Get Mystery Box with random crypto!

በፅሁፍ ያልተደረግ የብድር ገንዘብ ውጤቱ https://t.me/HenokTayeLa | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

በፅሁፍ ያልተደረግ የብድር ገንዘብ ውጤቱ

https://t.me/HenokTayeLawoffice
የገንዘብ ብድርን በተመለከት ለጠየቃችሁት የሕግ ምክር እነሆ
አሁን በሚደረግ ፈጣን ግብይትና የንግድ እንቅስቃሴ አብዛኛው ሰው የገንዘብ ልውውጥ በካሽ;በቼክ;በብድር መልክ ይገበያያል።በዚህ መሀል ሰዋች ባለን ቅርበት እና መተማመን አንዱ ለሌላው የገንዘብ ብድር ይሰጣል።ይሁንና ገንዘቡን የሚያበድርበት መንገድ በሕጉ በተቀመጠው ድንጋጌ መሠረት ካልሆነ ገንዘቡን የተበደረውን ሰው ለማስከፈል አዳጋች ይሆናል።ስለሆነም የትኛውም የገንዘብ ብድር ከ500ብር በላይ ከሆነ በፅሁፍ ሊሆንና የ ገንዘብ ብድር ውል ሊያሟላ በሚገባ የውል ፎርም ተዘጋጅቶ መፈራረም አስፈላጊ ነው።በተለያዩ ግላዊ ምክንያቶች የብድር ገንዘቡን በተወሰነ ጊዜው ውስጥ ተመላሽ እንደሚያደርግ ተናግሮ በቃሉ የማይገኝ ተበዳሪ አለና ከመተማመን በተጨማሪ ሌሎች ሕጋዊ አካሄዶችን መከተል ጠቃሚ ነው።

የገንዘብ ብድር ውል ማለት በአጭሩ ከፍ/ሀግ አንቀጽ 2471(1) ለይ ከተደነገገው ድንጋጌ መገንዘብ አንደሚቻለው ከተዋዋዮች አንዱ ወገን አበዳሪው ለሌላውን ተበዳሪ ሰው የተበደረውን ገንዘብ ለመመለስ ተገዳጅ በማድረግ ፡ገንዘቡን ለተበዳሪው ለመስጠት የሚገደድበት ውል ነው ማለት እንችላለን።

ከ500 የኢትዮጵያ ብር በላይ ለሆነ የብድር ውል ህጉ በጹሁፍ እንዲሆን ያስገድዳል ወይ?

በፍ/ህግ አንቀጽ 2472(1) በብድር የተሰጠው ገንዘብ 500 የኢትዮጵያ ብር በላይ በሚሆንበት ጊዜ የብድሩን ውል በጽሁፍ ወይም በፍርድ ቤት በሚደረግ የእምነት ቃል ወይም መሓላ ካልሆነ በቀር ለማስረዳት አይቻልም በሚል ተደንግጎዋል ። ድንጋጌ ከብድር ውጭ በሆነ ግንኙነት ከተከፈለ ገንዘብ ጋር በተያያዘ ተፈጻሚነት የሌለው መሆኑን በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 13 መ/ቁ 64397 እና ቅጽ 20 መ/ቁ 116961 ላይ ውሳኔ ተሰጥቷል።
በመሆኑም የብድር ውሉ ከ500 የኢትዮጵያ ብር በላይ በሚሆንበት ጊዜ የብድር ውል ስምምነቱ ስለመኖሩ በፍርድ ቤት የሚረጋገጠው በዋናነት የጽሁፍ ውሉን በማቅረብ ሲሆን ከዚህ ባለፈ ደግሞ በፍርድ ቤት በሚደረግ የእምነት ቃል ወይም መሓላ ብቻ ለማረጋገጥ እንደሚቻል ህጉ ያስረዳል።
when the loan amount is greater than Birr500 the existance of the agreement can be proofed in court of law by written evidence,a confession made in court or by outh taken in court.
ከ 500 የኢትዮጵያ ብር ብድር ውል ስምምነትን ለማስረዳት የሚቀርበው የጽሁፍ ውል ደግሞ ህጉ ያስቀመጠውን ፎርማሊት ያሟላ መሆን የሚገባው ሲሆን ። የጽሁፍ ውሉ በፍ/ህግ አንቀጽ 1727 በውሉ ግዴታ ያለባቸው ሰዎች ሁሉ መፈራረም ያለባቸው ይሆናል ከዚህም በተጨማሪ በብድር ውሉ ጽሁፍ ለይ በሁለት ምስክሮች ፊት ሊረጋገጥ የሚገባው ይሆናል። በሌላ በኩል ከዚህ በተለየ መልኩ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 5 መ/ቁ 31737 ለይ በፍ/ህግ አንቀጽ 2472 መሠረት በባንክ የተሰጠ የሃዋላ ወረቀት ብድርን ለማስረዳት እንደሚችል ውሳኔ ሰጦቶ እናግኛለን ።
ከላይ በፍ/ህግ አንቀጽ 2472 ለይ በተቀመጠው ድንጋጌ ከ500ብር በላይ የሚደረግ የብድር ውል ስምምነትን በተመለከተ በፍርድ ቤት ለማረጋገጥ በመሰረታዊነት የጽሁፍ ውል ሊቀረብ የሚገባ መሆኑን የሚያስቀምጥ እንጂ የብድር ውሉ ከጅምሩ በጽሁፍ ካልሆነ ተገቢነት ወይም ህጋዊነት የለውም( void contract) ነው ሊባል የሚችል አይደለም።የፍ/ህግ አንቀጽ 2472(1)(2) ከ500 ብር በላይ ለሚደረግ የብድር ውል ስምምነት የግድ ውሉ በጽሁፍ መሆን አለበት በሚል የተቀመጠ ሳይሆን ከ500 ብር በላይ ለሆኑ የብድር ውሎች በሰው ምስክር ወይም በግምት ለማስረዳት የማይቻል መሆኑን ነው።
the law requires written evidence to proof contract of loan in court of law when it is contested by the other party, it doesn't require a written contract for the formation of a valid contract of loan.
አንቀጽ 2472(2) ለይ እንደተጠቀሰው ለብድር ውል ማናቸውም ሌላ አይነት ማስረጃ በማቅረብ ለማስረዳት አይቻለም የሚል ሲሆን ድንጋጌው በባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ባለው ግንኙነት ለይ ተፈጻሚነት የሌለው መሆኑን የፍ/ሀግ አንቀጽ 2473(1) ያስረዳል። በባንኮች ሌሎች አበዳሪ ተቋማት ደንበኞቻቸው ገንዘብ የተበደሩና የተበደሩትን ገንዘብ ያልከፈሉ መሆኑን ለማሰረዳት በተመሣሣይ ሁኔታ የባንክ ተበዳሪ ብድር ያልወሰደ ወይም የወሰደውን ብድር የከፈለ መሆኑን ለማስረዳት በሰው ምስክር ወይም በህሊና ግምት ለማስረዳት የሚቻል መሆኑን የፍ/ህግ አንቀጽ 2473(3) እና በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ቅጽ 10 መ/ቁ 29181 ላይ ከተሰጠው ውሳኔ መረዳት ይቻላል።ከዚህም በተጨማሪ ከ500 ብር በላይ ለተደረገ የብድር ውል ለማስረዳት በቀረበው የጽሁፍ ውል ለይ የተፈረመው ፊርማ የተካደ እንደሆነ ፊርማው የተፈረመው በተበዳሪው መሆኑን ለማስረዳት በብድር ውሉ ላይ የፈረሙትን የሰው ማስረጃዎች በማቅረብ ለማስረዳት እንደሚቻል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሰጥቶ እናግኛለን።
ለሌሎች እንዲደርስ Share ማድረግ አይርሱ።
henoktayelawoffice

የገንዘብ ብድር ውል ፎርም በቴሌግራም ያግኙ
https://t.me/ethiolawtips

ምንጭ
የፍትሐብሔር ህግ
የፌድራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት