Get Mystery Box with random crypto!

ዳኝነትን የሚመለከቱ አባባሎች፣ ተረትና ምሳሌዎች፣ 1) ዳኛ ቢያጋድል በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ዳኝነትን የሚመለከቱ አባባሎች፣ ተረትና ምሳሌዎች፣
1) ዳኛ ቢያጋድል በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ፣
2) ዳኛ ለዳኛ ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል፣
3)ዳኛ ምን ያደላ ከተረታው ሊበላ፣
4)ዳኛ ሲመረምር ከራስ ይዞ እስከ እግር፣
5)ዳኛ ሲቆጣ ማር ይዞ ከደጁ፣
6)ዳኛ ሲገኝ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር፣
7)ዳኛ ስበር በእጅ ክበር፣
8)ዳኛ ቢንቁ የተያዘ እህል ይወቁ፣
9)ዳኛ አውጥቼ ዘንግ አቅንቼ፣
10)ዳኛ አይነቀፍ እሳት አይታቀፍ፣
11) ዳኛ ካዳላ ጭነት ቀላል፣
12) ዳኛ የወል ምሰሶ የማሃል፣
13) ዳኛ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት፣
14) ዳኛ የፈረደው ስለት የቀደደው፣
15) ዳኛ ያደላበት እሳት የበላበት፣
16)ዳኛ ያፈሰሱለት ፈረስ የከሰከሱለት፣
17) ዳኛ ይመረምራል ጣዝማ ይሰረስራል፣
18) ዳኛ ፍርድ አይከላ እህል ጎታ ይሞላ፣
19) ዳኛና በሬ ሀብታም ናቸው፣
20) ዳኛን ቢንቁ የተያዘ እህልን ይወቁ፣
21)ዳኞች ከመረመሩ ይናገራል ምድሩ ይገናል ነገሩ፣
ሌሎች ካሉ ጨምሩ
t.me/ethiolawtips