Get Mystery Box with random crypto!

ቼክ ተከፋይ (payee) የሆነ ሰው ቼኩን ያገኘበትን ውል የማስረዳት ሆነ በውሉ መሰረት ክፍያ እን | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ቼክ ተከፋይ (payee) የሆነ ሰው ቼኩን ያገኘበትን ውል የማስረዳት ሆነ በውሉ መሰረት ክፍያ እንዳልተፈጸመለት የማስረዳት ግዴታ የለበትም።
ይልቁንስ ለቼኩ መውጣት ምክንያት ነው የሚለዉን የግል ግንኙነትን በመከላከያነት በማንሳት ክፍያ ለመክፈል እንደማይገደድ የሚከራከር የቼኩ አውጪ (drawer) በቼኩ ክፍያ የማይፈጽምበት ህጋዊ ምክንያት ስለመኖሩ በቀዳሚነት የማስረዳት ሸክም (ግዴታ) አለበት።
ከዚህ አኳያ ፍርድ ቤት በቀዳሚነት መመርመር የሚገባዉ ጉዳይ የቼኩ አውጪ ለቼኩ መውጣት ምክንያት ነዉ ያለውንና ክፍያ የማይፈጸምበት ምክንያት መኖር አለመኖሩን እና በተገቢው ማስረጃ ማስረዳት መቻል አለመቻሉን መለየት ነዉ።
@habeshaadvocatesllp

t.me/ethiolawtips