Get Mystery Box with random crypto!

#የአዳዲስ_ረቂቅ_አዋጆች_ጉዳይ! * Abebayehu Geta Enaro መምህር ጠበቃ እና የሕግ አ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

#የአዳዲስ_ረቂቅ_አዋጆች_ጉዳይ!
*
Abe
bayehu Geta Enaro
መምህር ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ

....በቀደም የዛሬ 4 ቀን ገደማ ለ #Immigration ባለስልጣን ዳይሬክተር ከፍርድ ቤት ጋር ስልጣን ተጋርቶ ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የሚያደርግ እገዳ የማስተላለፍ ስልጣን የሚሰጤ አዋጅ ሊጸድቅ ሂደት ላይ መሆኑን እንደህግ ባለሙያ ሰምተን አጃኢብ ብለን ሳናባራ ፤ ዛሬ ደግሞ ከውጭ ሀገር በተላከው ገንዘብ ሀብት ንብረት አፍርቶ የተላከበትን ደረሰኝ ያላቀረበ ንብረቱ እንዲወረስ የማደነግግ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ ይላሉ።
ይብሱኑ የሚገርመው የአዋጁ ተፈፃሚነት ወደ ኋላ ተመልሶ እስከ 10 ዓመት መስራት መቻሉ ነው።
ህግ በተፈጥሮ መሠረታዊ የሆኑ መርሆችን ተከትሎ ሊወጣ ይገባል።
ከእነዚህ መርሆች አንድኛው #Non-Retrospective nature of the Law(ህግ ወደኋላ ተመልሶ የማይሰራበት) መርህ ይባላል።
ይህ መርህ የሚከተሉት ጥቅሞች አሉት
1. #ፍትሃዊነት እና ፍትህ፡ ግለሰቦች እና አካላት ሊዳኙ ወይም ሊቀጡ የሚችሉት በተግባራቸው ጊዜ በስራ ላይ በነበሩት ህጎች ላይ በመመስረት ብቻ ነው። ሲፈጸሙ ህጋዊ ለሆኑ ድርጊቶች ኢ-ፍትሃዊ ቅጣት ይከለክላል።

2. #ህጋዊ እርግጠኝነት እና መተንበይ ፡ ዜጎች እና የንግድ ድርጅቶች አሁን ያለውን ህግ አውቀው ጉዳያቸውን ማቀድ እና መምራት ይችላሉ፣ ይህም ድርጊታቸው የሚያስከትለውን ህጋዊ መዘዝ የሚገነዘቡበት የተረጋጋ አካባቢ ን ለመፍጠር ነው።

3. #በህጋዊ ስርአት መታመን ፡- ህጎች ወደ ኋላ ተመልሰው እንደማይለወጡ ማወቅ በህግ ስርዓቱ እና በመንግስት ላይ እምነት እንዲጥል ያደርጋል። ሰዎች በሕግ ​​ማዕቀፉ መረጋጋት እና አስተማማኝነት ማመንን ያረጋግጣል።

4. #የመብቶች ጥበቃ ፡- ወደ ኋላ የሚመለሱ ሕጎች ቅጣቶችን በመጣል ወይም ከእውነታው በኋላ ህጋዊ ሁኔታዎችን በመቀየር የግለሰብ መብቶችን ሊጣሱ ይችላሉ። ወደ ኋላ የማይመለስ አካሄድ እነዚህን መብቶች ለመጠበቅ ይረዳል።

5. #ህግን አክብሮ መኖርን ያበረታታል፡- ሰዎች የሚዳኙት በነባር ህጎች ብቻ እንደሆነ ሲያውቁ የመከተል እድላቸው ሰፊ ነው። ይህ በህብረተሰብ ውስጥ ህግን አክባሪ ባህሪን ያበረታታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ረቂቅ አዋጁ በወንጀል የማስረዳት ሸክሙ ከባድ(ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በላይ) በመሆኑ ምንጩ የማይታወቅ ሀብት ከተገኘ ከወንጀሉ ባሻገር በፍትሐብሔር ሳይቀር ክስ መመስረት ይችላል ተብሏል።
ሌላው በነባር የሙስና ወንጀል ህጎች ላይ በምንጩ ያልታወቀ ሀብት የተጠረጠረ ሰው የማስረዳት ሸክሙ ያለበት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ አዋጅም በተመሳሳይ ሁኔታ የማስረዳት ሸክሙ ከዓቃቤ ህግ ወደ ግለሰቦች እንደሚዞር ይጠበቃል።
ይህ #ንብረት_የማስመለስ አዋጅ ተብሎ የቀረበው ካነገበበት ዓላማ ባሻገር በዜጎች መሰረታዊ የንብረት እና ሰብዓዊ መብቶች አንፃር በግሌ #ንብረት_የመንጠቅ አዋጅ የሚል ስያሜ ይመጥነዋል የሚል እምነት አለኝ።
#ኧረ_በህግ_አምላክ!