Get Mystery Box with random crypto!

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiolawtips — Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ L
ርዕሶች ከሰርጥ:
نون
Immigration
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiolawtips — Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ
ርዕሶች ከሰርጥ:
نون
Immigration
የሰርጥ አድራሻ: @ethiolawtips
ምድቦች: ብድር, ግብሮች እና ህጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.28K
የሰርጥ መግለጫ

@lawyerhenoktaye (LL.B LL.M) 0953758395 ☎️
Youtube👇
https://youtu.be/5cnK4gX2Mrg
Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@lawyer_henok.t?_t=8iQ7AEnkz4v&_r=1
Facebook 👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100071372553654&mibextid=ZbWKwL

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-29 09:24:13 መጥሪያ አደራረስ ሥነ -ሥርዓት እና ውጤቱ

በፍትሐብሕር ጉዳይ ተከሣሽ ለሆነ ወገን ከፍ/ቤት የሚላከውን መጥሪያ ለተከሳሹ ሊደርስ የሚችልበትን የተሻለ አማራጭ መንገድ በመለየት ሊላክ ይገባል፡፡ የመኖሪያ አድራሻው በግልፅ ለሚታወቅ ተከሳሽ ፍ/ቤቱ የሚልከውን መጥሪያ በፍ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ብቻ እንዲለጠፍ በማድረግ ተከሳሹ አልቀረበም በሚል በሌለበት ጉዳዩ እዲታይ የሚሰጥ ውሣኔ ተገቢነት የለውም፡፡ በዚህ መንገድ በአግባቡ መጥሪያ እንዲደርሰው ያልተደረገ ተከሳሽ በሌለበት ታይቶ የተሰጠበት ውሣኔ እንዲነሣለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተገቢነት ያለው ነው፡፡ ተከሳሽን በአግባቡ መጥራት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕጉ ከተቀመጡት የመስማት መብት ከሚረጋገጥባቸው መርሆዎች አንደ ነው፡፡ ይህን መርህ ባለመጠበቅ የሚሰጠው ትዕዛዝ ወይም ውሳኔ በሕጉ አግባብ እንደተሰጠ አይቆጠርም፡፡ በመሆኑም ክሱ የቀረበለት ፍ/ቤት ወደጉዳዩ ሥረ-ነገር ገብቶ ተከሣሹን ባለዕዳ የሚያደርግ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፉት ተከሳሹን በአግባቡ ስለመጠራቱ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 105(1), 78. በሌላ በኩል ደግሞ ለተከሳሽ የተላከው መጥሪያ በጋዜጣ ጥሪ ሊደረግ የሚገባው ሌሎች አግባብነት ያላቸው የመጥሪያ አላላክ መንገዶች ቅደም ተከተላቸውን በጠበቀ መልኩ ከተከናወኑ በኋላ ነው፡፡ መጥሪያ በአግባቡ ደርሷል ለማለት የሚላክለት ሰው ስም በተሟላ ሁኔታ ተገልጾ መላክ ያለበት በአድራሻው መላክ አለበት፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 94-110, 78, 70/ሀ/
ለአንድ የመንግስት ተቋም የተላከ መጥሪያ መጥሪያው በአግባቡ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ካልደረሰ በስተቀር መጥሪያው ለተቋሙ መዝገብ ቤት ገቢ በመሆኑ ብቻ መጥሪያው እንደደረሠ ተቆጥሮ ክርክሩ ተቋሙ በሌለበት ሊታይ አይገበም፡፡ የመጥሪያ አሰጣጥ ዘዴና ቅደም ተከተል እንዲሁም መጥሪያው ለማን እንደሚሰጥ የሚመለከተው የፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ክፍል ዓይነተኛ ዓላማ ከሆኑት መካከል አንዱ ተከራካሪ ወገኖችን እኩል የመከራከር መብት እንዲኖራቸው በማድረግ ጉዳዩን ፍትሓዊ በሆነ አኳኋን ለመወሰን ማስቻል መሆኑን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ፍርድ ቤቱ መጥሪያ የሚደርስበትን ተገቢ መንገድና ለማን መድረስ እንዳለበት ማረጋገጥ ይገባዋል፡፡ መጥሪያ በተገቢው መንገድ ደርሶት ተከራካሪ ወገን ካልቀረበ ወይም መጥሪያን አልቀበልም ካለ ፍርድ ቤቱ ሊከተለው የሚገባው ስርዓትም በሕጉ በግልጽ ተመልክቷል፡፡ ከእነዚህም ድንጋጌዎች መካከል አንደ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 70(ሀ)፣ 103፣ 104፣ 105፣ 106 እና 107 ስር የተመለከተው ሲሆን በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት ተከሳሽ በላለበት ክርክሩ ታይቶ ውሳኔ ሊሰጥ የሚችለው መጥሪያው በአግባቡ የደረሰው መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም መጥሪያውን ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኑ ወይም ሊገኝ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም መጥሪያውን ለመቀበሌ ፈቃደኛ አለመሆኑ ወይም ሊገኝ ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ ድንጋጌዎቹ መጥሪያው በትክክል ያልደረሰው መሆኑ ከተረጋገጠ ጉዳዩ ተከሳሽ በሌለበት እንዲታይ የማይታዘዝ ስለመሆኑ ያስገነዝባል፡፡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 70(ሀ) ድንጋጌ ስር ላይ ‛መጥሪያው በትክክል መድረሱ“ የሚለው ሐረግ መኖሩም የሚያሳየው ስለመጥሪያ አሰጣጥና አደራረስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 94 እስከ 110 ድረስ የተመለከቱት ሁኔታዎች በአግባቡ መሟላታቸውን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ አንድ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ ታይቶ ውሳኔ ከተሰጠውም በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 78 መሰረት መፍትሔ መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ ተመልክቷል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት መፍትሔ ሊጠየቅ የሚችለው አቤቱታ አቅራቢው በሚያቀርበው አቤቱታ ላይ የጥሪው ትዕዛዝ ‛በሚገባ ያልደረሰው“ መሆኑን በመጥቀስ ይህንኑ ማረጋገጥ ሲችል ነው፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ድንጋጌዎች መገንዘብ የሚቻለው አንድ ሰው የመከራከር መብቱን እንደተወው የሚቆጠረው መጥሪያው በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓትና ቅደም ተከተል መሰረት ደርሶት ክርክር ያለው መሆኑን እያወቀ ሳይቀርብ ሲቀር ብቻ መሆኑን ነው፡፡ ፍርድ ቤቱ በሕጉ የተዘረጋውን ስርዓት ተከትሎ አማራጭ የመጥሪያ አደራረስ ሥርዓት ከፈጸመ መጥሪያው ለተከሳሹ እንደደረሰ እንደሚቆጠርና በቂና ሕጋዊ ምክንያት ካለው ብቻ ወደ ክርክሩ እንድገባ የሚፈቀድ መሆኑን ከላይ የተጠቀሱት ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ ያስገነዝባል፡፡ ስለሆነም ማንኛውም ውሳኔ መሰጠት ያለበትም በሕጉ በተዘረጋው ሥርዓት መሰረት መጥሪያው መድረሱ በሚገባ የተረጋገጠና የተከሳሽ የመከራከር መብት የተጠበቀ መሆኑ ሲታወቅ ሊሆን ይገባል፡፡ የፍ/ሥ/ህ/ቁ 70/ሀ/፣78/2/፣96፣102
ከላይ በተመለከተው መሠረት ለተከሳሽ የተላከው መጥሪያ በአግባቡ መድረስ አለመድረሱ ሳይረጋገጥ ክርክሩ በሌለበት ይቀጥል በሚል ትዕዛዝ ተሰጥቶ ክርክሩ የቀጠለ እንደሆነ ክርክሩን ወደ ኋለ የሚመልስና ለአላስፈላጊ እንግልት የሚዳርግ ነው፡፡ ስለዚህ በሌለበት ክርክሩ ይቀጥል ለማለት መጥሪያው ለሚመለከታቸው ተከሳሾች መድረስ አለመድረሱን በአግባቡ ማጣራት ያስፈልጋል፡፡ መጥሪያ በአግባቡ ያልደረሰው ሰው ተከሳሽ በሌለበት የተሰጠው ውሳኔ እንድነሳለት የሚጠይቀው በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 78 መሠረት ሲሆን አንድ አንድ ጊዜ በስህተት ወይም ባለማወቅ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የውሳኔ መቃወሚያ የሚቀርብበት ጊዜም አለ፤ ይህ ደግሞ ተገቢነት ያለው አይደለም፡፡ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የውሳኔ መቃወሚያ የሚቀርበው ከጅምሩ በክርክሩ መግባት የነበረበት ግን በክርክሩ ውስጥ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት ያልተጠቀሰ፤ በተሰጠው ውሳኔም መብቱ/ጥቅሙ የተነከ ሰው ነው፡፡ በክርክር ወቅት መጥሪያ አልደረሰኝም ብሎ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358 መሠረት የውሳኔ መቃወሚያ የሥነ-ሥርዓት ህጉን የተከተለ አይደለም፡፡ የሰበር ውሳኔዎች ቅጽ 9 የመ/ቁ. 50022, ቅጽ 9 የመ/ቁ. 50376
t.me/ethiolawtips
498 views06:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 06:26:50 ዕለታዊ
--------------_
የከሳሾች እና የተከሳሾች መጣመር
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
በአንድ በኩል ከአንድ በላይ ከሳሾች በሌላ በኩል ደግሞ ከአንድ በላይ ተከሳሾች በአንድ ክርክር ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉበትን ሁኔታ ህጋችን ደንግጎ ይገኛል ።የክሶችን ከአንድ በላይ መሆን የሚመለከተው የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 35 ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት ከሳሾች ሁለት ወይንም ከዚህ በላይ ሆነው መቅረብ የሚችሉት ከሁለት ዓይነት ሁኔታዋች አንዱ የተሟላ እንደሆነ ነው።
አንደኛው ሁኔታ ለክሱ መነሻ የሆነው ሀብት ወይንም መብት የከሳሾቹ የጋራ መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሀብቱ ወይንም መብቱ በተናጠል የየራሳቸው ቢሆንም እንኳን በሚቀርበው ክስ ሊወሰን የሚችለው የህግና የሥረ ነገር ጭብጥ አንድ አይነት መሆኑ ነው።
ስለዚህም ሁለት ወይንም ከዚያ በላይ ከሳሾች በአንድ ክስ ውስጥ ተጣምረው ሲቀርቡ ከነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ቢያንስ አንደኛው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ የሚገባ ነው።
በአንድ ክስ ውሰጥ የተከሳሾችን መጣመር የሚመለከተው የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 36 ነው።በዚህ ህግ ድንጋጌ መሠረት በመርህ ደረጃ ሁለት ወይንም ከዚያ በላይ ተከሳሾች በአንድ ክስ ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉት አንድ ሁኔታ ተሟልቶ ሲገኝ ነው።
ይህም በንዑስ ቁጥር አንድ ስር እንደተገለፀው በሚቀርበው ክስ ሊወሰን የሚችለው የሕግና የስረ ነገር ጭብጥ አንድ አይነት መሆኑን የሚመለከተው ሁኔታ ነው።ይሁንና ድንጋጌው ንዑሳነ ቁጥሮች 2-5 ባሉት ሁኔታዎች ከላይ የተገለፀው ሁኔታ ባይሟላም ሁለትና ከዚያ በላይ ተከሳሾች ተጣምረው ክስ ሊቀርብባቸው የሚችል መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።



ኢትዮ ሕግ
ሊንኩን ይጫኑ ለበለጠ መረጃ
https://t.me/ethiolawtips

Join
ለሌሎች ያጋሩ
992 viewsedited  03:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-02 14:24:31 የደምዳሚ (ድምዳሜ) ማስረጃ /conclusive evidence/ 5 የሰበር ችሎት ትርጓሜዎች

1//// የተሟላና ሙሉ ዕምነት የሚጣልበት ማስረጃ

የልዩ አዋቂ /expert/ የሚደርስበት የመጨረሻ አስተያየት ከሚኖረው ሙያዊ ዕውቀት አድማስ፣ ከሚታገዝበት መሣሪያና ከመሳሰሉት ጋር የተሟላና ሙሉ ዕምነት የሚጣልበት ማስረጃ /conclusive evidence/ ሊሆን ስለማይችል በዓይን ምስክሮች የተነገረን ፍሬ ነገር ለማስተባበል የሚያበቃ አቅም አይኖረውም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 43453 ቅጽ 12

የትራፊክ ፖሊስ የአደጋ ፕላን ሪፖርት የባለሙያ ሙያዊ አስተያየትን በወረቀት ላይ ስዕላዊ በሆነ መንገድ የሚያስቀምጥ በባለሙያ የሚረጋገጥ ሰነድ በመሆኑ እንደ ማንኛውም የልዩ አዋቂ የምስክርነት ቃል በተገቢው መንገድ ሊመዘን የሚገባው የማስረጃ አይነት እንጅ ሁልጊዜ ድምዳሜ ማስረጃ (Conclusive Evidence) ያለመሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 92141 ቅጽ 17

2//// አሳሪ ማስረጃ

በአስተዳደር አካል የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤት ነው ተብሎ የምስክር ወረቀት መስጠት ማስረጃውን ደምዳሚ ወይም አሳሪ (Conclusive Evidence) የሚያደርገው አይደለም፡፡ ይልቁንም ይኸው ማስረጃ የተሰጠበት አግባብ በፍ/ህ/ህ/ቁ. 1195 ድንጋጌ ስር በተመለከቱት ሁኔታዎች መሰረት ስለመሆኑ ማስረዳት ከተቻለ በፍ/ህ/ቁ. 1195 ስር የተመለከተው ሕጋዊ ግምት ሊስተባበል የሚችል (rebuttable legal presumption) መሆኑን ከድንጋጌዎቹ ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዳይ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 64014 ቅጽ 13

3//// ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል ወሳኝ ማስረጃ

አንድ ለማይንቀሳቀስ ንብረት የተሰጠ የባለሃብትነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ባለሃብትነትን በተመለከተ የህግ ግምት የሚያሰጥ ቢሆንም በሌላ ተቃራኒ ማስረጃ ሊስተባበል፣ በተቃራኒው ከሚቀርቡት ማስረጃዎች ጋር ሊመዘን የሚችል እንጂ እንጅ ማስተባበያ ሊቀርብበት የማይችል ወሳኝ /conclusive evidence/ ያለመሆኑን መገንዘብ ይቻላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 67011 ቅጽ 13

4//// የመጨረሻ ማስረጃ

የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ማስረዳት ከተቻለ ፍ/ቤት ልጅ ነው ሲል የሕግ ግምት ሊወስድ የሚችል መሆኑን የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 157/1/ ያመለክታል፡፡ ከአንቀፁ መረዳት እንደሚቻለው የልጅነት ሁኔታ መኖሩን ማረጋገጥ የመጨረሻ ማስረጃ (conclusive evidence) ሳይሆን የሕግ ግምት ብቻ ነው፡፡ ግምቱም ቢሆን አስገዳጅነት ያለው የሕግ ግምት አይደለም፡፡ ግምቱን የሚቃወም ወገን ማስረጃ በማቅረብ ማፍረስ እንደሚችል ንዑስ አንቀፅ 2 ይደነግጋል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 42648 ቅጽ 10

5///// ክርክር ሊነሳበት የማይችል፣ ሙሉ እምነት ሊጣልበት የሚችል ማስረጃ

ልጅነት የሚረጋገጥበት ዋናው ማስረጃ የልደት ምስክር ወረቀት እንደሆነ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 154 ላይ ተመልክቷል፡፡ ይህ ማለት ግን የልደት ምስክር ወረቀት ክርክር ሊነሳበት የማይችል ሙሉ እምነት ሊጣልበት የሚችል /Conclusive/ ማስረጃ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 33440 ቅጽ 5

ለበለጠ ሕግነክ መረጃ በቴሌግራም ለማግኘት ሊንኩን ይጫኑ
https://t.me/ethiolawtips
1.0K views11:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 08:40:31 እነዚህ አራት መሠረታዊ የቼክ መገለጫዋች በቼኩ ላይ ከሌሉ ቼኩ ሕጋዊ አይደለምና ጥንቃቄ አድርጉ
################
1ኛ/ቼኩን ተቀብሎ ክፍያ እንዲፈፅም የታዘዘው የባንክ ቤት ስም በግልፅ በቼክ ላይ ሊኖር ይገባል።ይህም ባንክ በህግ የባንክ ቤትን ስራ ለማከናወን ስልጣን የተሰጠው ተቋም ብቻ መሆን ይኖርበታል።በኢትዮጽያ ከሚገኙ ባንኮች ተመሳስሎ የሚፃፋ የባንክ ቤት ስሞች ስለሚኖሩ ቼኩ ላይ የተፃፈው ባንክ በኢትዮጵያ እውቅና ያለውና ሕጋዊ ፈቃድ አውጥቶ በስራ ላይ የሚገኝ ባንክ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።በህጋዊ መልኩ ታትመው ከወጡት ጋር ተመሳስለው የሚሰሩ ቼክ መሳይ ሃሰተኛ ሰነዶች እየበዙ በመምጣታቸው ይህን በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል።በንግድ ሕጉ በግልፅ እንደተደነገገው ሕጋዊ እውቅና ካለው ባንክ ቼኩ ወጪ እስካልተደረገ ለክፍያ ወደ ባንክ ቢቀርብም ገንዘብ ክፍያ ተፈፃሚ አይሆንም።

2ኛ.ለቼክ አውጪው ሊከፈለው የሚገባውን የገንዘብ መጠን በግልፅ ሊፃፍበት ይገባል። ይህም ሲባል ገንዘቡን ወጪ ለማድረግ ሌሎች መሟላት የሚገባቸውን ቅድመሁኔታዋች ያላመላከተ መሆን ይጠበቅበታል።አንዳንዶች ቼኩን ሲሰጡ ቼኩ ላይ የሚገልፁት ሌሎች ፅሁፎች ቼኩ ተቀባይነት እንዳይኖረው ያደርጋሉ።ለአብነት ያህል ይህ እስኪደረግ ድረስ ክፍያ ተፈፃሚ እንዳይሆን የሚሉ ክልከላዋች እና ሌሎች መሠል ፅሁፎች የቼኩን ሕጋዊነት የሚያሳጡ ስለሚሆኑ በቼኩ ላይ ከባንክ ወጪ የሚደረገው የገንዘብ መጠን ብቻ የተጠቀሰበት ብቻ እንጂ ሊሆን የሚገባው ከዚህ በተጨማሪ እንደቅድመሁኔታ ገንዘቡን ወጪ ለማድረግ የሚቀመጡ መስፈርቶች ቼኩ ዋጋ እንዲያጣ የሚያደርጉ ስለሆኑ በቼኩ ላይ የሚገለፁ ፅሁፎችን በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል ።

3=ቼኩ የወጣበት ቦታ እና ጊዜ በቼኩ ላይ የተፃፈበት መሆን አለበት ።ቼኩ የወጣበትን ቦታናጊዜ የማይገልፅ ከሆነ ህጋዊ ቼክ አይደለም።
4/ በቼኩ ላይ የተገለፀው ገንዘብ ከመቼ ጀምሮ ወጪ መደረግ እንደሚችል ቀኑን ወሩን እና አመተምህረቱን የተገለፀበት እንዲሁም ገንዘቡ የሚከፈልበትን የባንክ ቤት ስም ወይም ቦታ የሚገልፅ መሆን አለበት።ይህን ያላሟላ ቼክ ህጋዊ ያልሆነ ሀሰተኛ ቼክ ሲሆን
ሀሰተኛ ቼክ ማለት ቼክን ለማተም ስልጣን ባለዉ ባንክ ቤት ታትሞ ያልተሰጠ ወይም ታትሞ ከተሰጠዉ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ቼክ መሳይ ሰነድ ነው።

የወንጀል ተጠያቂነት
----------------------------
ማንም ሰዉ ይህንን ሀሰተኛ ቼክ የሰራ ፣ የተገለገለ ወይም ህጋዊ አስመስሎ ለሶስተኛ ወገን ያስተላለፈ እንደሆነ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ
አንቀፅ 375 ና በተከታዮቹ አንቀፃች እንዲሁም በተደራቢነት በወ.ህ.ቁ 692 መሰረት
በማታለል ወንጀል ተጠያቂ ይሆናል።
Lawyer.Henok Taye
Join
Telegram t.me/ethiolawtips
355 views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 15:55:48
ሰ/መ/ቁጥር - 219887 ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
አንድ ሰው ሁለት ሚስቶችን ያገባ እንደሆነ እና ጋብቻው በሞት ወይም በሌላ ህጋዊ ምክንያት የፈረሰ እንደሆነ እና ከሁለቱ ሚስቶች አንደኛዋ ንብረቶቹን በማፍራት ሂደት የተለየ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑን ያረጋገጠች እንደሆነ ከተፈራው ንብረት ግማሽ ድርሻ የሚገባት ሲሆን፣ የሌላኛዋ ተጋቢ ከባል ጋር ግማሹን ትካፈላለች።

በእርግጥ ሟች ሁለት ሚስቶች ኖረውት የሞተ እንደሆነ ሁለቱ ሚስቶች የንብረቱን ድርሻ ግማሹን ለሁለት ሊካፈሉ እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅሊይ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁጥር 24625 ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በሰ/መ/ቁጥር 45548 ላይ (ቅጽ 13 ላይ እንደታተመው) አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ያሉት እንደሆነ ንብረቶቹን በማፍራት ረገድ ከሚስቶቹ አንደኛዋ ሚስት ከሌላኛዋ የተሻለ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ባደረገችው አስተዋጽኦ ልክ ልትካፈል ትችላለች የሚል ሃሳብ መነሻ በማድረግ ባል ንብረቱን በሚያፈራበት ጊዜ ከእርሱ ጋር በትዳር የነበረች ሚስት ንብረቱን በማፍራት ረገድ በቀጥታ አስተዋጽኦ እንዳደረገች ግምት ተወስዶ ከንብረቱ ግማሹን ድርሻ የማግኘት መብት እንዳላት እና በአንፃሩ በቀጥታ አስተዋጽኦ ያላደረገች ሚስት ከባል ድርሻ ግማሹን የማግኘት መብት ብቻ ያላት ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ በሰ/መ/ቁጥር 50489 (ቅጽ 11 እንደታተመው) ጨምሮ በሌልች በርካታ መዛግብት ላይም ይህንኑ የሚያጠናክር ውሳኔ ሰጥቷል።
@habeshaadvocates

t.me/ethiolawtips
1.1K views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 10:01:55
በውል አዋዋይ ፊት የተደረገ ኑዛዜ መነበብ አስፈላጊነት
ሰ/መ/ቁ. 210987 መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም
ኑዛዜ ውልን ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ ሰው ፊት ቢደረግም ስለ መነበቡ በኑዛዜው ላይ ካልተገለጸ ወይም ስለ መነበቡ አመላካች ቃሌ ወይም ሐረግ ከሌለ ህጋዊ ውጤት የለውም።
ኑዛዜ ውልን ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ ሰዉ ሥራዉን በሚያካሄድበት ክፍል ዉስጥ መደረጉ ኑዛዜዉ በተናዛዡና በምስክሮች ፊት መነበብና ይህም ስለመፈጸሙ በኑዛዜዉ ላይ መገለጽ እንዳለበት በአስገዳጅነት የተደነገገዉን ሊሟላ እንደሚገባዉ እንጂ የኑዛዜዉ መነበብ ጉዳይ ቀሪ የሚያደርገዉ አይሆንም፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 17429 (ቅጽ 2) ባሳለፈዉ አስገዳጅ ውሳኔ በኑዛዜዉ ሰነድ ላይ ምስክሮች ኑዛዜዉ ሲደረግ ሰምተናል፣ አይተናል የሚል ሐረግ ከተቀመጠ ኑዛዜዉ እንደተነበበ የሚያመለክት በመሆኑ፣ ኑዛዜዉ እንደተነበበ የሚቆጠር ነዉ በማለት የወሰነ ሲሆን፣ እንዲሁም በሰ/መ/ቁ. 70057 (ቅጽ 13) ላይ ባሳለፈዉ አስገዳጅ ዉሳኔ ኑዛዜዉ ላይ እንደተነበበ ካልገለጸ አልያም ኑዛዜዉ እንደተነበበ አመላካች ቃል ካልተቀመጠ ኑዛዜዉ ፈራሽ መሆኑን መወሰኑን ያመለክታል፡፡
@habeshaadvocates
t.me/ethiolawtips
780 views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 19:21:12
ቼክ ተከፋይ (payee) የሆነ ሰው ቼኩን ያገኘበትን ውል የማስረዳት ሆነ በውሉ መሰረት ክፍያ እንዳልተፈጸመለት የማስረዳት ግዴታ የለበትም።
ይልቁንስ ለቼኩ መውጣት ምክንያት ነው የሚለዉን የግል ግንኙነትን በመከላከያነት በማንሳት ክፍያ ለመክፈል እንደማይገደድ የሚከራከር የቼኩ አውጪ (drawer) በቼኩ ክፍያ የማይፈጽምበት ህጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ በቀዳሚነት የማስረዳት ሸክም (ግዴታ) አለበት።
ከዚህ አኳያ ፍርድ ቤት በቀዳሚነት መመርመር የሚገባዉ ጉዳይ የቼኩ አውጪ ለቼኩ መውጣት ምክንያት ነዉ ያለውንና ክፍያ የማይፈጸምበት ምክንያት መኖር አለመኖሩን እና በተገቢው ማስረጃ ማስረዳት መቻል አለመቻሉን መለየት ነዉ።
@habeshaadvocatesllp

t.me/ethiolawtips
966 views16:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 10:06:42 በፍርድ የማይዳኝ ጉዳይ /Justiciability/---በሰበር ችሎት

ፍቺ--ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ በሕግ ለሌላ አካል የተሰጠ

ሰ/መ/ቁ. 51790 ቅጽ 12፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁ. 587/2000 አንቀጽ 19/1/ ለ፣ የፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁ. 515/1999፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሠራተኞች አስተዳደር ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ. 155/2000 አንቀጽ 37

ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ. ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1/ ድንጋጌ በግልጽ የሚያሳየው ጉዳይ ነው፡፡ ከዚሁ የሕገ መንግስት ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ፍርድ ቤቶች አንድን ጉዳይ (አቤቱታ) ተቀብለው ውሳኔ መስጠት የሚችሉት ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ በሕግ ለሌላ አካል ያልተሰጠ ጉዳይ በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ መሆኑን ነው፡፡ በሕግ ተለይተው በአስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲቋጩ በተባሉ ጉዳዮች ላይ መደበኛ ፍርድ ቤት የመዳኘት የስረ ነገር ስልጣን ስለሌለው በሕጉ መሰረት ለአንድ አስተዳደር አካል ቀርቦ አስተዳደራዊ ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ ወይም ለአስተዳደር መቅረብ የሚገባውን ጉዳይ ፍርድ ቤት ሊያስተናግደውም ሆነ አከራክሮ ውሳኔ ሊሰጥበት አይችልም፡፡ ለአንዳንድ የመንግስት አካላት በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የመወሰን ስልጣን የሚሰጡት ሕጎች መጠበቅና መከበር ያለባቸው ሲሆን የዳኝነት አካል ስልጣንም በሕግ የተወሰነ ስለሆነ ሕግ የመተርጎም ስራው በሕጉ በተመለከተው አድማስ የሚመራ ይሆናል፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 4 ድንጋጌ የሚያሳየውም ፍርድ ቤቶች በሌላ ሕግ በግልጽ በታገዱ ጉዳዮች ላይ አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የሌላቸው መሆኑን ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 54697 ቅጽ 12፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 4

አንድ ጉዳይ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል ነው የሚባለው የክርክሩ መሠረታዊ ባህሪ በፍርድ ለመጨረስ አመች የሆነ ሲሆንና ተከራካሪዎቹ የሚከራከሩበት ጉዳይ ንድፈ ሃሳባዊ ወይም ምናባዊ የፈጠራ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ሣይሆን በነባራዊ ዕውነታና ተጨባጭ በሆነ ችግር ወይም ክስተት መሠረት ያደረገ የመብት ወይም የሃላፊነት ጥያቄ ሲሆን እንደሆነ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 42150 ቅጽ 12፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ ዓለም አቀፍ የሲቨልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ስምምነት አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀፅ 1፣ የአፍሪካ የሰዎችና የህዝቦች መብት ቻርተር አንቀጽ 7
(የአንድ ዳኛ የተለየ ሓሳብ)

ግንባታ በጊዜው አለመጠናቀቁን ወይም የገንዘብ አቅም ማነስን አሊያም በሌላ ምክንያት አስተዳደሩ በሚወስዳቸው የኪራይ (lease) ይዞታ ማቋረጥ እርምጃዎች ላይ ባለይዞታው ቅሬታ ሲያድርበት ጉዳዩን ለማየት በሕግ በግልጽ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ሌላ አካል እስከሌለ ድረስ ጉዳዩ በፍርድ ሊወስን የሚገባው ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 80202 ቅጽ 15

የንብረት ባለሀብትነት መብት ከአንዱ ወገን ወደ ሌላው እንዴት መተላለፍ እንዳለበት በህጉ የተመለከተውን ደንብና ሥርዓት ሳይከተል ስለሆነ የንብረቱ ባለሀብት ስለመሆኑ የህግ ግምት መውሰጃ የሆነው የባለቤትነት ምስክር ወረቀት ቀሪ ነው፤ ሊሰረዝ ይገባል በማለት የሚቀርብ ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1195፣ 1196 እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33/2/ እና 231/1/ሀ/ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት በፍ/ቤት ሊረጋገጥ የሚችል የዳኝነት ጥያቄ እንጂ ጉዳዩ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል ጉዳይ አይደለም ለማለት የሚያበቃ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 75414 ቅጽ 14፣ ፍ/ህ/ቁ 1195፣ 1196፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 33(2)፣ 231(1) ሀ

የቀበሌ ቤት የተከራይነት መብት ተከራይ ሲሞት ለወራሾቹ ወይም ለቤተሰቦቹ የሚተላለፍ መሆን ያለመሆኑ በፍ/ብ/ሕጉ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት የኪራይ ውል የተመለከቱትን ድንጋጌዎች፣ የቀበሌ ቤትን የኪራይ መብትና ግዴታ ለመግዛት በሚመለከተው አካል በወጡት ደንብና መመሪያዎች አንጻር ታይቶ በፍርድ ቤት ዳኝነት የሚሰጥበት እንጂ የቤቱ አስተዳዳሪ የሆነ ቀበሌ ለፈለገው ሰው የሚያከራየው ነው ተብሎ በፍርድ እንዳያልቅ የሚደረግ ጉዳይ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 97948 ቅጽ 17
@habeshaadvocatesllp

t.me/ethiolawtips
1.1K views07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 22:17:12 ማንኛውም የቀበሌ መኖሪያ ቤት የተከራየ ሰው የራሱ ቤት ከገነባ ወይም የጋራ ሕንጻ ቤት ከገዛ ወይም የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲን ቤት ካገኘ ወይም በሌላ በማናቸውም ምክንያት ቤቱን የለቀቁ ከሆነ ቤቱን ባለበት ሁኔታ ለአስተዳደሩ ማስረከብ ያለበት ስለመሆኑ፣ የ አ.አ.ከ.አስተዳደር ባወጣው የመንግስት ቤቶች አስተዳደር መመሪያ ቁ . 3/2007 አንቀ ጽ 42/ ሀ ሰመቁ 123056/20
t.me/ethiolawtips
1.5K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 21:59:22
ሰ/መ/ቁ 226490 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም
የወራሽነት ማስረጃ ከፍርድ ቤት የተሰጠው ሰው የመብት ጥያቄ ሲያቀርብ ሌላኛው ወራሽ የመውረስ መብት እንደሌለው ክርክር ለማቅረብ በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃውን ማሰረዝ አስፈላጊ አይደለም።
ስለሆነም የወራሽነት ማስረጃ የተሰጠው ሰው የውርስ ድርሻውን ለማግኘት ባቀረበው ክስ ላይ የሟች ልጅ አይደለም ብሎ ለመቃወም በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃው እንዲሰረዝ አቤቱታ አቅርቦ ማሰረዝ አይጠበቅበትም።

ወራሽነትን በማረጋግጥ የሚሰጥ የወራሽነት ማስረጃ በአመልካች ብቻ የቀረበውን የአንድ ወገን ማስረጃ በመቀበል የሚሰጥ ማስረጃ (Declaratory judgment) ለመክሰስ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑን አሳይቶ የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ ለማቅረብ በማስረጃነት የሚቀርብ፤ በማንኛውም ተዓማኒነት እና ክብደት ባለው ማስረጃ ሊስተባበል የሚችል ማስረጃ በመሆኑ ማስረጃው
በተሰጠበት መዝገብ ላይ መብት ወይንም ጥቅሜን ይነካል በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የፍርድ መቃወሚያ የሚቀርብበት አይደለም።
@habeshaadvocatesllp
t.me/ethiolawtips
1.1K views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ