Get Mystery Box with random crypto!

ሰ/መ/ቁጥር - 219887 ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም አንድ ሰው ሁለት ሚስቶችን ያገባ እንደሆ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ሰ/መ/ቁጥር - 219887 ታህሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም
አንድ ሰው ሁለት ሚስቶችን ያገባ እንደሆነ እና ጋብቻው በሞት ወይም በሌላ ህጋዊ ምክንያት የፈረሰ እንደሆነ እና ከሁለቱ ሚስቶች አንደኛዋ ንብረቶቹን በማፍራት ሂደት የተለየ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑን ያረጋገጠች እንደሆነ ከተፈራው ንብረት ግማሽ ድርሻ የሚገባት ሲሆን፣ የሌላኛዋ ተጋቢ ከባል ጋር ግማሹን ትካፈላለች።

በእርግጥ ሟች ሁለት ሚስቶች ኖረውት የሞተ እንደሆነ ሁለቱ ሚስቶች የንብረቱን ድርሻ ግማሹን ለሁለት ሊካፈሉ እንደሚገባ የፌዴራል ጠቅሊይ ፍርድ ቤት በሰ/መ/ቁጥር 24625 ላይ ውሳኔ ሰጥቷል። በሌላ በኩል በሰ/መ/ቁጥር 45548 ላይ (ቅጽ 13 ላይ እንደታተመው) አንድ ሰው ሁለት ሚስቶች ያሉት እንደሆነ ንብረቶቹን በማፍራት ረገድ ከሚስቶቹ አንደኛዋ ሚስት ከሌላኛዋ የተሻለ አስተዋጽኦ ያደረገች መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ ባደረገችው አስተዋጽኦ ልክ ልትካፈል ትችላለች የሚል ሃሳብ መነሻ በማድረግ ባል ንብረቱን በሚያፈራበት ጊዜ ከእርሱ ጋር በትዳር የነበረች ሚስት ንብረቱን በማፍራት ረገድ በቀጥታ አስተዋጽኦ እንዳደረገች ግምት ተወስዶ ከንብረቱ ግማሹን ድርሻ የማግኘት መብት እንዳላት እና በአንፃሩ በቀጥታ አስተዋጽኦ ያላደረገች ሚስት ከባል ድርሻ ግማሹን የማግኘት መብት ብቻ ያላት ስለመሆኑ አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡ በሰ/መ/ቁጥር 50489 (ቅጽ 11 እንደታተመው) ጨምሮ በሌልች በርካታ መዛግብት ላይም ይህንኑ የሚያጠናክር ውሳኔ ሰጥቷል።
@habeshaadvocates

t.me/ethiolawtips