Get Mystery Box with random crypto!

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiolawtips — Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ L
ርዕሶች ከሰርጥ:
نون
Immigration
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiolawtips — Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ
ርዕሶች ከሰርጥ:
نون
Immigration
የሰርጥ አድራሻ: @ethiolawtips
ምድቦች: ብድር, ግብሮች እና ህጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.28K
የሰርጥ መግለጫ

@lawyerhenoktaye (LL.B LL.M) 0953758395 ☎️
Youtube👇
https://youtu.be/5cnK4gX2Mrg
Tiktok👇 https://www.tiktok.com/@lawyer_henok.t?_t=8iQ7AEnkz4v&_r=1
Facebook 👇 https://www.facebook.com/profile.php?id=100071372553654&mibextid=ZbWKwL

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-06-04 19:55:34 አውራሽ/ሟች/ በህይወት እያለ ከይዞታ ቦታው ላይ ለሌላ ሠው ቤት እንዲሠራ ፈቅዶ ቢሰጠው ሟች በሚሞትበት ጊዜ በሟች ፈቃድ ቤት የሠራው የቤቱ ባለቤት እንደሚሆንና ከሌላው ቦታ ጋር ሆኖ የውርስ ክፍል የሚሆን ስላለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 826/2/ እና 1179/1/። ሰ/መ/ቁ-96628 ቅፅ-17.
በመሆኑም ፈቅዶ የሰጠው ሟች የቦታውን መብት ለባለ ሀብቱ እያስተላለፈ /እያጠ/ ስለሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ/826/2/ መሰረት አውራሻቸው የሌለው መብት ለወራሾች ሊተላለፍ የሚችልበት የሕግ መሠረት የለም፡፡በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1179(1) መሠረት ባለመብት የሚሆነው አውራሽ ሳይቃወመው በራሱ ወጭ በሠራቸው ቤቶችና ቤቶቹ በተሰሩበት ወይም ባረፉበት ቦታ ላይ ብቻ ይሆናል ።ይህ ቦታም የውርስ ሀብት ክፍል በሆኑ ንብረቶቹ ውስጥ ሊካተት አይችልም ።
t.me/ethiolawtips
Share #Join
1.9K viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 19:54:40 ጋብቻ በአንደኛው ተጋቢ ሞት ምክንያት በፈረሰ ጊዜ የጋራም ሆነ የግል ንብረት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠየቅ እንዳለበት በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677 መሠረት በቁ. 1845 ላይ የተቀመጠው #የ10_ዓመት ይርጋ ተፈፃሚ ስለመሆኑ፣
የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677፣ 1845 * ቅፅ-4 መ/ቁ 17937
ጋብቻ ልዩ ባህርይ ቢኖረውም ከሁለቱም ተጋቢዎች ስምምነት የሚመነጭ መብትና ግዴታም የሚጥል በመሆኑ በቤተሰብ ሕግ ግልጽ ድንጋጌ ሣይኖር ሲቀር በውል ሕግ መርሆች ወይም ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ማድረግ የውል ሕግ አንቀጽ 1677ም የሚፈቅደው ነው:: ይኸው ድንጋጌ «ግዱታዎቹ ከውል የተገኙ ባይሆኑም የዚህ አንቀፅ ደንቦች ይፈፀሙባቸዋል» በማለት ይደነግጋል፡፡ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተለየ የይርጋ ጊዜ ስለሌለው በዚህ ድንጋጌ መሠረት የውል ሕግ የይርጋ ድንጋጌዎች እንዲገዛ ማድረግ ተገቢ ነው:: የውል ሕግ ይርጋ አጠቃላይ ድንጋጌ በአንቀፅ 1845 እንደተገለፀው በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር 10 ዓመት ነው፡፡
t.me/ethiolawtips
#share Join
1.6K views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 19:31:40 የግልጽ ኑዛዜን መስፈርት በተመለከተ የተሰጡ ከ6 በላይ የሰበር አስገዳጅ ትርጉሞች የታረሙበት/የተለወጡበት ውሳኔ።

ከሞት በፊትም ሆነ ከሞት በኋላ ለሚፈጸም ስጦታ የፍትሃብሄር ህግ ቁጥር 2443 ተፈጻሚ ነው።
ይህም ማለት ፎርምን በተመለከተ በፍ/ሕ/ቁ881 የተመለከተውን የግልጽ ኑዛዜ ፎርማሊቲ ማሟላት አለበት
በሰነዶች ማረጋገጫ ወይም ውል አዋዋይ ፊት የተደረገ ኑዛዜ ወይም የስጦታ ውል የግድ በሰነዱ ላይ በምስክሮች እና በተናዛዙ ወይም በስጦታ ሰጪው ፊት ተነቧል በሚል መገለጽ አያስፈልገውም።

ተጨማሪ የሰበር ውሳኔ በቴሌግራም
https://t.me/ethiolatips
1.6K views16:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 18:51:57 በፅሁፍ ያልተደረግ የብድር ገንዘብ ውጤቱ

https://t.me/HenokTayeLawoffice
የገንዘብ ብድርን በተመለከት ለጠየቃችሁት የሕግ ምክር እነሆ
አሁን በሚደረግ ፈጣን ግብይትና የንግድ እንቅስቃሴ አብዛኛው ሰው የገንዘብ ልውውጥ በካሽ;በቼክ;በብድር መልክ ይገበያያል።በዚህ መሀል ሰዋች ባለን ቅርበት እና መተማመን አንዱ ለሌላው የገንዘብ ብድር ይሰጣል።ይሁንና ገንዘቡን የሚያበድርበት መንገድ በሕጉ በተቀመጠው ድንጋጌ መሠረት ካልሆነ ገንዘቡን የተበደረውን ሰው ለማስከፈል አዳጋች ይሆናል።ስለሆነም የትኛውም የገንዘብ ብድር ከ500ብር በላይ ከሆነ በፅሁፍ ሊሆንና የ ገንዘብ ብድር ውል ሊያሟላ በሚገባ የውል ፎርም ተዘጋጅቶ መፈራረም አስፈላጊ ነው።በተለያዩ ግላዊ ምክንያቶች የብድር ገንዘቡን በተወሰነ ጊዜው ውስጥ ተመላሽ እንደሚያደርግ ተናግሮ በቃሉ የማይገኝ ተበዳሪ አለና ከመተማመን በተጨማሪ ሌሎች ሕጋዊ አካሄዶችን መከተል ጠቃሚ ነው።

የገንዘብ ብድር ውል ማለት በአጭሩ ከፍ/ሀግ አንቀጽ 2471(1) ለይ ከተደነገገው ድንጋጌ መገንዘብ አንደሚቻለው ከተዋዋዮች አንዱ ወገን አበዳሪው ለሌላውን ተበዳሪ ሰው የተበደረውን ገንዘብ ለመመለስ ተገዳጅ በማድረግ ፡ገንዘቡን ለተበዳሪው ለመስጠት የሚገደድበት ውል ነው ማለት እንችላለን።

ከ500 የኢትዮጵያ ብር በላይ ለሆነ የብድር ውል ህጉ በጹሁፍ እንዲሆን ያስገድዳል ወይ?

በፍ/ህግ አንቀጽ 2472(1) በብድር የተሰጠው ገንዘብ 500 የኢትዮጵያ ብር በላይ በሚሆንበት ጊዜ የብድሩን ውል በጽሁፍ ወይም በፍርድ ቤት በሚደረግ የእምነት ቃል ወይም መሓላ ካልሆነ በቀር ለማስረዳት አይቻልም በሚል ተደንግጎዋል ። ድንጋጌ ከብድር ውጭ በሆነ ግንኙነት ከተከፈለ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ተፈጻሚነት የሌለው መሆኑን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 13 መ/ቁ 64397 እና ቅጽ 20 መ/ቁ 116961 ላይ ውሳኔ ተሰጥቷል።
በመሆኑም የብድር ውሉ ከ500 የኢትዮጵያ ብር በላይ በሚሆንበት ጊዜ የብድር ውል ስምምነቱ ስለመኖሩ በፍርድ ቤት የሚረጋገጠው በዋናነት የጽሁፍ ውሉን በማቅረብ ሲሆን ከዚህ ባለፈ ደግሞ በፍርድ ቤት በሚደረግ የእምነት ቃል ወይም መሓላ ብቻ ለማረጋገጥ እንደሚቻል ህጉ ያስረዳል።
when the loan amount is greater than Birr500 the existance of the agreement can be proofed in court of law by written evidence,a confession made in court or by outh taken in court.
ከ 500 የኢትዮጵያ ብር ብድር ውል ስምምነትን ለማስረዳት የሚቀርበው የጽሁፍ ውል ደግሞ ህጉ ያስቀመጠውን ፎርማሊት ያሟላ መሆን የሚገባው ሲሆን ። የጽሁፍ ውሉ በፍ/ህግ አንቀጽ 1727 በውሉ ግዴታ ያለባቸው ሰዎች ሁሉ መፈራረም ያለባቸው ይሆናል ከዚህም በተጨማሪ በብድር ውሉ ጽሁፍ ለይ በሁለት ምስክሮች ፊት ሊረጋገጥ የሚገባው ይሆናል። በሌላ በኩል ከዚህ በተለየ መልኩ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 5 መ/ቁ 31737 ለይ በፍ/ህግ አንቀጽ 2472 መሠረት በባንክ የተሰጠ የሃዋላ ወረቀት ብድርን ለማስረዳት እንደሚችል ውሳኔ ሰጦቶ እናግኛለን ።
ከላይ በፍ/ህግ አንቀጽ 2472 ለይ በተቀመጠው ድንጋጌ ከ500ብር በላይ የሚደረግ የብድር ውል ስምምነትን በተመለከተ በፍርድ ቤት ለማረጋገጥ በመሰረታዊነት የጽሁፍ ውል ሊቀረብ የሚገባ መሆኑን የሚያስቀምጥ እንጂ የብድር ውሉ ከጅምሩ በጽሁፍ ካልሆነ ተገቢነት ወይም ህጋዊነት የለውም( void contract) ነው ሊባል የሚችል አይደለም።የፍ/ህግ አንቀጽ 2472(1)(2) ከ500 ብር በላይ ለሚደረግ የብድር ውል ስምምነት የግድ ውሉ በጽሁፍ መሆን አለበት በሚል የተቀመጠ ሳይሆን ከ500 ብር በላይ ለሆኑ የብድር ውሎች በሰው ምስክር ወይም በግምት ለማስረዳት የማይቻል መሆኑን ነው።
the law requires written evidence to proof contract of loan in court of law when it is contested by the other party, it doesn't require a written contract for the formation of a valid contract of loan.
አንቀጽ 2472(2) ለይ እንደተጠቀሰው ለብድር ውል ማናቸውም ሌላ አይነት ማስረጃ በማቅረብ ለማስረዳት አይቻለም የሚል ሲሆን ድንጋጌው በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ባለው ግንኙነት ለይ ተፈጻሚነት የሌለው መሆኑን የፍ/ሀግ አንቀጽ 2473(1) ያስረዳል። በባንኮች ሌሎች አበዳሪ ተቋማት ደንበኞቻቸው ገንዘብ የተበደሩና የተበደሩትን ገንዘብ ያልከፈሉ መሆኑን ለማሰረዳት በተመሣሣይ ሁኔታ የባንክ ተበዳሪ ብድር ያልወሰደ ወይም የወሰደውን ብድር የከፈለ መሆኑን ለማስረዳት በሰው ምስክር ወይም በህሊና ግምት ለማስረዳት የሚቻል መሆኑን የፍ/ህግ አንቀጽ 2473(3) እና በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 10 መ/ቁ 29181 ላይ ከተሰጠው ውሳኔ መረዳት ይቻላል።ከዚህም በተጨማሪ ከ500 ብር በላይ ለተደረገ የብድር ውል ለማስረዳት በቀረበው የጽሁፍ ውል ለይ የተፈረመው ፊርማ የተካደ እንደሆነ ፊርማው የተፈረመው በተበዳሪው መሆኑን ለማስረዳት በብድር ውሉ ላይ የፈረሙትን የሰው ማስረጃዎች በማቅረብ ለማስረዳት እንደሚቻል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሰጥቶ እናግኛለን።
ለሌሎች እንዲደርስ Share ማድረግ አይርሱ።
henoktayelawoffice

የገንዘብ ብድር ውል ፎርም በቴሌግራም ያግኙ
https://t.me/ethiolawtips

ምንጭ
የፍትሐብሔር ህግ
የፌድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
1.7K viewsedited  15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 20:31:58 ሰበር መ/ቁ 220119 ጥቅምት 1 ቀን 2015ዓ.ም
የማይንቃሳቀስ ንብረት ገዥ ስመ ንብረቱ በሻጭ የተመዘገበና ከእዳና እገዳ ነጻ መሆኑን ከሚመለከተዉ አስተዳደር አካል በማረጋገጥ የተዋዋለ እንደሆነ አንድ ጠንቃቃ ሰዉ ማድረግ የሚጠበቅበት ጥንቃቄ እንዳደረገ ግምት ተወስዶ ሕጉ ጥበቃ ያደርግለታል፡፡
የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1553 እስከ 1646፤2878 እና 3052 ድንጋጌዎች የማይንቀሰቃስ ንብረት ምዝገባ አስፈላጊነትም የንብረት መብት ጥበቃ ለማረጋገጥ፣ የግብይት ዋስትና እና የ3ኛ ወገኖችን መብት ለማስከበር እንደሆነ የሚያሥገነዝቡ ናቸዉ፡፡ ስለዚህም የማይንቃሳቀስ ንብረት ላይ በዉል መብት ለማቋቋም የፈለገ ሰዉ እንደ አንድ ጠንቃቃ ገዥ ይህንኑ ስርዓት ተከትሎ ማለትም ስመ ንብረቱ በሻጭ ስም የተመዘገበና ንብረቱ ከእዳና እገዳ ነጻ መሆኑን የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት፡፡በዚህ ረገድ ተገቢ ጥንቃቄ ማድረጉ ከተረጋገጠ ዉሉ የሚፈርስበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም፡፡ (የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2881 ይመለከታል፡፡)
s-habeshaadvocatesllp

t.me/ethiolawtips
2.3K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 14:23:00
t.me/ethiolawtips
2.3K views11:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-03 14:22:54
ግሩም ውሳኔ
በሰባት ዳኞች ተለውጧል።
~~~````~~~
የሰበር መዝ/ቁ 191393
ሚያዚያ 30/2015
~~~
ካሁን በፊት በተለያዩ የሰበር ውሳኔዎች "ለውርስ ክርክር ተፈፃሚነት ያለው ሟች በሞተበትና ውርሱ በተከፈተበት ጊዜ ተፈፃሚነት የነበረው ህግ ሳይሆን ክርክሩ በቀረበ ጊዜ በስራ ላይ ባለው ህግ መሰረት ሊሆን ይገባል" በሚል የተሰጡ ውሳኔዎች በሰባት ዳኞች ተለውጦ ተፈፃሚ የሚሆነው ህግ ሟች በሞተበትና ውርሱ በተከፈተበት ጊዜ ተፈፃሚነት ያለው ህግ ሊሆን ይገባል ተብሏል።
#Join

t.me/ethiolawtips
4.8K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 08:43:25 ዳኝነትን የሚመለከቱ አባባሎች፣ ተረትና ምሳሌዎች፣
1) ዳኛ ቢያጋድል በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ፣
2) ዳኛ ለዳኛ ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል፣
3)ዳኛ ምን ያደላ ከተረታው ሊበላ፣
4)ዳኛ ሲመረምር ከራስ ይዞ እስከ እግር፣
5)ዳኛ ሲቆጣ ማር ይዞ ከደጁ፣
6)ዳኛ ሲገኝ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር፣
7)ዳኛ ስበር በእጅ ክበር፣
8)ዳኛ ቢንቁ የተያዘ እህል ይወቁ፣
9)ዳኛ አውጥቼ ዘንግ አቅንቼ፣
10)ዳኛ አይነቀፍ እሳት አይታቀፍ፣
11) ዳኛ ካዳላ ጭነት ቀላል፣
12) ዳኛ የወል ምሰሶ የማሃል፣
13) ዳኛ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት፣
14) ዳኛ የፈረደው ስለት የቀደደው፣
15) ዳኛ ያደላበት እሳት የበላበት፣
16)ዳኛ ያፈሰሱለት ፈረስ የከሰከሱለት፣
17) ዳኛ ይመረምራል ጣዝማ ይሰረስራል፣
18) ዳኛ ፍርድ አይከላ እህል ጎታ ይሞላ፣
19) ዳኛና በሬ ሀብታም ናቸው፣
20) ዳኛን ቢንቁ የተያዘ እህልን ይወቁ፣
21)ዳኞች ከመረመሩ ይናገራል ምድሩ ይገናል ነገሩ፣
ሌሎች ካሉ ጨምሩ
t.me/ethiolawtips
4.9K views05:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-28 08:42:14
የወንጀል ድርጊቱ ከምሽቱ 5፡00 ሰዓት ላይ የተፈፀመ ከሆነ በሌሊት የተፈጸመ ባለመሆኑ በወ/ህ/ቁ 84(1)(ሐ) መሰረት ቅጣት ማክበጃ ምክንያት ሊሆን አይገባም።
(ሰ/መ/ቁጥር 220926) ሚያዚያ 25 ቀን 2014ዓ/ም የተወሰነ።
ጥያቄ
1. ለመሆኑ ሌሊት ለማለት ስንት ሰዓት መሆን አለበት?
2. አንድ ወንጀል በቡድን ተፈፀመ የሚባለዉ መቼ ነው?
t.me/ethiolawtips
3.6K views05:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 09:28:08
ደመወዝ 39513
t.me/ethiolawtips
478 views06:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ