ቡኃላ የምንበላውን ቁርስ ይዤ ስመጣ ክፍሉ ባዶ ነበር…ሻወር ቤት ፈልኩ ..አልጋ ስር ሳይቅር ፈለኩ…በጣም ደንገጥኩ.. ልጮህ ሁሉ ነበር፣.ቡኃላ ጠረጳዛ ላይ መልዕክት ትቶልኝ ነበር›
‹‹ምን ይላል መልዕክቱ?››
‹‹እማዬ ናፍቃኛለች…እሷ ጋር ሄጄያለው…በተለመደው መልክ ማታ ተመልሼ መጣለው…በጣም እወድሻለው›› ይላል፡
ከዛ ተረጋጋው.‹. ቢሆንም መንገድ ላይ አደጋ ያጋጥመው ይሆን…?› የሚል ስጋት ስላለብኝ ከአንድ ሰዓት ቡኃላ መሰለኝ ለፖሮፌሰር ደወልኩና ጠየቅኳት ..በደስታ እሷ ጋር እንዳለ ነገረችኝ..፡፡
ከዛ ቡኃላ በቃ ሰባት ሰዓት ላይ ተደውሎልኝ እራሱን አጥፈቷል ተባልኩ…መአት ነው የወረደብኝ…ከከረምኩበት ገነት የሆነ ክፉ አጋንንት በእንዴት አይነት ፍጥነት አሽቀንንሮ ሲኦል እንደጨመረኝ አልገባኝም…አለም ግን እንዴተ አስቀያሚ ነች….ጠንካራ አለት ነው ብዬ የቆምኩበት አፈር ነው ድንገት ተደርምሶ እንጦሮጦስ ወስዶ ያሰመጠኝ፡፡››በእንባዋ እየታጣበች በመሪር ሀዘን የነበረውን ነገር አስረዳችው፡፡
‹‹እሺ ፕሮፌሰርስ?››
‹‹እሷ እንዳለቸው ነው.ሶስት ሰዓት ሲሆን ሳሎን ቁጭ ብለን ቁርስ አየበላን ሳለ . በሩ በዝግታ ተከፈተ… አይኔን ወደዛ ስልክ የእኔ ምስኪን ልጅ ነበር..፡፡ብታይ አምሮበታል…እነዛ ሰማያዊ አይኖቹን እላዬ ላይ ሲያንከባልላቸው የተሰማኝ የደስታ ስሜት ልግልፃልህ አልችልም...ከአርባ ምናምን የጭንቅ ቀን ቡኃላ ነበር ልጄን ያቀፍኩት …እቤቱን በጪኸት አስነካውት፤ ግቢው ውስጥ ያሉት ሰዎች ሁሉ ተሰበሰቡ ፡፡