Get Mystery Box with random crypto!

ዕለታዊ --------------_ የከሳሾች እና የተከሳሾች መጣመር ፣ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ዕለታዊ
--------------_
የከሳሾች እና የተከሳሾች መጣመር
፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
በአንድ በኩል ከአንድ በላይ ከሳሾች በሌላ በኩል ደግሞ ከአንድ በላይ ተከሳሾች በአንድ ክርክር ውስጥ ሊኖሩ የሚችሉበትን ሁኔታ ህጋችን ደንግጎ ይገኛል ።የክሶችን ከአንድ በላይ መሆን የሚመለከተው የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 35 ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሰረት ከሳሾች ሁለት ወይንም ከዚህ በላይ ሆነው መቅረብ የሚችሉት ከሁለት ዓይነት ሁኔታዋች አንዱ የተሟላ እንደሆነ ነው።
አንደኛው ሁኔታ ለክሱ መነሻ የሆነው ሀብት ወይንም መብት የከሳሾቹ የጋራ መሆኑ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሀብቱ ወይንም መብቱ በተናጠል የየራሳቸው ቢሆንም እንኳን በሚቀርበው ክስ ሊወሰን የሚችለው የህግና የሥረ ነገር ጭብጥ አንድ አይነት መሆኑ ነው።
ስለዚህም ሁለት ወይንም ከዚያ በላይ ከሳሾች በአንድ ክስ ውስጥ ተጣምረው ሲቀርቡ ከነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ቢያንስ አንደኛው የተሟላ መሆኑን ማረጋገጥ የሚገባ ነው።
በአንድ ክስ ውሰጥ የተከሳሾችን መጣመር የሚመለከተው የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 36 ነው።በዚህ ህግ ድንጋጌ መሠረት በመርህ ደረጃ ሁለት ወይንም ከዚያ በላይ ተከሳሾች በአንድ ክስ ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉት አንድ ሁኔታ ተሟልቶ ሲገኝ ነው።
ይህም በንዑስ ቁጥር አንድ ስር እንደተገለፀው በሚቀርበው ክስ ሊወሰን የሚችለው የሕግና የስረ ነገር ጭብጥ አንድ አይነት መሆኑን የሚመለከተው ሁኔታ ነው።ይሁንና ድንጋጌው ንዑሳነ ቁጥሮች 2-5 ባሉት ሁኔታዎች ከላይ የተገለፀው ሁኔታ ባይሟላም ሁለትና ከዚያ በላይ ተከሳሾች ተጣምረው ክስ ሊቀርብባቸው የሚችል መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።



ኢትዮ ሕግ
ሊንኩን ይጫኑ ለበለጠ መረጃ
https://t.me/ethiolawtips

Join
ለሌሎች ያጋሩ