Get Mystery Box with random crypto!

#ቃል #ዳንኤላ_ስቴል ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ ምዕራፍ አስር (10) የአንቡላንሱን በር ቦግ | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

#ቃል
#ዳንኤላ_ስቴል
ትርጉም፣ ባሴ ሐብቴ

ምዕራፍ አስር (10)


የአንቡላንሱን በር ቦግ አድርገው ከፈቱና ወሳንሳውን በጥንቃቄ ተሸክመው ወደ ሆቴሉ ገቡ ። የሆቴሉ ማኔጀር እውጭ ደረጃውን ወርዶ ነበር የተቀበላቸው ። ወደተዘጋጀላቸው ክፍል እየመራ ወሰዳቸው ። በሆቴሉ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ቪላ ያህል ምቾትና ስፋት ያለው ክፍልና ዙሪያ ገባው በጠቅላላ ለእነሱ ሲባል ተለቆ ነበር ። ሁለት ወይም ሶስት ቀን ያህል እዚህ ሊቆዩ አስበዋል ። ይህ የሆነው ደግሞ በሁለት ምክንያት ነው። አንደኛ ማሪዮን ሂልያርድ ቦስተን ከተማ ውስጥ አንድ ስብሰባ ላይ መገኘት ነበረባትና ወደኒውዮርክ ለመመለስ አትችልም ነበር። ሁለተኛ ማይክል ወደ እናቱ መኖሪያ ቤት ከመሔዱ በፊት ከሆስፒታል ወጥቶ ለትወሰነ ጊዜ ሆቴል ውስጥ ለመቆየት እንደሚፈልግ ተናግሮ ነበር። እርግጥ ነው የማሪዮን ስብሰባ ቢኖርም ማይክል ግን ወደ ቤት ሄዶ እዚያው ኒውዮርክ ሊጠብቃት እንደሚችል ታውቃለች ። ግን ደግሞ ሆቴል መቆየት እፈልጋለሁ ካለ ይህን ፍላጎቱን ማሟላት አለባት። ምንም እንኳ ፍላጐቱ የልጅ ቢመስልም ማሪዮን የጠየቀውን ሁሉ ልታሟላለት በልቧ ዝግጁ ነበረችና ይሁን ብላ ተቀበለችው ።

የአንቡላንስ ሠራትኞች ከናወሳንሳው አውርደው እንደሚሰበር ዕቃ ተጠንቅቀው አልጋው … ሲያስተኙት «ማሚ ፤ በክርስቶስ ይዤሻለሁ ፤ይህን ያህል ጥንቃቄ አያስፈልገኝም ። ሀኪሞቹን ሰምትሻቸው የለም? ደህና ነው፤ምንም አልሆነም ፤ ነበርኮ ያሉሽ » አለ ማይክል ።
«ቢሆንም ፤ ቢሆንም ችላ ማለት ደግ አይደለም» እለች ማሪዮን።
«ችላ ማለት ? » እለ ማይክል ። ይህን ብሎ ክፍሉን እየቃኘ ትንሽ አጉረመረመ ። ማሪዮን ዝም ብላ ለእምቡላንሱ ሠራተኞች ጉርሻ ትሰጥ ነበር ።

ክፍሉ በተለያዩ የእበባ ዓይነቶች ተሞልቷል ። አልጋው አጠገብ በሚገኝ ጠረጴዛ ላይም አንድ ችልቅ ቅርጫት በፍራፍሬ ተሞልቶ ተቀምጧል ። ዝግጅቱ ማይክልን እምብዛም አላስደነቀውሙም ። ምክንያቱም ሆቴሉ የማሪዮን ሂልያርድ ንብረት ነው ባሊፈው ዓሙት እንደ ገዛችው ያስታውሳል
« አሁን ዘና በላ የኔ መኳንንት ስለምንም ነገር ማሰብ መጨንቅ አያሻህም ። በነገራችን ላይ የሚበላ ነገር ምን ይምጣልህ ? » አለች ነገራት።
«ምን ዓይነት የምግብ አመራረጥ ነው የኔ ሸጋ ? » አለች። እውነቱን ለመናገር ግን ምርጫው ተስማሚ ይሁን አይሁን አላወቀችም ። ምክንያቱም አልሰማችውም። እሱ ምግብ ሲዘረዝር የሷ ሀሳብ እቀጠሮዋ ላይ ስለነበር ሰዓቷን በማየት ላይ ነበረች። ስለዚህም «እንግዲህ እንደፍላጎትህ አድርግ ። ማለት የሚያስፈልግሀን ነገር ራስህ ማዘዝ ትችላለህ ። በበኩሌ ፤ ጆርጅ እንደመጣ መሄድ አለብኝ ወደ ስብሰባው›› አለች ። ይህን እንዳለች ደወሉ ተንጫረረ ። በሩ ሲከፈት ጆረጀ ኮሎዌ ነበር ።
« እሺ ፤ አሁንስ እንዴት ነው ? ተሻልህ ፤ ማይክል ?»
«ደህና ነኝ ። ብቻ ሁለት ላምንት ሙሉ እሆስፒታል ውስጥ ያላንዳች ስራ ተጋድሜ ሰንብቼ ስለወጣሁ በሁኔታው እፍረት ቢጤ እየተሰማኝ ነው»

ማይክ የልቡን በልቡ ይዞ በአፉ ይህን ይበል እንጂ በገፅታው ላይ ግን የተሰበረ ስሜት ጉልህ ሆኖ ይታይ ነበር ። እናቱም ያንን ገፅታውን እይታለች ። ግን ድካም ነው ፤ ድንጋጤ ነው ፤ ሌላ ምንም አይደለም ብላ ራሷን አስተማምና ተፅናንታለች፡፡ ስለናንሲ ያስባል ፤ የናንሲን «ሞት» በመስማቱ ነው ይህ ሁኔታ የሚታይበት ለማለት አልደፈረችም ። ከዚህ ሀሳብ አጥብቃ ትሸሻለች ። ማይክል ሆስፒታል ውስጥ በቆየበት ጊዜም ስለአደጋው ፈፅሞ እያነሱም ነበር ፤እናትና ልጅ። የሚወያዪት ስለ ድርጅቱ እድገት፣ በተለይም በሳንፍራንሲስኮ ስለሚሰራው የሕክምና ማእከል ኮንትራት እና ስለሚገኘው ትርፍ ነበር ።
« ዛሬ ጧት ከኒውዮርክ ከመነሳቴ በፊት አዲሱን ቢሮህን ተዘዋውሬ አየሁት ። መቼም ድንቅ ቢሮ ነው» አለ ጆርጅ በግርጌ በኩል አልጋው ላይ እየተቀመጠ።
«ገና ሲጀመር ታውቆኛል።ድንቅ ቢሮ ነው ፤ አይደል ? » አለ ማይክል ።ልብሷን ቀይራ የምትመለሰውን እናቱን እየተመለከተ «ማሚ ጥሩ ነገር የማቀድና የመምረጥ ችሎታ ስላላት ቢያምር አያስደንቅም »
«እሱ ላይ ልክ ብለሀል» አለና ጆርጅ ሞቅ ባለ ፈገግታ ማሪዮንን ተመለከታት ። ይህን ጊዜ ማሪዮን በእጅዋ ባዶውን አየር ቁልቁል ወደኋላ እየገፋች «የአፍ ሹም ሽረቱን ተዉት ። ይልቅ ሳይረፍድ አልቀረምና ቶሎ ተነሳ እንሂድ ፤ ጆርጅ » አለች « በነገራችን ላይ ጆርጅ ለመሆኑ አስፈላጊ የሆኑ መዘክሮችን አጠናቀህ ይዘሀል? »
« በሚገባ »
‹‹እንግዲያስ እንሂድ» ብላ ወደ አልጋው ሂዳ ግንባሩን እየሳመችው «ማይክል የኔ ቆንጆ ምንም ማሰብ አያስፈልግም በደንብ እረፍ። ነገ ቀጥ ብለህ መስራት ልትጀምር ነው ። በነግራችን ላይ ምሳህን እንዳትረሳ» አለችው ።
«አልረሳም። ደህና ዋሉ መልካም ስብሰባ። መልካም እድል››
« እድል አልክኝ ?» አለች ሳቅ ብላ « እድልና ስራ በምንም በምን ግንኙነት የላቸውም›› ይህን ስትል ማይክልና ጀርጅ ሳቁ ። ማሪዮንና ጆርጅ ተሰናብተውት ወጡ ማይክልን ።

ልክ ሲወጡለት ከተጋደመበት ተነስቶ አልጋው ላይ ተቀመጠና ማሰብ ጀመረ። የሚያደርገውን ነገር በሚገባ አጥንቶታል፡። ሁለት ሳምንት ሙሉ ምን እንደሚያደርግ አውጠንጥኖ ጨርሷል አሁን ጊዜው ደረሰ ። ባቀደው መሠረት መፈጸም ብቻ ነው ያለበት፡፡ በእቅዱ መሠረት አንደኛው ተፈፅሟል ። ቦስተን ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ መቆየት እፈልጋለሁ የሚለውን ሀሳብ ያቀረበው ለዚህ ነበር።ይህን ምክንያት ቢያቅርብላት ኋላ ይደርሳል ወይም እኔ እንዲፈጸም አደርጋለሁ ትለው ነበር ። ስለዚህ የቅብጥብጥ ልጅ አጉል ፍላጐት የመሰለ ምክንያት ሰጣት ። የፈለገውን በደስታ አደረገችለት ። በዚያ ላይ ብቻውን የሚሆንበት ጊዜ ያስፈልገው ነበር። በስብሰባው ላይ እንድትገኝ ገፋፋት። ጆርጅና አንድ ሌላ ሰው ሊገኙ ይችሉ ነበር ። ግን ለስራው አንቺ ትሻያለሽ ምንም ቢሆን እያለ አሳመናት ።

ድንገት ቢመለሱ በማለት ከወጡ በኋላ ለግማሽ ሰዓት ያህል ከአልጋው ላይ አልወረደም ። ባለበት ቁጭ እለ። ያን ያህል ጊዜ ካለፈ በኋላ ርግጠኛ ሆነ። ከዚያም ልብሱን ይለባብስ ጀመር። ሰውነቱ ያሰበውን ያክል አልጠነከረም። ልብሱ ራሱ አዲስ ሆነበት ፤ ቆሞ መሄድም እንግዳ ነገር።

ወጣ ድካም ሲሰማው እየተቀመጠ ሲያልፍለት እየተነሳ ጉዞ እየቀጠለ። ከሆቴሉ ወጥቶ ታክሲ መጠበቅ ጀመረ ታክሲውን አገኘ። የሚሄድበትን አድራሻ ነገረውና ወደዚያው ተጓዘ፡፡ ታክሲው ራሱ ዳተኛ የሆነ መሰለው። በጣም ቸኮለ። ለረጂም ጊዜ የተለያት ሲሆን ዛሬ ግን በስጋ የቀጠራትን ያህል ሆኖ ተሰማው። እዚያ እስኪደርስ በጣም ቸኮለ። ቆማ የምትጠብቀው እሷም ቀጠሮ እንዳላቸው የምታውቅ እንደሚመጣ የምታውቅ ይመስል ጊዜም መኪናም ተንቆራሰሱበት ።

እቦታው ላይ ሲደርስ በደስታ ፈገግ እለ ፣ ለብቻው ። ክዚያም ሾፌሩን እያዬ ፈገግ አለ ። ጠቀም ያለ ገንዘብ ሰጠው። ጉርሻው ከክፍያው የላቀ ነበር ። እና ዞሮም ሳያየው ፤ ጠብቀኝ ትመልሰኛለህም ሳይለው ጉዞውን ቀጠለ ። ማንም ሰው እንዲጠብቀው አልፈለገም ምክንያቱም የፈለገውን ያህል ጊዜ እዚያ ሊቆይ ይፈልጋል ። እንዲያውም ሀሳቡን አውጥቶ አውርዶ ጨርሶታል። ኪራዩን ሊከፍል ፤ በናፈቀ ጊዜ ወይም በከፋው ጊዜ እዚያ ቤት እየመጣ ሊቀመጥ ፤የተወሰነ ሰዓት ሊያሳልፍ እንደሚችል አውጠንጥኖ በልቡ ተስማምቷል ። ምናለው ? ከኒውዮርክ ቦስተን የአንድ ሰዓት ጉዞ ነው ። ያች አፓርታማ ለሱ ልዪ ነገር ናት፤የናንሲ መኖሪያ ። የናንሲና የማይክል መኖሪያ። የነሱ መኖሪያ ነበረች…ናት ።