Get Mystery Box with random crypto!

በውል አዋዋይ ፊት የተደረገ ኑዛዜ መነበብ አስፈላጊነት ሰ/መ/ቁ. 210987 መጋቢት 27 ቀን 20 | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

በውል አዋዋይ ፊት የተደረገ ኑዛዜ መነበብ አስፈላጊነት
ሰ/መ/ቁ. 210987 መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም
ኑዛዜ ውልን ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ ሰው ፊት ቢደረግም ስለ መነበቡ በኑዛዜው ላይ ካልተገለጸ ወይም ስለ መነበቡ አመላካች ቃሌ ወይም ሐረግ ከሌለ ህጋዊ ውጤት የለውም።
ኑዛዜ ውልን ለማዋዋል ስልጣን ባለዉ ሰዉ ሥራዉን በሚያካሄድበት ክፍል ዉስጥ መደረጉ ኑዛዜዉ በተናዛዡና በምስክሮች ፊት መነበብና ይህም ስለመፈጸሙ በኑዛዜዉ ላይ መገለጽ እንዳለበት በአስገዳጅነት የተደነገገዉን ሊሟላ እንደሚገባዉ እንጂ የኑዛዜዉ መነበብ ጉዳይ ቀሪ የሚያደርገዉ አይሆንም፡፡ የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ. 17429 (ቅጽ 2) ባሳለፈዉ አስገዳጅ ውሳኔ በኑዛዜዉ ሰነድ ላይ ምስክሮች ኑዛዜዉ ሲደረግ ሰምተናል፣ አይተናል የሚል ሐረግ ከተቀመጠ ኑዛዜዉ እንደተነበበ የሚያመለክት በመሆኑ፣ ኑዛዜዉ እንደተነበበ የሚቆጠር ነዉ በማለት የወሰነ ሲሆን፣ እንዲሁም በሰ/መ/ቁ. 70057 (ቅጽ 13) ላይ ባሳለፈዉ አስገዳጅ ዉሳኔ ኑዛዜዉ ላይ እንደተነበበ ካልገለጸ አልያም ኑዛዜዉ እንደተነበበ አመላካች ቃል ካልተቀመጠ ኑዛዜዉ ፈራሽ መሆኑን መወሰኑን ያመለክታል፡፡
@habeshaadvocates
t.me/ethiolawtips