Get Mystery Box with random crypto!

ሰ/መ/ቁ 226490 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም የወራሽነት ማስረጃ ከፍርድ ቤት የተሰጠው ሰው | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ሰ/መ/ቁ 226490 ጥቅምት 29 ቀን 2015 ዓ/ም
የወራሽነት ማስረጃ ከፍርድ ቤት የተሰጠው ሰው የመብት ጥያቄ ሲያቀርብ ሌላኛው ወራሽ የመውረስ መብት እንደሌለው ክርክር ለማቅረብ በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃውን ማሰረዝ አስፈላጊ አይደለም።
ስለሆነም የወራሽነት ማስረጃ የተሰጠው ሰው የውርስ ድርሻውን ለማግኘት ባቀረበው ክስ ላይ የሟች ልጅ አይደለም ብሎ ለመቃወም በቅድሚያ የወራሽነት ማስረጃው እንዲሰረዝ አቤቱታ አቅርቦ ማሰረዝ አይጠበቅበትም።

ወራሽነትን በማረጋግጥ የሚሰጥ የወራሽነት ማስረጃ በአመልካች ብቻ የቀረበውን የአንድ ወገን ማስረጃ በመቀበል የሚሰጥ ማስረጃ (Declaratory judgment) ለመክሰስ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑን አሳይቶ የድርሻ ክፍፍል ጥያቄ ለማቅረብ በማስረጃነት የሚቀርብ፤ በማንኛውም ተዓማኒነት እና ክብደት ባለው ማስረጃ ሊስተባበል የሚችል ማስረጃ በመሆኑ ማስረጃው
በተሰጠበት መዝገብ ላይ መብት ወይንም ጥቅሜን ይነካል በማለት በፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 358 መሠረት የፍርድ መቃወሚያ የሚቀርብበት አይደለም።
@habeshaadvocatesllp
t.me/ethiolawtips