Get Mystery Box with random crypto!

እግሯ እየተብረከረከ ቀስ ብላ ወደ አልጋው ሄዶች :: ጎንበከ ብላ ፊቱን ዳበስ ፤ ዳበስ አደረገችው | ✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

እግሯ እየተብረከረከ ቀስ ብላ ወደ አልጋው ሄዶች :: ጎንበከ ብላ ፊቱን ዳበስ ፤ ዳበስ አደረገችው ። «ሄይ ማም» አለ አይኑን ገለጥ አድርጐ ማይክ በዚች ዓለም ላይ ለማሪዮን የእነዚያን ቃላት ያህል ውብ ነገር አልነበረም ። የደስታ እንባ አፈሰሰች ፤እየሳቀች ።
«ማይክ በጣም እወድሀለሁ » አለች ።
«እኔም እወድሻለሁ እናት አለም» አላት ። ይህን ሲያይ በሕክምና ዓለም የኖረውና ብዙ ክፉና ደግ ብዙ ሞት ሽረት ያየው ዶክተር ዊክፊልድ ሳይቀር አይኑን እንባ ቆጠቆጠው። ይህን ለጋ ለግላጋ ወጣትና ይህችን ያህል ጊዜ እንቅልፍ ሳያሸንፋት ፤ እህል ሳያምራት የልጀዋን መታመም ስታብሰለስል ከጎኑ ሳትለየው ለመቆየት የቻለች እናት ሲያይ ሐኪሙ እንኳ አላስችል ብሎት እንባው መጣበት ። ስለዚህም ቀሳ ብሎ ትቷቸው ወጣ ። መውጣቱን ሁለቱም አላዩም ።

እቅፍ አድርጋ ይዛው ብዙ ሰዓት ቆየች ። እሱም ጸጉሯን በእጁ እያረሰ «በጣም አትሸበሪ ፤ ማሚ። አሁን ሁሉም ነገር ተስተካክሏል።የክርስቶስ ያለህ ! እንዴት አድርጎ ነው የራበኝ እባካችሁ» አለ ድምፁን ስትሰማ፤ ነፍሱ ተመልሳ «ራበኝ» ሲል ዳነልኝ በቃ የኔ ነው ፣ማንም አይወስድብኝም ፤ ማንም አይቀማኝም ስትል አሰበች ። ደስ አላት ፤ ሳቀች ። «ዊክን እንጠይቀውና ይሁን ካለ በዓለም ላይ ካሉት ቁርሶች ሁሉ የላቀውንና የጣፈጠውን ቁርስ እናቀርብልሃለን » አለች ።
«ዊክ ቢፈልግ ገደል ይግባ ። እኔ በራብ መሞቴ ነው› አለ ማይክል ።
«ማይክል ምናልክ ! » አለች ። ግን ቁጣ ሊሆንላት አልቻለም አትችልምም ። ልትወደው ብቻ ነው እምትችለው ። ቁጣዋ ያሳደረበትን ስሜት ለማየት ፊቱን ስታጤን ልውጥ ሲል ታያት። ቅር ተሰኝቶ አይደለም አልነበረም ። ድንገት አንድ ነገር ያስታወሰ መሆኑ በግልፅ ታይቷታል። ለምን ሆስፒታል ውስጥ እንዳለ የገባው መሆኑ ገብቷታል። የመጀመሪያው አነሳሱ ሌላ ነበር ። በልጅነቱ ቶንሲል አሞት ሰንብቶ ከእንቅልፉ ሲነቃ እንደተሻለው ሲገነዘብ የሚሰማው አይነት ስሜት ነበር ። አይስ ከሬምና እናቱን ብቻ የፈለገው ለዚያ ነበር ። አሁን ግን ፊቱ ላይ ብዙ ነገር አነበበች ። ተነስቶ ሊቀመጥ ሞከረ። ምን እንደሚፈልግ ግራ ገባው እንጂ የሆነ ነገር ሊጠይቅ ፈልጐ ነበር፡፡ ከፊቱ አንድ ነገር ለመረዳት የፈለገ ይመስላል ። ትኩር ብሎ አያት። እስዋም አየችው። እጁን ጭብጥ አድርጋ ይዛ
«የኔ ውድ በቃ ፣፤ ቻለው» አለችው።
«እማዬ . . . ያንለት ሌለት . . ሌሎቹስ! አሁን ትዝ አለኝ» አለ ።
«ቤን ወደ ቦስተን ተወስዷል። ተገጫጭቷል ። ቢሆንም ደህና ነው። ካንተ ይሻላል» አለችው። ይህን ብላ በረጂሙ ተነፈሰች ፤ በጣም ማዘኗን ለመግለፅ ። እና እጁን ጥብቅ አድርጋ ያዘችው ። ቀጥሎ የሚመጣውን ጥያቄ አስቀድማ አውቃዋለች ።መልሱን አስቀድማ ስላዘጋጀች አልተጨነቀችም ።
«ናንሲስ ? » አለ ።«ናንሲ የት አለች ማሚ !?»
ፊታ መልሱን ነገረው ።እንባው ዱብ ዱብ አለ። አጠገቡ ተቀምጣ እጁን ቀስ ብላ እያሻሸች ፤
«በጣም ተጎድታ ነበር ስለዚህ አልተቻለም ። ሕይወቷን ማትረፍ አልተቻለም» አለች ። ቀጥላም… «ሀኪሞች ያልሞከሩት አልነበረም ። አልቻሉም » አለችና ንግግሯን አቋረጠች ። «ዛሬ ጠዋት አረፈች » አለችው ቀጥላ ።
«አየሻት? ሄደሽ አየሻት ?» አለ ፊቷን ትኩር ብሎ ስትዋሽ ውሸቷን ለማንበብ የሚሞክር መስሎ ።
«ትናንት ሌሊት. . . ለጥቂት ጊዜ... አጠገቧ ሄጄ ቁጭ ብዬ ነበር ። »
«ምንው አምላኬ ! ምነው … ናንሲ!ወይኔ ! የኔ ናንሲ» አለ ። ትራሱ ሳይ ተደፍቶ እንደልጅ አለቀሰ ። ማሪዮን ከጀርባው ላይ እጅዋን ጣል አድርጋ ተወችው ። ስሟን እየደጋገመ እያነሳ አለቀሰ ። እስኪደክመውና ድምጹ ተዘግቶ ማልቀስ እስኪ ሳነው። ቀና ብሎ እናቱን አያት ። በዚህ ጊዜም ከዚህ በፊት አይታው የማታውቀው አዲስ ስሜት እፊቱ ላይ አየች ። የናንሲን ስም እየደጋገመ ሲጠራና ሲያለቅስላት ልክ ከውስጡ አንድ ነገር የጠፋ ያህል ነበር ያን ነገር አየችው ። ከውስጡ አንድ ነገር ጐድሎ የእሱ የአካል ክፍል ተነጥሎ እንደሞተ ታያት....

ይቀጥላል......

ሀሳብ አስተያየታችሁን
@Tsiyon_awit
አድርሱኝ

ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@itsmetsiyearsemalj
@itsmetsiyearsemalj