Get Mystery Box with random crypto!

እነዚህ አራት መሠረታዊ የቼክ መገለጫዋች በቼኩ ላይ ከሌሉ ቼኩ ሕጋዊ አይደለምና ጥንቃቄ አድርጉ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

እነዚህ አራት መሠረታዊ የቼክ መገለጫዋች በቼኩ ላይ ከሌሉ ቼኩ ሕጋዊ አይደለምና ጥንቃቄ አድርጉ
################
1ኛ/ቼኩን ተቀብሎ ክፍያ እንዲፈፅም የታዘዘው የባንክ ቤት ስም በግልፅ በቼክ ላይ ሊኖር ይገባል።ይህም ባንክ በህግ የባንክ ቤትን ስራ ለማከናወን ስልጣን የተሰጠው ተቋም ብቻ መሆን ይኖርበታል።በኢትዮጽያ ከሚገኙ ባንኮች ተመሳስሎ የሚፃፋ የባንክ ቤት ስሞች ስለሚኖሩ ቼኩ ላይ የተፃፈው ባንክ በኢትዮጵያ እውቅና ያለውና ሕጋዊ ፈቃድ አውጥቶ በስራ ላይ የሚገኝ ባንክ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል።በህጋዊ መልኩ ታትመው ከወጡት ጋር ተመሳስለው የሚሰሩ ቼክ መሳይ ሃሰተኛ ሰነዶች እየበዙ በመምጣታቸው ይህን በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል።በንግድ ሕጉ በግልፅ እንደተደነገገው ሕጋዊ እውቅና ካለው ባንክ ቼኩ ወጪ እስካልተደረገ ለክፍያ ወደ ባንክ ቢቀርብም ገንዘብ ክፍያ ተፈፃሚ አይሆንም።

2ኛ.ለቼክ አውጪው ሊከፈለው የሚገባውን የገንዘብ መጠን በግልፅ ሊፃፍበት ይገባል። ይህም ሲባል ገንዘቡን ወጪ ለማድረግ ሌሎች መሟላት የሚገባቸውን ቅድመሁኔታዋች ያላመላከተ መሆን ይጠበቅበታል።አንዳንዶች ቼኩን ሲሰጡ ቼኩ ላይ የሚገልፁት ሌሎች ፅሁፎች ቼኩ ተቀባይነት እንዳይኖረው ያደርጋሉ።ለአብነት ያህል ይህ እስኪደረግ ድረስ ክፍያ ተፈፃሚ እንዳይሆን የሚሉ ክልከላዋች እና ሌሎች መሠል ፅሁፎች የቼኩን ሕጋዊነት የሚያሳጡ ስለሚሆኑ በቼኩ ላይ ከባንክ ወጪ የሚደረገው የገንዘብ መጠን ብቻ የተጠቀሰበት ብቻ እንጂ ሊሆን የሚገባው ከዚህ በተጨማሪ እንደቅድመሁኔታ ገንዘቡን ወጪ ለማድረግ የሚቀመጡ መስፈርቶች ቼኩ ዋጋ እንዲያጣ የሚያደርጉ ስለሆኑ በቼኩ ላይ የሚገለፁ ፅሁፎችን በጥንቃቄ መመልከት ያስፈልጋል ።

3=ቼኩ የወጣበት ቦታ እና ጊዜ በቼኩ ላይ የተፃፈበት መሆን አለበት ።ቼኩ የወጣበትን ቦታናጊዜ የማይገልፅ ከሆነ ህጋዊ ቼክ አይደለም።
4/ በቼኩ ላይ የተገለፀው ገንዘብ ከመቼ ጀምሮ ወጪ መደረግ እንደሚችል ቀኑን ወሩን እና አመተምህረቱን የተገለፀበት እንዲሁም ገንዘቡ የሚከፈልበትን የባንክ ቤት ስም ወይም ቦታ የሚገልፅ መሆን አለበት።ይህን ያላሟላ ቼክ ህጋዊ ያልሆነ ሀሰተኛ ቼክ ሲሆን
ሀሰተኛ ቼክ ማለት ቼክን ለማተም ስልጣን ባለዉ ባንክ ቤት ታትሞ ያልተሰጠ ወይም ታትሞ ከተሰጠዉ ጋር ተመሳስሎ የተሰራ ቼክ መሳይ ሰነድ ነው።

የወንጀል ተጠያቂነት
----------------------------
ማንም ሰዉ ይህንን ሀሰተኛ ቼክ የሰራ ፣ የተገለገለ ወይም ህጋዊ አስመስሎ ለሶስተኛ ወገን ያስተላለፈ እንደሆነ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ህግ
አንቀፅ 375 ና በተከታዮቹ አንቀፃች እንዲሁም በተደራቢነት በወ.ህ.ቁ 692 መሰረት
በማታለል ወንጀል ተጠያቂ ይሆናል።
Lawyer.Henok Taye
Join
Telegram t.me/ethiolawtips