Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ መረጃ - NEWS

የሰርጥ አድራሻ: @ethio_mereja_news
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 58.36K
የሰርጥ መግለጫ

ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም ታሪክ አታበላሽም።

ለአስታየት @ethio_merjabot
@biruke_promotion

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-17 20:52:46 የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ፣ ዛሬ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ያልተከፈላቸው ደመወዝ እንዲከፈላቸው በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የመንግሥት ሠራተኞችን በኃይል እንደበተነ ዶይቸቨለ ዘግቧል።

ፖሊስ ሰልፈኞቹን የበተነው፣ አቤቱታቸውን ለማቅረብ ወደ ርዕሰ መስተዳድሩ ጽሕፈት ቤት በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።

ከኹለት እስከ ሦስት ወራት ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው የጠየቁ ሠራተኞች፣ ባለፈው ማክሰኞም አቤቱታቸውን በሰልፍ ማሰማታቸው አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
5.2K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-17 19:33:35 ቢጂአይ ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ ኩባንያ በቢጂአይ ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻና የፋብሪካ ሽያጭ ዙሪያ በፈጠሩት ውዝግብ ዙሪያ ፍርድ ቤት-መር በኾነ አስማሚ ወገን አማካኝነት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ቢጂአይ አስታውቋል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፐርፐዝ ብላክ ኩባንያ በቢጂአይ ላይ መስርቶት የነበረውን ክስ ዘግቶ፣ በቢጂአይ ላይ ጥሎት የነበረውን እግድ አንስቷል።

በአዲሱ ስምምነት መሠረት፣ ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ከፐርፐዝ ብላክ የተቀበለውን 1 ቢሊዮን ብር የቀብድ ክፍያ መልሷል ተብሏል።

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ኩባንያ ሜክሲኮ የሚገኘውን ዋና መስሪያ ቤቱን በመልቀቅና ፋብሪካውን በመንቀል ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር የወሰነው፣ ፋብሪካው ካረፈበት ቦታ በቁፋሮ የሚወጣው ውሃ መጠኑ በመመናመኑ እንደኾነ ቀደም ሲል መግለጡ አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
5.6K viewsedited  16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-17 18:54:54 ቄስ በላይ መኮንንን ጨምሮ በ5 ግለሰቦች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ

ቄስ በላይ መኮንንን ጨምሮ በአምስት ግለሰቦች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ በመደበኛ ችሎት ተመሰረተባቸው።

ክሱ የተመሰረተባቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን÷ ተከሳሾቹም 1ኛ ቄስ በላይ መኮንን፣ 2ኛ በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማራው ኢያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣ 3ኛ በኮሚሽን ሥራ የተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር፣ 4ኛ ዓለምገና ሳሙኤል ዲንሳ እና 5ኛ የኒሞና ንግድ ሥራ ኃላ/የተ/የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ ናቸው።

4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በቁጥጥር ሥር አለመዋላቸው እና ሌሎቹ ግን በችሎቱ መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግም በተከሳሾቹ ላይ ሁለት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

በአንደኛው ክስ በሁሉም ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ ቁጥር 32 ንዑስ ቁጥር 1(ሀ) እና የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 2 እና ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ነው።

በዚሁ የክስ ዝርዝር ላይም ተከሳሾች በጋራ በመሆን ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ክፍያ እንዲከፈላቸው የሚያደርግ ምንም ዓይነት የሥራ ግንኙነት ሳይኖራቸው፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚገኘው የኅብረቱ የባንክ ሒሳብ ላይ ገንዘብ በዶላር ተቀንሶ ለተከሳሾች ክፍያ እንዲፈፀም የተሰጠ ምንም ዓይነት የክፍያ ትዕዛዝ በሌለበት ሁኔታ ትዕዛዝ እንዳለ አስመስለው በተጭበረበረ መንገድ ከ6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በመውሰድ ለግል ጥቅማቸው በማዋል የማይገባቸውን ብልፅግና ለራሳቸው ለማግኘትና ለሌሎች ሰዎች ለማስገኘት በማሰብ የሚል ተጠቅሷል።

2ኛ ተከሳሽ ለአፍሪካ ኅብረት ድርጅት የግንባታ ቁሳቁስ እንዳቀረበ በማስመሰል የካቲት/2016 ዓ.ም በማቅረብ ወደ ተከሳሹ ሒሳብ ቁጥር 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ከአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ ተዘዋውሮ ገቢ እንዲሆንለት ያዘዘ መሆኑን የሚያሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ በስሙ እንዲዘጋጅ ማድረጉ በክሱ ላይ ተመላክቷል፡፡

3ኛ ተከሳሽ በረከት ሙላቱ ጃፋር ለአፍሪካ ኅብረት ጥልቅ የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ለመሥራት የተስማማ በመሆኑ ከአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ  ወደ ራሱ የሂሳብ ቁጥር 2 ሚሊየን 525 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ገቢ እንዲደረግ ማዘዙን የሚያሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ በስሙ እንዲዘጋጅ ማድረጉ በክሱ ተገልጿል፡፡

4ኛ ተከሳሽ ዓለምገና ሳሙኤል ዲንሳ ለአፍሪካ ኅብረት የጥልቅ ጉድጓድ የውኃ ቁፋሮ ሥራ የሠሩ በመሆኑ ኅብረቱ ወደ ግለሰቡ የሒሳብ ቁጥር 1 ሚሊየን 315 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ገቢ እንዲደረግ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ማዘዙን የሚያሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ በስሙ እንዲዘጋጅ አድርጓል ተብሏል በክሱ ዝርዝር ላይ፡፡

5ኛ ተከሳሽ አበራ መርጋ ተስፋዬ ለአፍሪካ ኅብረት ከማኅበሩ የግንባታ ቁሳቁስ እንዳቀረበ እና ከኅብረቱ ሒሳብ በክፍያ እንዲፈጸምለት ወደ ራሱ በሆነው የድርጀቱ ሒሳብ 1 ሚሊየን 210 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ክፍያ እንዲፈፀም ማዘዙን የሚሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶች በስሙ እንዲዘጋጅ ማስደረጉና ገንዘቡን ወጪ ለማድረግ ሰነዶቹን በውል ባልታወቀ ጊዜ እና ቦታ ለ1ኛ ተከሳሽ መስጠታቸው በክሱ ተጠቅሷል።

እንዲሁም በሁለተኛው የክስ መዝገብ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ ቁጥር 382 ንዑስ ቁጥር 1 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሳሾቹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅምን ወይም መሻሻልን ለማግኘት በማሰብ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8 ሠዓት ተኩል ላይ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አፍሪካ ኅብረት ቅርንጫፍ በመቅረብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚገኘው ኅብረቱ ሒሳብ ላይ ገንዘብ በአሜሪካን ዶላር ወጪ ተደርጎ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ለተጠቀሱት ተከሳሾች እንዲከፈል የሚያዙ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን ጠቅላላ ድምሩ 6 ሚሊየን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም በወቅቱ የምንዛሪ ተመን 346 ሚሊየን 843 ሺህ 475 ብር ለማስተላለፍ ሐሰተኛ ሰነዶቹን ለባንክ እንዲቀርብ በማድረግ እና በማቅረብ በፈጸሙት የክፍያ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም ሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል ተከሰዋል የሚል ዝርዝር አቅርቦባቸዋል።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ችሎት ቀርበው ማንነታቸውንና አድራሻቸውን ካስመዘገቡ በኋላ የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

3ኛ ተከሳሽ ጠበቃ የለኝም ማለታቸውን ተከትሎ ከጠበቃ ጋር ተማክረው እንዲቀርቡና ክሱንም በንባብ ለማሰማት ለፊታችን ሰኞ ተቀጥሯል።

ፍርድ ቤቱ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት ፖሊስ አፈላልጎ እንዲያቀርባቸው በቀጣይ ቀጠሮ ትዕዛዝ እንደሚሰጥበት ገልጿል።

ታሪኩ -አዱኛ

@ethio_mereja_news
5.5K viewsedited  15:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-17 17:33:34
ጃዋር መሀመድ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ አምባሰደርን የሰላም ጥሪ ማውገዙ አሳዛኝ ነው አሉ

የአሜሪካ በኢትዮጵያ አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ “የሰጡትን ሃቀኛ እና ድፍረት የተሞላበት መግለጫ” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማውገዙ ግራ የሚያጋባ እና አሳዛኝ ነው ሲሉ አንጋፋው ፖለቲከኛ ጃዋር መሀመድ ገለጹ።

ጃዋር መሀመድ ዛሬ በይፋዊ ፌስቡክ ገጻቸው ላይ አምባሳደሩ የሰጡትን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ይቀበለዋል ተብሎ የሚጠበቅ ባይሆንም አምባሳደሩ “በተለመደ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ሳይሸፋፍን ይልቁንም የአገር እውነተኛ ወዳጅ ማድረግ እንዳለበት ሁሉ በግልፅ እና በፍትሃዊነት ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች የፖለቲካ ግጭቶችን በትጥቅ ሃይል ለመፍታት የሚያደርጓቸውን አውዳሚ እና የተሳሳተ ሙከራ እንዲተዉ” መጠየቃቸውን አስፍረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ያቀረቡት መግለጫ በሕዝብ የተመረጠን መንግስት ለመገልበጥ የተነሱ ቡድኖችን በመዘርዘር መንግስት እንዴት አገሪቷን መምራት እንዳለበት የሚገልጽ ያልተገባ ምክርን ያዘለ ነው” ሲል ተቃውሞታል።

የአምባሳደሩ መግለጫ “ያልተረጋገጡ መረጃዎች ያሉትና የሁለቱን አገራት ግንኙነት የሚጻረር መሆኑን የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “ስህተቶች እንዲታረሙ” ከኤምባሲው ጋር በቅርበት  እንደሚሰራ ትናንት ባወጣው መግለጫ ማሳወቁ ይታወሳል።

ጃዋር መሀመድ በጽሁፋቸው የፕሪቶሪያ ስምምነት በመፈራረም መንግስት የእርስ በርስ ጦርነቶችን በድርድር ለመፍታት ፍላጎት እንዳለው ቢያሳይም የገባውን ቃል “አሁን ወደኋላ እየተመለሰ ይመስላል” ብለዋል።

መንግስት ተቃዋሚዎቹን በወታደራዊ መንገድ ለማጥፋት ወደመሞከር የተመለሰ ሲሆን ይህ የተሞከረ እና ያልተሳካለት ስልት ባለፉት ዓመታት አገሪቱን አውድሟል ሲሉ ፖለቲከኛው ገልጸዋል።

በሰላማዊ መንገድ የተገኘውን ውጤት ከማጠናከር ይልቅ ከፍተኛ ወታደራዊ እና የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎችን መንግስት እያደረገ፤ ከዚሁ ጎን ለጎን ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ምህዳሩን ዋስትና በማስጠበቅ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ጀምሯል በማለትም አክለዋል።

በቅርቡ በነቀምት እና በባህር ዳር በተደረጉት የድጋፍ ሰልፎች ላይ ከተናገሩት በተቃራኒ በአብዛኛው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎች በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች እየተስፋፉ እንጂ እየቀነሱ አይደሉም ያሉት ጃዋር መሀመድ፤ መከላከያ ሠራዊት በአንዳንድ አካባቢዎች ጥሩ ውጤት ያስመዘገበ ቢሆንም፣ “ስለ ታጣቂዎች የጅምላ መክዳት በተመለከተ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች በጣም የተጋነኑ እና አንዳንዶቹ ፍጹም የፈጠራ ወሬዎች ናቸው” በማለት ጽፈዋል።

አብዛኛዎቹ ዞኖች እና ወረዳዎች በመንገድ አለመገናኘታቸው ማሳያው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ጉዞው በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር እንደሆነ የጠቀሱት ፖለቲከኛው ጃዋር፤ ገበሬዎች ማዳበሪያ መቀበልም ሆነ ሰብል መትከል አይችሉም፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና እና ሕግ-ወጥ ግድያ ህይወትን በገጠሩ ሕዝብ ላይ መቋቋም የማይቻል አድርጎታል ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
5.9K viewsedited  14:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-17 14:14:40
በቁጥጥር ስር ውሏል!

የአሶሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪ በነበረችው ደራርቱ ለሜሳ ግድያ ወንጀል የተጠረጣሪው ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።

የወረዳ አንድ ፖሊስ ጽ/ቤት ኃላፊ ምክትል ኮማንደር በላቸው ፈረደ እንደገለጹት የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸው በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ወረዳ አንድ ልዩ ቦታው ሰላም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አከባቢ ዕለቱ ረቡዕ ግንቦት 07/2016 ዓ/ም ከጧቱ በግምት 2:45 ላይ በሟች እና በተጠርጣሪው መካከል በተፈጠረው በሀሳብ ያለመግባባት ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ ጀርባዋ ላይ በጩቤ በመውጋት የተማሪዋ ህይወት ሊያልፍ ችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

ምክትል ኮማንደሩ አክለውም ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ወንጀሉን የፈጸመውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ የሚገኝ መሆኑን ገልጸው በቀጣይ የምርመራ ውጤቱን በአጭር ጊዜ ለህዝብ እንደሚገለጽም ተናግረዋል።

በመጨረሻም የወንጀል ድርጊቱ የተፈጸመው ከዩኒቨርስቲው ግቢ ውጪ እና ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ ዱከም ከተማ አቋርጦ ወደ አሶሳ ከተማ ለስራ ጉዳይ በመምጣት የወንጀል ድርጊት የፈፀመ ሲሆን ነገር ግን በአንዳንድ ማህበራዊ ሚድያዎች ድርጊቱ የተፈጸመው በግቢ ውስጥ ነው በሚል የሚሰራጨው እና የብሔር ግጭት አስመስለው የሚወራው ፍጹም ከእውነት የራቀ እና ሁለቱም የአንድ ብሔር ተወላጅ እንዲሁም በጓደኝነት አብረው እየኖሩ የነበሩ መሆኑን ኃላፊው ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
6.9K views11:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-17 09:46:25
መንግስት የአሜሪካ አምባሳደር ያደረጉትን ንግግር ተቃወመ

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ለኢትዮጵያ መንግሥት ላይ "ውንጀላ አቅርበዋል"፤ "መንግሥት አገሪቱን እንዴት መምራት እንዳለበትም ያልተጠየቁትን ምክር ለግሰዋል" በማለት ወቅሷል።

የአምባሳደሩ ንግግር "ትርጉም የማይሰጡ" እና "በበቂ ኹኔታ ያልተጤኑ" ሃሳቦችን ያካተተ ነው ያለው ሚንስቴሩ፣ አምባሳደሩ "በምርጫ የተመረጠውን መንግሥት በኃይል ለመጣል የሚሠሩ ቡድኖችንም በስም ጠቅሰዋል" በማለት ተችቷል።

ኢምባሲው፣ በአምባሳደሩ መግለጫ ላይ የተንጸባረቁትን "የፍሬ ነገር ስህተቶች" ለማስተካከል ከኢምባሲው ጋር እንደሚሠራ ገልጧል።

አምባሳደር ማሲንጋ ትናንት የመን የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ውስጥ ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት በሲቪሎች ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳይ በመጥቀስ "አገር ዓቀፍ የተኩስ አቁም" እንዲደረግ ጠይቀው ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.7K viewsedited  06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-16 19:45:34 በሕወሃት አመራር ውስጥ የርስበርስ መገዳደል ሊሰፍንና ይህም በትግራይ ሕዝብ ላይ አደጋ ሊደቅን ይችላል በማለት ዶይቸቨለ የዜና ማሠራጫ ጣቢያ ባለፈው ዕሁድ "ሐሰተኛ" እና "አሳሳች" መረጃ አሠራጭቷል ሲል ሕወሃት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ከሷል።

ሕወሃት፣ የጣቢያው ዘገባ በክልሉ ሽብር እና ጥርጣሬ እንዲነግስ የሚያደርግ እና ምናልባትም ያልታወቀ ስውር ሴራ መኖሩን የሚያሳይ ሊኾን ይችላል ብሏል።

ሕወሃት፣ የጣቢያው አስተዳደር በዘገባው ላይ ምርመራ በማድረግ ለዘገባው ተጠያቂ በኾኑ ግለሰቦች ላይ አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስድና ይቅርታ እንዲጠይቅም ጠይቋል።

@sheger_press
8.4K views16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-16 16:46:20
እነ አቶ ምትኩ ካሳ በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ!

የቀድሞ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት እነ አቶ ምትኩ ካሳ በተከሰሱበት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ።የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በተከሳሾቹ ላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው ምስክር ቃልና የሰነድ ማስረጃን መርምሮ ብይን ሰጥቷል።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግ በየደረጃው ተሳትፏቸው ተጠቅሶ የተረጂዎችን ቁጥር በማጋነን የተለያዩ የእርዳታ ዓይነቶችን ከመጋዘን ወጪ በማድረግ ለተረጂዎች ሳይደርስ ተሽጦ ለግል ጥቅም ውሏል በማለት የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 (1) ሀ እንዲሁም 33 እና የሙስና ወንጀልን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁ.881/2007 አንቀጽ 9 ንዑስ ቁጥር 3 እና በህገወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብን ወይም ንብረትን ምንጩን ደብቆ ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀል ክስ በነሃሴ ወር 2014 ዓ.ም መመስረቱ ይታወሳል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:-

https://www.fanabc.com/archives/246245

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
8.7K viewsedited  13:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-16 12:34:53
አዋሽ ባንክ ለ3ኛ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምርጥ ባንክ በመባል መመረጡ ተገለፀ።

ግሎባል ፋይናንስ ማጋዚን ለ31ኛ ጊዜ የምርጥ ባንኮችን ዝርዝር ይፋ ባደረገው መሠረት ከ36 የአፍሪካ አገራት ውስጥ ከተመረጡ ባንኮች መካከል አዋሽ ባንክ አንዱ ሆኗል።

የምርጥ ባንኮች ልየታ የተደረገው በተለያዩ መስፈርቶች መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ የባንኮቹ ትርፋማነት፣ የሀብት ዕድገት፣ተደራሽነት እና የመሳሰሉት ከመስፈርቶቹ መካከል የተካተቱ ናቸው።

በዚህ መሠረት አዋሽ ባንክ ከ36 አገራት ከተመረጡ የአፍሪካ ባንኮች መካከል አንዱ ሆኖ መመረጡን እና ከኢትዮጵያ ደግሞ ብቸኛው ባንክ መሆኑን የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ ሽፈራው ገልጸዋል።

በዚህኛው አመት በተካሄደው ምርጫ ከ1መቶ50 በላይ አገራት የሚሰሩ ባንኮች የተካተቱበት መሆኑም ነው የተገለጸው።

አዋሽ ባንክ በአሁኑ ጊዜ ከ9መቶ38 በላይ ቅርንጫፎች በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እንዳለው የተገለፀ ሲሆን ከ12.1 ሚሊየን በላይ ደንበኞችንም ማፍራቱ ተነግሯል።

የባንኩ ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ከ2መቶ15 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱም ተገልጿል።

ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች የተሰጠው የብድር መጠንም ከብር 1መቶ78 ቢሊየን ብር በላይ መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደገለፁት ለባንኩ የሚሰጠው ዕውቅናና የሽልማት ስነ-ስርዓት የአለም ገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክ በዋሽንግተን ዲሲ በኦክቶበር 2024 በሚያደርጉት ጉባኤ ወቅት እንደሚከናወን አስታውቀዋል።(ethiofm)

@ethio_mereja_news
8.6K viewsedited  09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-16 12:05:29 በኢትዮጵያ ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች!

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ኧርቪን ጄ.ማሲንጋ፣  ረቡዕ፣ ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም.፣ አገራቸው በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ያላትን ፖሊሲ የሚያንጸባርቅ ንግግር አድርገዋል፡፡

አምባሳደሩ፣ በአዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ ግቢ ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያ በትጥቅ ግጭት ውስጥ የገቡ አካላት፣ ግጭት አቁመው በንግግር ሰላምን እንዲያሰፍኑና የሰብአዊ መብቶችን እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡

የታጠቁ ቡድኖች፣ ፖለቲካዊ ዓላማዎቻቸውን በዐመፅ ለማሳካት እየገፉ መኾናቸውንና መንግሥትም ይህን ለመከላከል የሚወስዳቸው ርምጃዎች፣ በፖለቲካ ምኅዳሩ ላይ የማይካድ ተጽእኖ ያለው መኾኑን የተናገሩት አምባሳደር ማሲንጋ፣ ውይይትን ወደ ጎን ያለው ይህ አካሔድ የመብት ጥሰቶችም እንዲቀጥሉ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

በመላ አገሪቱ “ሰላማዊ ዜጎች፣ በተለያዩ ኀይሎች ከሕግ ውጭ ግድያ፣ የዘፈቀደ እስራት፣ አስገዳጅ ስወራ፣ ከግጭት ጋራ የተያያዘ ጾታዊ ጥቃት እና ሌሎችም ጥቃቶች እየተፈጸሙባቸው መኾኑን የሚገልጹ ዘገባዎችን ስናይ እጅግ አዝነናል፤” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱት የፋኖ ታጣቂ ቡድኖች፣ ፊታቸውን ወደ ድርድር እንዲያዞሩ አምባሳደሩ ሲጠይቁ፤ ህወሓት፣ በኀይል ወሰን ለማስመለስ ከሚደረግ እንቅስቃሴ እንዲቆጠብና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊትም የሰላም ውይይትን እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡

በአፍሪካ ቀንድ የዩናይትድ ስቴትስ ልዩ መልዕከክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር፣ ልዩ ልዩ የሲቪክ ተቋማት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች መሪዎች እና ተወካዮች በተገኙበት አምባሳደሩ ባደረጉት የፖሊሲ ንግግር፣ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በውስጣዊ ግጭቶች እየታመሰች እንደምትገኝ አስታውሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥትም፣ የአገሪቱን ችግሮች በኀይል ለመፍታት ከሚያደርገው ጥረት እንዲቆጠብ የጠየቁት አምባሳደሩ፣ በእስር ላይ የሚገኙ ቁልፍ የፖለቲካ ሰዎችን መፍታቱ ጠቃሚ እንደኾነም

አስገንዝበዋል። ያን ተፈጻሚ ማድረግም፣ ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉትን የፖለቲካ ውይይት ሊያግዝ እንደሚችል ነው የተናገሩት።

አምባሳደር ማሲንጋ፣ ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲፈጸምም ጠይቀዋል፡፡

ሁሉም የታጠቁ ተዋናዮች፣ በመላ አገሪቱ ዐዲስ የሕዝብ መፈናቀልን ጨምሮ ለሰዎች ሥቃይ ምክንያት ከመኾን መገታት እንዳለባቸው ያነሡት አምባሳደሩ፣ ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትንና የውኃ መሠረተ ልማቶችን ዒላማ ማድረግ እንዲቆም፣ የተሟላና ያልተገደበ ሰብአዊ አቅርቦት እንዲኖርም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ይህም እንደ መነሻ፣ ጊዜያዊ አገር አቀፍ የተኩስ አቁምን እንደሚጨምር አመልክተዋል፡፡

ግጭት የኢትዮጵያውያንን ሥቃይ ከማባባስ ያለፈ መፍትሔ የሌለው በመኾኑ፣ ውይይት ትኩረት እንዲደረግበት ያሳሰቡት አምባሳደሩ፣ ምንም እንኳን ፍጹም ሊኾን ባይችልም፣ ኹሉም ወገኖች የአገራዊ ምክክሩን ዕድል ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

Via VoA

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
7.7K viewsedited  09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ