Get Mystery Box with random crypto!

በፍርድ የማይዳኝ ጉዳይ /Justiciability/---በሰበር ችሎት ፍቺ--ዳኝነት የተጠየቀበት ጉ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

በፍርድ የማይዳኝ ጉዳይ /Justiciability/---በሰበር ችሎት

ፍቺ--ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ በሕግ ለሌላ አካል የተሰጠ

ሰ/መ/ቁ. 51790 ቅጽ 12፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ቁ. 587/2000 አንቀጽ 19/1/ ለ፣ የፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁ. 515/1999፣ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሠራተኞች አስተዳደር ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁ. 155/2000 አንቀጽ 37

ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ስልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት ያለው ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ. ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 37/1/ ድንጋጌ በግልጽ የሚያሳየው ጉዳይ ነው፡፡ ከዚሁ የሕገ መንግስት ድንጋጌ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ፍርድ ቤቶች አንድን ጉዳይ (አቤቱታ) ተቀብለው ውሳኔ መስጠት የሚችሉት ዳኝነት የተጠየቀበት ጉዳይ በሕግ ለሌላ አካል ያልተሰጠ ጉዳይ በሚሆንበት ጊዜ እንደሆነ መሆኑን ነው፡፡ በሕግ ተለይተው በአስተዳደራዊ ውሳኔ እንዲቋጩ በተባሉ ጉዳዮች ላይ መደበኛ ፍርድ ቤት የመዳኘት የስረ ነገር ስልጣን ስለሌለው በሕጉ መሰረት ለአንድ አስተዳደር አካል ቀርቦ አስተዳደራዊ ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ ወይም ለአስተዳደር መቅረብ የሚገባውን ጉዳይ ፍርድ ቤት ሊያስተናግደውም ሆነ አከራክሮ ውሳኔ ሊሰጥበት አይችልም፡፡ ለአንዳንድ የመንግስት አካላት በተወሰኑ ጉዳዮች ላይ የመወሰን ስልጣን የሚሰጡት ሕጎች መጠበቅና መከበር ያለባቸው ሲሆን የዳኝነት አካል ስልጣንም በሕግ የተወሰነ ስለሆነ ሕግ የመተርጎም ስራው በሕጉ በተመለከተው አድማስ የሚመራ ይሆናል፡፡ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 4 ድንጋጌ የሚያሳየውም ፍርድ ቤቶች በሌላ ሕግ በግልጽ በታገዱ ጉዳዮች ላይ አከራክሮ የመወሰን ስልጣን የሌላቸው መሆኑን ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 54697 ቅጽ 12፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 4

አንድ ጉዳይ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል ነው የሚባለው የክርክሩ መሠረታዊ ባህሪ በፍርድ ለመጨረስ አመች የሆነ ሲሆንና ተከራካሪዎቹ የሚከራከሩበት ጉዳይ ንድፈ ሃሳባዊ ወይም ምናባዊ የፈጠራ ታሪክ ላይ የተመሠረተ ሣይሆን በነባራዊ ዕውነታና ተጨባጭ በሆነ ችግር ወይም ክስተት መሠረት ያደረገ የመብት ወይም የሃላፊነት ጥያቄ ሲሆን እንደሆነ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 42150 ቅጽ 12፣ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 37፣ ዓለም አቀፍ የሲቨልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን ስምምነት አንቀጽ 14 ንዑስ አንቀፅ 1፣ የአፍሪካ የሰዎችና የህዝቦች መብት ቻርተር አንቀጽ 7
(የአንድ ዳኛ የተለየ ሓሳብ)

ግንባታ በጊዜው አለመጠናቀቁን ወይም የገንዘብ አቅም ማነስን አሊያም በሌላ ምክንያት አስተዳደሩ በሚወስዳቸው የኪራይ (lease) ይዞታ ማቋረጥ እርምጃዎች ላይ ባለይዞታው ቅሬታ ሲያድርበት ጉዳዩን ለማየት በሕግ በግልጽ የዳኝነት ስልጣን የተሰጠው ሌላ አካል እስከሌለ ድረስ ጉዳዩ በፍርድ ሊወስን የሚገባው ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 80202 ቅጽ 15

የንብረት ባለሀብትነት መብት ከአንዱ ወገን ወደ ሌላው እንዴት መተላለፍ እንዳለበት በህጉ የተመለከተውን ደንብና ሥርዓት ሳይከተል ስለሆነ የንብረቱ ባለሀብት ስለመሆኑ የህግ ግምት መውሰጃ የሆነው የባለቤትነት ምስክር ወረቀት ቀሪ ነው፤ ሊሰረዝ ይገባል በማለት የሚቀርብ ጥያቄ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1195፣ 1196 እና በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 33/2/ እና 231/1/ሀ/ በተመለከቱት ድንጋጌዎች መሠረት በፍ/ቤት ሊረጋገጥ የሚችል የዳኝነት ጥያቄ እንጂ ጉዳዩ በፍርድ ሊያልቅ የሚችል ጉዳይ አይደለም ለማለት የሚያበቃ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 75414 ቅጽ 14፣ ፍ/ህ/ቁ 1195፣ 1196፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 33(2)፣ 231(1) ሀ

የቀበሌ ቤት የተከራይነት መብት ተከራይ ሲሞት ለወራሾቹ ወይም ለቤተሰቦቹ የሚተላለፍ መሆን ያለመሆኑ በፍ/ብ/ሕጉ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት የኪራይ ውል የተመለከቱትን ድንጋጌዎች፣ የቀበሌ ቤትን የኪራይ መብትና ግዴታ ለመግዛት በሚመለከተው አካል በወጡት ደንብና መመሪያዎች አንጻር ታይቶ በፍርድ ቤት ዳኝነት የሚሰጥበት እንጂ የቤቱ አስተዳዳሪ የሆነ ቀበሌ ለፈለገው ሰው የሚያከራየው ነው ተብሎ በፍርድ እንዳያልቅ የሚደረግ ጉዳይ አይደለም፡፡
ሰ/መ/ቁ. 97948 ቅጽ 17
@habeshaadvocatesllp

t.me/ethiolawtips