Get Mystery Box with random crypto!

አሁን የንግድና የድርጅት ባለቤት የሆነችው ማሪዮን ሂልያርድ ሙሉ በሙሉ ብቅ አለች ። ልጅዋ ይህን | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

አሁን የንግድና የድርጅት ባለቤት የሆነችው ማሪዮን ሂልያርድ ሙሉ በሙሉ ብቅ አለች ። ልጅዋ ይህን ሁሉ ስትል ቢሰማ ልግደልሸ ሳይላት አይቀርም ነበር ። «ናንሲ ፤ እስኪ ስለአዲሱ ገፅታሽ አስቢ ። ስለአዲሱ ህይወትሽ አስቢ። ስለ አዲሲቷ ናንሲ አስቢ። ስለነዚህ ነገሮች አስቢ አሁን ካለሽበት ሁኔታ ወጥተሽ ስለምታገኝው እዲስ ህይወት አስቢና አመዛዝኝ ፣ ናንሲ ። « በሌላ በኩል እንዲህ እንዳለሽ ብትኖሪ የሚመጣብሽን ደግሞ አስቢው ። እንዲህ ማስፈራሪያ መስለሽ ምን ሆነሽ ልትኖሪ ትችያለሽ? ሱቅ ብትገቢ ፤ ሰዎች ለማየት ይፀየፉሻል። በመንገድ ላይ ድንገት ያዩሽ ሰዎች ይበረግጋሉ ። ህፃናት አይተውሽ አሪ ብለው ያለቅሣሉ ይህን ደሞ አስቢው ። እንዲሀ ሆኖ መኖር የሚቻል ይመስልሻል ? ግን እንዲህ ያለመሆን አማራጭ አለሽ»
«ምንም አማራጭ የለኝም›› እለች ናንሲ ።
«አለሽ ናንሲ… አለሽ ። አዲሱ ህይወት በእጅሽ ነው ፤ ካወቅሽበት ማለቴ ነው» ማሪዮን ከመቀመጫዋ ተነሳች ። እና ቀጠለች «ቀላል ነው ከባድም ሊሆን ይችላል ። ግን አማራጭ ነው» መምረጥ አለብሽ ናንሲ።

ናንሲ አዲሱ ህይወት በእጅሽ ነው የተክፈለውን ያህል እክፍላለሁ ፡፡ ግን አንች ደግሞ ውል ትገቢያለሽ ፤ ከማይክል ጋር ምንም አይነት ግንኙነት ላለማድረግ ። ይህን ካደረግሽ አዲሱ ግፅታ የግልሽ ነው። ማይክልን ግን ዞር ብለሽ ማየት የለብሽም ነገር ግን ይህን ስጦታ አልቀበልም ብትይ ዞሮ ዞሮ ያው ነው። ማይክል ያንቺ አይሆንም ። ስለዚህ ህይወትሽን በሙሉ ለምን ማስፈራሪያ መስለሽ ትኖሪያለሽ አማራጭ እያለሽ ? ለኔ አይታየኝም!»
«እኔስ እሺ ልበል። ግን ማይክል ይህን ውል ባይቀበልስ? እኔ ልሽሽ ልደበቅ ፤ ግን እሱ ቢመጣስ? ቢፈልግና ቢያገኘኝስ›› «በዚያ አንች መጨነቅ የለብሽም ። አንች ያለብሽ የራስሽን ቃል ማክበር ብቻ ነው። ማይክል የፈለገውን ቢያደርግ ያ የራሱ ጉዳይ ነው»
«ይህን ቃልሽን ትጠብቂያለሽ ? ማለት እሱ ፈልጐኝ ከመጣ ያ የራሱ ጉዳይ ነው ብለሽ ትተይዋለሽ?»
«ቃል፣ ቃል ነው»

ይህን ስትሰማ ናንሲ ደስ አላት ። በዚህ ድርድር ማሪዮን ሂልያርድን እንደተጫወተችባት ገመተች። ምክንያቱም በማይክል ላይ እምነቷ የጠነከረ ነበርና ነው ። ማይክል መኖሯን ካወቀ እናቱ የፈለገችውን ያህል ብትለፋ ናንሲን ሊፈልግ መምጣቱ እይቀርም ። ናንሲ ይህን ስለምታወቅ ኮራች ፤ደስ አላት
«ተስማማን ወይስ..? መልስሽን አልነገርሽኝም ናንሲ አለች ማሪዮን ። በዛባት መቆየት አትችልም ፤ከዚህ በላይ።
« ተስማምተናል » አለች ናንሲ ።

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj