Get Mystery Box with random crypto!

ጋብቻ በአንደኛው ተጋቢ ሞት ምክንያት በፈረሰ ጊዜ የጋራም ሆነ የግል ንብረት በምን ያህል ጊዜ ውስ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ጋብቻ በአንደኛው ተጋቢ ሞት ምክንያት በፈረሰ ጊዜ የጋራም ሆነ የግል ንብረት በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መጠየቅ እንዳለበት በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677 መሠረት በቁ. 1845 ላይ የተቀመጠው #የ10_ዓመት ይርጋ ተፈፃሚ ስለመሆኑ፣
የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1677፣ 1845 * ቅፅ-4 መ/ቁ 17937
ጋብቻ ልዩ ባህርይ ቢኖረውም ከሁለቱም ተጋቢዎች ስምምነት የሚመነጭ መብትና ግዴታም የሚጥል በመሆኑ በቤተሰብ ሕግ ግልጽ ድንጋጌ ሣይኖር ሲቀር በውል ሕግ መርሆች ወይም ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ማድረግ የውል ሕግ አንቀጽ 1677ም የሚፈቅደው ነው:: ይኸው ድንጋጌ «ግዱታዎቹ ከውል የተገኙ ባይሆኑም የዚህ አንቀፅ ደንቦች ይፈፀሙባቸዋል» በማለት ይደነግጋል፡፡ የባልና ሚስት የንብረት ክርክር የተለየ የይርጋ ጊዜ ስለሌለው በዚህ ድንጋጌ መሠረት የውል ሕግ የይርጋ ድንጋጌዎች እንዲገዛ ማድረግ ተገቢ ነው:: የውል ሕግ ይርጋ አጠቃላይ ድንጋጌ በአንቀፅ 1845 እንደተገለፀው በሌላ አኳኋን ካልተወሰነ በስተቀር 10 ዓመት ነው፡፡
t.me/ethiolawtips
#share Join