Get Mystery Box with random crypto!

እንዲህ እያለ በቀላሉ የረጅም ጊዜ ትውውቅ ያላቸው እስኪመስላት ራሱን አላመዳት ። ባንዴ ። ይህን | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

እንዲህ እያለ በቀላሉ የረጅም ጊዜ ትውውቅ ያላቸው እስኪመስላት ራሱን አላመዳት ። ባንዴ ። ይህን ሁሉ የሚላት ለመቀራረብ ብቻም አልነበረም። በረጂም ጉዞ ላይ ስለነበረች ለጥቂት ጊዜ ያላንዳች እንቅስቃሴና ሀሳብ ስታርፍ ሰውነቷ በቀላሉ ዘና እንደሚል ስላወቀም ነበር ። ነርሶቹም ደስ አላቸው ። እነሱም ከጉዞ ጣመናቸው ማረፍ ያስፈልጋቸው ነበርና ካንቡላንስ ነጂው ጋር እያወጉ ይዝናኑ ነበር። ወደናንሲ አይናቸውን ጣል ሲያደርጉ ዶክተር ግሬግሰን ናንሲን ሲያጫውታት ስላዩ ስውየው ደስ ብሏቸዋል ።
«እኔ ? እኔ እንኳ ያደኩት ኒው ሃምፕሻዬር ነው ። እናትም አባትም አልነበረኝምና እዚያው ባለ የእጓለማውታን ማሳደጊደያ ውስጥ አደኩ ። ወደ ቦተስን የመጣሁት አስራ ስምንት አመት ከሞላኝ በኋላ ነው»
«ይኸማ ልብ የሚሰቅል ታሪክ ነው። ወይስ ማሳደጊያ ቤቱ በቻርልስ ልቦለዶች ውስጥ እንዳሉት ያለ በጭካኔ የተሞላ ነበር» አለ ፒተር ። ናንሲ በፒተር አጠያየቅ ፤ በተለይም ሁሉን ነገር ቀላል አድርጐ በመቀበል ችሎታው ተገረመች የዲክንስ የእጓለማውታ ማሳደጊያዎችን ማሰቡ አሳቃት ።
«ዲክንስ ውስጥ ? በፍጹም ! ያሳደጉኝ መነኩሲቶች በጣም ዶጋጐች ነበሩ ። ደስ የሚሉ። በዚህ የተነሳ እንዲያውም እኔም እራሴ ለመመንኮስ ሀሳብ አድሮብኝ ነበር ። እንደነሱ ለመሆን አለች ናንሲ ።
«አረ የስላሴ ያለህ ! ጆሮ አይሰማው የለ ! ስሚ የኔ እህት» አለ ፒተር ፤ናንሲ ሳቀች ።
«የኔ እህት ልክ ህክምናውን እንደጨረስሽ በቀጥታ ወደ ፊልሙ ከተማ ወደ ሆሊውድ!... ገባሽ?... ነገር ግን... ይህን አይሆንም ብለሽ ቁንጅናሽን ይዘሽ ገዳም ብትገቢ አያድርገውና !... ገዳም ብትገቢ እኔ ምን የማደርግ . . . እኔ ሌላ ምንም አላደርግም ። ወደወደብ ሄጄ፤ አንዱ ቋጥኝ ላይ ወጥቼ፤ ከዚያ ላይ ተወርውሬ ስምጥ ። በቃ ። የለም የለም ፤ እንዲሀ በቀላሉ አንላቀቅም ። እንዲያውም ህክምናዬን ከጨረስኩ በኋላ ቁንጅናዬን አንድ ገዳም ወስጄ ላልደብቅ ለፒተር ግሬግሰን ቃል እገባለሁ ስትይ ማይልኝ፡፡ ይህ ቀልድ ነው ። ሆኖም እንደዘበትም ቢሆን ቃል መገባት ደግ አይደለም ። ይህን ታውቃለች ። ትወቅ እንጂ ቃል ለመግባት ደግሞ አይከብዳትም ። ምክንያቱም እካሏ ይመለሰን እንጂ ወደየት እንደምትሔድ ታውቃለች ። ማይክል አለላት ። በዚያ ላይ ሞግዚቷና እናቷ እንደነበሩት እማሆይ ሜሪ የመሆን ፍላጐቷም አስቀድሞ ጠፍቶ ነበር ። ይህ ሁሉም ሆኖ ትንሽ ጫወታ አይጎዳም በማለት ፣ «እንዲያ ከሆነ እሺ›› አለች
«ምንድነው እሺ ? ቃል ገባሁ ማለችሽ ነው? ቃል በቃል ልትናገሪ ይገባል። ቃል ገብቻለሁ በይ »
«እሺም ቃል ኪዳን ነው። ስለዚህም ቃል ገግብቻለሁ
«ቃል ገብቻለሁ ! ብሎ ነገር ምን ለመሆን ነው ቃል የገባሽው ?»
«መነኩሴ ላለመሆን››
«እፉፉዎዬ ! አሁን ቀለል እለኝ » አለ ፒትር ።

እስካሁን ሰውነቷ ዘና እንደሚል ገባው ። ስለዚሀም ነርሶቹ እንዲወጡ በጥቅሻ ጠራቸው ። በወሬ ብዙ ማድከሙም ደግ እይደለም። ይበቃታል ፤ ሲል እያሰበ ። ሁለቱ ነርሶች ሲመጡ
«ከጌደኞችሽ ጋር ለምን አላስተዋወቅሽኝም ? » አላት ።
«ደግ » አለችና ናንሲ ፤ «ባለሰቀዝቃዛ እጅዋ ሊሊ ትባላለች ። ባለሞቃት እጅዋ ደግሞ ግሬችን ትባላለች» አራቱም በዚህ ንግግር ሳቁ ።
«አመሰግናለሁ ናንሲ » ሊሊ የናንሲን እጅ በማበረታታት መንገድ ጨበጥ አደረገች ። ናንሲ በድንገት ደስ አላት ። እኒህ ሶስት ጓደኞቿ ምንም እንኳ እንግዳ ቢሆኑ የልብን የሚነግሯቸው የሚተማመኑባቸው ጓደኞቿ እንደሆኑ ተገነዘበች ። እነሱ እያሉ ምንም ችግር ይኖራል የሚል ሥጋት አልነበረባትምና ስለአስታማሚና ስለመሳሰሉት ያላትን ሀሳብ አራገፈች ። ይህን አራግፋ ፤ድና ስትወጣ ለማይክል ምን መስላ እንደምትታየው ታሰላስል ጀመር። ፒትር ግሬግሰንን አሰበችው ። የሚቀበሉት ፤ የሚወዱት ሰው ሆኖ አግኝታው ነበርና በህክምናው ተማመነችበት ። ውብ መልክ እንደሚሰጣት ገባት ምክንያቱም ለሰው ፍቅር አለው ። ስለዚህም ይጠነቀቃል ፤ ይጨነቃል ።"

«ወደ ሳንፍራንሲሰኮ እንኳን ደህና መጣሽ ብጥሌ!›› አለ ፒተር ግሬግሰን ። የሊሊ ሚጢጢ እጅ ናንሲን ለቅቋት የፒትር ሰፊ እጅ ያዛት ። ማረፊያቸው እስኪደርሱ ድረስ ማለትም በመንገድ ላይ አምቡላንሰ ውስጥ እጅዋ በእጁ ውስጥ ነበር ። በሚያስገርም አኳኋን ስሜቷን ሁሉ ቀየረው ። እናም የመጣችው ወደማታውቀው ሰፍራ ሳይሆን ወደ ቤቷ፤ ወደትወለደችበት ሀገር እንደሆነ አድርጋ ገመተች......

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj