Get Mystery Box with random crypto!

ዱንያ short ላይፍ

የቴሌግራም ቻናል አርማ duniyashortleif — ዱንያ short ላይፍ
የቴሌግራም ቻናል አርማ duniyashortleif — ዱንያ short ላይፍ
የሰርጥ አድራሻ: @duniyashortleif
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 250

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-06-30 20:34:09 ዐጢይያህ ኢብኑ ዑርወህ አስ ሰዕዲይ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹አንድ ባሪያ (በግልፅ) የተከለከሉ ነገሮችን ለመጠንቀቅ ሲል (በግልፅ) ያልተከለከሉት እስካልተው ድረስ (አላህን) የሚፈሩ (ሙተቂን) ከሆኑ ሰዎች ደረጃ አይደርስም፡፡››

ሐዲሱን ቲርሚዚይ ዘግበውታል

‹‹ ከአጠራጣሪ ነገሮች መራቅና ሀላል መሆኑ በግልፅ የማይታወቅን ነገር መጠንቀቅ የተቅዋ ምልክት ነው፡፡



Share share share share share share
66 viewsቢስሚላሂ, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 18:56:14 የምዕመናን መሪ የሆኑት ዑመር ኢብኑ አል ኸጣብ (ረ.ዐ)‌‎ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸለሁ አሉ። ‹‹ስራዎች ሁሉ የሚመዘኑት በኒያ (በሃሳብ) ነው። ሁሉም ሰው ያሰበውን ነገር ያገኛል። ስደቱ ወደ አላህ እና ወደ መልእክተኛው ከሆነ፥ ስደቱ ወደ አላህ እና ወደ መልእክተኛው ይሆንለታል። የተሰደደው ዓለማዊ (ዱንያ) ጥቅማጥቅም ለማግኘት ወይም ሴት ለማግባት ከሆነ ስደቱ ለተሠደደበት ነገር ነው፡፡››

ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

‹‹ ከማንኛውም ተግባር በፊት ኒያ አስፈላጊ መሆኑን ነው፡፡
‹‹ አንድን ነገር ለማከናወን በልቦና ማሰቡ በቂ ሲሆን መናገሩ (ድምፅ ማውጣቱ) ሱና ነው፡፡



Share share share share share share
72 viewsቢስሚላሂ, 15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-27 20:43:37 አቡ ሁሬይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹የቂያማ ቀን ግዙፍና የሰባ ገላ ያከው ሰው ከአላህ ዘንድ የትንኝ ክንፍ ያህል ክብደት የሌለው ሆኖ ይመጣል (ይቀርባል)፡፡››

ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ የቂያማ ቀን የሰው ታላቅነትና ማንነት የሚለካው በሰራው መልካም ስራ መጠን እንጂ በውጫዊ ገፅታ ወይም ውፍረት አለመሆኑን እንረዳለን፡፡



Share share share share share share share
74 viewsቢስሚላሂ, 17:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 20:03:39 አብደሏህ ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹በአላህ ዘንድ መልካም ባልንጀራ፤ ለባልንጀራው መልካም የሆነው ነው፤ በአላህ ዘንድ መልካም ጎረቤት ለጎረቤቱ መልካም የሆነው ነው፡፡››

ሐዲሱን ቲርሚዚይ ዘግበውታል

‹‹ ለጓደኞችና ለጎረቤት ጠቃሚ መሆንንና ጉዳት እንዳያገኛቸው መከላከል የሚያስገኘው ትሩፋት፡፡



Share share share share share share
82 viewsቢስሚላሂ, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 20:01:55 ሞኝነት ነዉ

ተዉባን ማዘግየት
ሞትን መርሳት
ሚስጥርን ማባከን
ዓላማን መዘንጋት
ግዴታን አለመወጣት
ጊዜን ማባከን
ወላጅን አለመታዘዝ
ሰዉን መበደል
73 viewsቢስሚላሂ, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-25 20:07:52 አነስ (ረ.ዐ)‌‎ እንዳስተላለፉት በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘምን ሁለት ወንድማማቾች ነበሩ፡፡ አንደኛ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ (ኢልም ሲቀስም)፤ ሌላኛው ደግሞ በስራ ተጠምዶ ይውላሉ፡፡ ሰራተኛው ወንድሙን ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ከሰሰ፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹ምናልባትም ‹ሪዝቅ› የምታገኘው በርሱ ሰበብ ሊነሆን ይችላል›› አሉት፡፡

ሐዲሱን ቲርሚዚይ ዘግበውታል፡፡

‹‹ የአላህ ዲንና ሸርዓ ለመጠበቅ ሲል የሚባክን አላህ መሰረታዊ ፍላጎቶቹን የሚያሟለበትን መንገድ ያመቻችለታል፡፡
‹‹ አንድ ሰው ‹ሪዝቅ‹ የሚያገኘው በስሩ ባሉ ቤተሰቦቹ ሰበብ መሆኑን፡፡



Share share share share share share
83 viewsቢስሚላሂ, 17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 20:33:58 ኢብኑ ዐብባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹ከልብሶቻችሁ ነጩን ልበሱ፡፡ እርሷ ከልብሶቻችሁ ሁሉ በላጯ ናትና፡፡ ሙታኖቻችሁንም በርሷ ገንዙ፡፡››

ሐዲሱን ነሳኢና ሀኪም ዘግበውታል

‹‹ ነጭ ልብስ ተወዳጅ ነው፡፡ በጁምዓ ቀንና በተለያዩ አጋጣሚዎች የበለጠ ይወደዳል፡፡
‹‹ ሙታንንም በነጭ ልብስ ከፈን መገነዝ የተወደደ መሆኑን እንረዳለን፡፡



Share share share share share share
87 viewsቢስሚላሂ, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 19:40:54 አቡ ሁሬይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹ከናንተ አንዳችሁ ሰዎችን (ኢማም ሆኖ) በሚያሰግድበት ወቅት (ሶላቱን) ቀለል ያድርግ፤ ከነርሱ (ከተከታዮቹ) መሀከል ደካሞች፣ በሽተኞችና ዕድሜያቸው የገፉ ሰዎች ይኖራሉና፡፡ ከናንተ አንዳችሁ ለብቻው በሚሰግድበት ወቅት ግን ያሻውን ያህል ያስረዝም፡፡››

በሌላ ዘገባ ደግሞ ‹‹ጉዳይ ያላቸው›› በሚል ቃል ማከላቸው ተመልክቷል፡፡

ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ ተከታዮቹ ሶላቱ እንዲረዝምላቸው የሚፈልጉ ከሆነ ግን ማስረዘሙ ተወዳጅ ነው፡፡ ከዛ ውጪ ማስረዘሙ አግባብ አይደለም፡፡



Share share share share share share share share
97 viewsቢስሚላሂ, 16:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 02:00:38 አቢ አብባስ አብደሏህ ኢብኑ አብባስ ኢብኑ አብደል ሙጦሊብ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በሀዲሰል ቁድስ ተከታዩን ተናግረዋል፡- ‹‹አላህ መልካምና ክፉ ተግባራትን ፅፏል፤ ይህንኑ አብራርቷልም፡፡ አንዲትን መልካም ተግባር ለመፈፀም ያሰበና ያልፈጸማት ልዑልና ቁድስ የሆነው አላህ ከርሱ ዘንድ አንድ ሙሉ መልካም ተግባር (የመልካም ተግባር ምንዳ) ይፅፍለታል፡፡ አስቦ ከፈፀማት ደግሞ ከ10 እስከ 700 እጥፍ፣ ከዚያም በላይ መልካም ተግባራትን ይፅፍለታል፡፡ ክፉ ተግባር አስቦ ካልፈፀማት አላህ ከርሱ ዘንድ አንድ ሙሉ መልካም ተግባር ይፅፍለታል፡፡ ግን አስቦ ከፈፀማት አንድ ክፉ ተግባር ብቻ ይፃፍበታል፡፡

ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ መልካም ተግባርን ለመፈፀም አስቦ (ኒያ ኖሮት) መፈፀም ባይችልምም አላህ ምንዳውን አይነሳውም፡፡
‹‹ ክፉ ነገር ለመፈፀም ኒያ ኖሮት ግን አላህን ፈርቶ ከመፈፀም የተቆጠበ አላህ መልካም ተግባር ምንዳ እንደሚፅፍለት፡፡



Share share share share share share
100 viewsቢስሚላሂ, 23:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:34:25 አቡ ሁሬይራ (ረ.ዐ)‌‎ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹አንድን ሙስሊም አንድም ችግር ወይም በሽታ፣ ሀሳብ ወይም ቁጭት፣ የሚያውክ ነገር ወይም ጭንቀት አያገኘውም - በምትወጋው እሾህ እንኳ አላህ በእርሷ (ሰበብ) ወንጀሎችን ያበሰለት ቢሆን እንጂ!››

ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ በሽታዎችና ሌሎችም አዋኪ ነገሮች ለሙስሊሙ ወንጀሉን ያራግፉታል፡፡



Share share share share share
90 viewsቢስሚላሂ, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ