Get Mystery Box with random crypto!

ሰበር መ/ቁ 220119 ጥቅምት 1 ቀን 2015ዓ.ም የማይንቃሳቀስ ንብረት ገዥ ስመ ንብረቱ በሻጭ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ሰበር መ/ቁ 220119 ጥቅምት 1 ቀን 2015ዓ.ም
የማይንቃሳቀስ ንብረት ገዥ ስመ ንብረቱ በሻጭ የተመዘገበና ከእዳና እገዳ ነጻ መሆኑን ከሚመለከተዉ አስተዳደር አካል በማረጋገጥ የተዋዋለ እንደሆነ አንድ ጠንቃቃ ሰዉ ማድረግ የሚጠበቅበት ጥንቃቄ እንዳደረገ ግምት ተወስዶ ሕጉ ጥበቃ ያደርግለታል፡፡
የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 1553 እስከ 1646፤2878 እና 3052 ድንጋጌዎች የማይንቀሰቃስ ንብረት ምዝገባ አስፈላጊነትም የንብረት መብት ጥበቃ ለማረጋገጥ፣ የግብይት ዋስትና እና የ3ኛ ወገኖችን መብት ለማስከበር እንደሆነ የሚያሥገነዝቡ ናቸዉ፡፡ ስለዚህም የማይንቃሳቀስ ንብረት ላይ በዉል መብት ለማቋቋም የፈለገ ሰዉ እንደ አንድ ጠንቃቃ ገዥ ይህንኑ ስርዓት ተከትሎ ማለትም ስመ ንብረቱ በሻጭ ስም የተመዘገበና ንብረቱ ከእዳና እገዳ ነጻ መሆኑን የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት፡፡በዚህ ረገድ ተገቢ ጥንቃቄ ማድረጉ ከተረጋገጠ ዉሉ የሚፈርስበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም፡፡ (የፍ/ብ/ህግ ቁጥር 2881 ይመለከታል፡፡)
s-habeshaadvocatesllp

t.me/ethiolawtips