Get Mystery Box with random crypto!

#ቃል #ዳንኤላ_ስቴል ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ ምዕራፍ ሰባት (7) በሩ ላይ ቆማ ለረጂም ጊ | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

#ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ ሰባት (7)


በሩ ላይ ቆማ ለረጂም ጊዜ ፍዝዝ ብላ ቆየች ። ልግባና. . . ላድርገው? ... ግራ ገባት ። ለማይክል ነው። ለማይክል ስል ነው። ማይክልን ነፃ ማውጣት አለብኝ አለች ራሷን ለማበረታታት ። ቀስ እያለች እግሮቿን እየጐተተች ወደ ክፍሉ ውስጥ ገባች።

ክፍሉ ጨለማ ነበር። ምንም ብርሃን እንዳይገባ የተከለከለ ይመስላል። መብራቱም አልበራም ። ሻተሮቹም ተዘግተዋል ። አሁንም የለቅሶው የማንተግ ድምፅ ይሰማታል ። ቀስ ብላ ተጠጋች። አልጋው እንደ ጥላ ሆኖ ይታያል ። የልቅሶው ድምፅ ጐላ እያለ ይሰማ ጀመር። «ሰውነው... ማነው? » አለች ናንሲ ። ማሪዮን ተጠጋች። የናንሲ ራሷ ፊቷ በጠቅላላ በፋሻ ተጠቅልሏል ። ድምጺም የታፈነና እንግዳ ነገር ሆኖ ተሰማት ለናንሲ ለራሷ።
«ማነው... ሰው አለ?» አለች ናንሲ ። እና ታለቅስ ጀመር ። «አይኔ አያይም ... ሰው አለ?... አይኔ ፈፅሞ አያይም» አለችና ሳግ አከታትሎ ይነትጋት ጀመረ ። « አይንሽ ምንም አልሆነም ። ሁለቱም አይኖችሽ ደህና ናቸው፤ እንዳታይ የሚከላከልሽ የተሸፈንሽበት ፋሻ ነው» አለች ማሪዮን፡፡ ናንሲ ይህን ብትሰማም ለቅሶዋ ጨመረ ።
«ለምንድን ነው እንቅልፍ ያልወሰደሽ?» አለች ማሪዮን ድርቅ ባለና ስሜቱ በተሟጠጠ ድምፅ «የሚያስተኛ መድሀኒት አልሰጡሽም ?» ማሪዮን ራሷ በህልሟ የምትነጋገር መስሎ ተሰማት። .... መርፌ ወግተውኝ ነበር። ግን መድሀኒቱ ሊሰራ አልቻለም። እንቅልፍ ባይኔ አልዞር አለ» አለች ናንሲ። «ይጠዘጥዝሻል...ወይም ውጋት የመሳሰለ ህመም አለው «ምንም አይሰማኝም ። አካሌ በጠቅላላ ደንዝዟል ። ማን... አንቺ ማን ነሽ?» ስሟን ልትነግራት አልደፈረችም ። በዚያ ፋንታ አልጋው አጠገብ ወንበር ስላየች ሂዳ እዚያ ላይ ቁጭ እለች ። የልጅቷን እጅ አየች። ሁለቱም እጆቿ እንዲሁ በፋሻ ተጠቅልለዋል አይንቀሳቀሱም ። ትዝ አላት ዶክተር ዊክፊልድ የነገራት ። ፊቷ እንዳይጐዳ በእጅዋ መከላከሏ ያለ ነው ። ስለዚህ ሁለቱም እጆቿ በጣም ተጐድተዋል። ለወደፊቱ በሰዓሊነት ሀይወቷን ለመቀጠል ተስፋ የላትም ስትል አሰበች ።

‹‹ናንሲ» አለች ማሪዮን ለመጀመሪያ ጊዜ ይህን ስም እየጠራች። ግድ የለም ይሁን ለማይክል ስል... ‹‹ናንሲ ....» ድምጺ ለስለስ ያለ ነበር ። «ፊትሽ ምን ያህል እንደተጐዳ ሀኪሞቹ ነገሩሽ » .. በክፍሉ ፀጥታ ነገሰ። ዘለአለም አለም ያህል ጊዜ ሁለቱም ጸጥ ብለው ቆዩ። ድንገት የለቅሶ ሳግ ፀጥታውን አደፈረሰው «በፊትሽ ላይ የደረሰው አደጋ መጠን ከምን እስከምን እንደሆን ነገሩሽ ? አሰቃቂ እንደሆነ አውቀሽዋል ?» አለች ማሪዮን አሰቃቂ የሚለውን ቃል ስትናገር ልቧ ሊከዳት ምንም አልቀራትም። ሁሉ ነገር አስጠላት ። ሆዷ ተገላበጠ ። አንጀቷ ተላወሰ ወዲያው የለም፣ መዳከም አያስፈልግም አለች ማይክልን እያሰበች። «ናንሰ. ፤ የቀድሞ መልክሽን መመለስ ይትርና ትንሽ እንኳ ለማስተካክል በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ እንደተበላሸሽ ነግረውሻል?» አለች ማሪዮን ። የናንሲ ለቅሶ ቁጣ የተቀላቀለበትና ስቃይ የተሞላበት ሆነ።
«አልነገሩኝም ዋሽተውኛል እነሱ ያሉኝ...»
«ናንሲ ፤፡ ሀክምናውን ሊያደርግልሽ የሚችል በሀገሪቱ ውስጥ ያለ አንድ ሃኪም ብቻ ነው ። እሱን ለማግኘትም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዶላሮች ያስፈልጋሉ ። ይህን ያህል ገንዘብም አንች የለሽም ማይክልም አያገኝም »
«ቢኖረውም ያን ያህል ገንዘብ ከፍሎ እንዲያሳክመኝ አልፈቅድም «» የሚያነጋግራት ድምፅም ኑሮና እድልዋም አናደደዷት፤ «አልፈቅ. .. ቅድለትም » አለች ሳግ ኢያቋረጣት ።
«ያሰብሽው ነገር አለ?» አለች ማሪዮን ።
«ምንም ያሰብኩት ነገር የለም!»
«ይህን መስለሽ የማይክልን ፊት ማየት ትደፍሪያለሽ ? እሱስ የሚችል ይመስልሻል ? ርግጥ መቼም በይሉኝታ ትንሽ ሊሞክር ይችላል ። ታማኝ ለመሆን መሞከሩ አይቶርም ። ግን ያን ሁሉ የሚያደርገው ወዶሽ ሳይሆን አዝኖልሽ እንደሆነ እያወቅሽ ደስታ ልታገኝ የምትችይ ይመስልሻል !? » ከዚያ በኋላ ማሪዮን እነገሩ ውስጥ ዝፍቅ ብላ ገባችበት ።
«ናንሲ … ሃኪሞቹን አነጋግሬ ነበር ከድሮው ገፅታሽ አንድም ያልተለወጠ ነገር የለም ። ፊትሽ ፈፅሞ ሌላ ሆኗል ። ስለዚህም የነበረሽ ነገር ሁሉ የለሽም ። ካሁን በኋላ ... ከዚህ በፊት ከኖርሽው ነገር ላንቺ የሚሆን እንደሌለ መገንዘብ አለብሽ ለተወሰነ ጊዜ ሁለቱም ፀጥ አእሉ። ማሪዮን ቀጠለች ። «ከማይክል ጋር ለመኖር ብትሞክሪ ከላይ እንደነገርኩሽ ላንቺም ለሱም ስቃይ እንጂ ሌላ ትርፍ የለውም ። ስለዚህ ቁረጪ ናንሲ። ተለያይታችኋል በቃ ።ማለት ከወደድሽው ይ…ገባሻል። ለሚወዱት ሰው ስቃይ መሆን ደስ አይልም ። አንቺም:..አንቺም ቢሆን መሰቃየት የለብሽም ። አንቺም አዲስ ህይወት ሀ ብለሽ ልትመሰርቺ የምትችይበት መንገድ አለ ናንሲ » ማሪዮን ናንሲ ትናገር እንደሆነ ጠበቀች ናንሲን ግን ሳግ ሲነትጋት ይሰማ እንጂ ምንም ቃል አልተነፈሰችም ። «ይህ ቢሆን አዲስ ህይወት ፤ አዲስ አለም ልታገኝ የምትችይበት መንገድ ይኖራል » አለች ማሪዮን ። አሁንም መልስ የለም ። «አዲስ ፊት ፤ አዲስ ገፅታ ፣ አዲስ ኑሮ!» አለች ማሪዮን ሳጉ ቆመ ።
«ከየት ? እንዴት ›› አለች ናንሲ ።
«እኔ እማውቀው ሰው አለ ። ሳንፍራንሲስኮ ውስጥ የሚኖር። ይህ ሰው እንደገና ቆንጆ ሴት ሊያደርግሽ ይችላል ። ይህ ሰው የስእል ስራሽን እንድትቀጥይ ሊያደርግ ይችላል ። ይህን ለማድረግ በርግጥ ረጂም ጊዜና በርካታ ገንዘብም ይወስዳል ። ሆኖም ገንዘብም ቢጠፋ ፤ ጊዜም ቢወስድ ከሚገኘው ጥቅም ጋር ሲነፃፀር ኢምንት ይሆናል ። አይመስልሽም ናንሲ?›› አሁን ማሪዮን በነገሩ ገባችበት ። ውል መዋዋል ነው የንግድ ውል ። በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚተረፍበት ውል። ያ ደግሞ ሥራዋ ነው።

«ታዲያ ያን ያህል ገንዘብ እኛ ከየት እናመጣለን!›› አለች ናንሲ። «እኛ» የሚለውን ቃል ስትሰማ ማሪዮን ሂልያርድ ሽምቅቅ አለች ። « እኛ›› ያለችው እሷን ከማይክል ጋር ደብላ መሆኑ ነው ስትል አሰበች። ተናደደች። ቢሆንም ለጊዜው መቻል አለባት። ይህን የጀመረችውን ነገር በትእግስት ከዳር ማድረስ አለባት፡፡
«ልክ ነሽ ናንሲ ። በቀላሉ የሚቻል አይደለም ። ግን እችላለሁ ። ማን እንደሆንኩ እስካሁን ሳታውቂ አልቀረሽም፤ አይደለም ?››
« አውቄአለሁ»
«እንዳልኩሽ ማይክል ከእንግዲህ ያንች ሊሆን እንደማይችል ገብቶሻል ፤ አይደለም ? በተለይ እንዲህ ሆነሽ ቢያይሽ እሱንም ፀፀቱ ሊገለው እንደሚችል ይገባሻል ፤ አይደለም
«ይገባኛል »
«ስለዚህ ታማኝነትህን አሳየኝ ማለት ያውም ቢተርፍ ማለቴ ነው፤ መፈታተን ፤ በጣም ከፍተኛ የሆነ ክፋት እንደሆነ ትረጃለሽ፤ አይደለም ናንሲ ? ይህን አእትረጂም ?›»
«እረዳለሁ » አለች ድክም ባለ ድምፅ ።
«ስለዚህ የቀረ ነገር ቀርቷል ።። የጠፋ ነገር ጠፍቷል ፤ አይደለም?»
«አዎ»
«ናንሲ ፤፡ አንድ ሃሳብ ላቀርብልሽ እፈልጋለሁ ። ድርድር ነው፡።፡ እንደምንስማማ ተስፋ እለኝ፡፡