Get Mystery Box with random crypto!

ዱንያ short ላይፍ

የቴሌግራም ቻናል አርማ duniyashortleif — ዱንያ short ላይፍ
የቴሌግራም ቻናል አርማ duniyashortleif — ዱንያ short ላይፍ
የሰርጥ አድራሻ: @duniyashortleif
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 250

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-06-17 20:38:10 አል አገር ኢብኑ የሳር አል-ሙዘኒይ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ በፀፀት ተመለሱ (ተውበት አድርጉ)፤ ምህረትንም ለምኑት፤ እኔ በየቀኑ 100 ጊዜ ተውበት አደርጋለሁ፡፡››
ሐዲሱን ሙስሊም ዘግበውታል

‹‹ ምህረትን መለመን እና ተውበትን ማብዛት አፅንዖት ለመስጠት፡፡
‹‹ 100 ጊዜ የተባለው ብዛት ለማመላከት እንጂ ገደብ ለማድረግ አይደለም፡፡



Share share share share share
86 viewsቢስሚላሂ, 17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 20:27:03 :::::የሱናዋ ቆንጆ::::

ጠንካራዋ ወጣት በተውሒድ የፀናች፡
ከቢድዐ ርቃ ሱናን የጠበቀች፡
ቲፎዞ የማትሆን ለጥመት ቡድኖች፡
የሱና ተከታይ እህቴሥ እሷ ነች፡
ተውሒድና ሱናን አጥብቃ የያዘች፡
በኢሥላም ብርሀን ደምቃ የተዋበች፡

ሱና ሲነገራት ላይ ውሥጧ ሚፈካ፡
የቢድዐ ካዝና ያልሆነች ፋብሪካ፡

ተረት ለሚያወራ አድናቂ ያልሆነች፡
ሰለፍይዋ ጀግና እሷሥ እህቴ ነች፡
የጮኸው ሰው ሁሉ ደርሦ ማያሞኛት፡
ቁርዐንና ሀድሥ መረጃ ሚዳኛት፡
ሀታ አነጋገሯ የተሥተካከለ፡
የድምፆ ለዘብታ ወንድ ያላማለለ፡
ንግግሯ ቁጥብ " ሰለፍይ" የሆነች፡
እውነቱን ልናገር ይህች እህቴ ነች፡

በሰለፎች መሥመር በጠራ አቂዳዋ፡
ከቢድዐ አንጃወች ታጋይ ለሱናዋ፡
በኢኽቲላጥ ቦታ አትገኝም እሷ፡
የሱና ወጣት ነች ሀያሉን ፈጣሪ ትፈራለች ነፍሷ፡

ባለንበት ዘመን በሱና ላይ ፀንታ እንግዳ የሆነች፡
እኔም ወንድሟ ነኝ እሷም እህቴ ነች፡
እናም እህቶቸ!
አቧራው ተነሥቶ ቢድዐ የወረሰው ሱናው እሥኪመጣ፡
እውቀትን ፈልጉ በተውሒድ ላይ ፅኑ የፈለገው ይምጣ፡

የሀቅ ዘበኛ የቢድዐ ጠላት፡
እውነተኛ ቆንጆ ሱንይ እህቴ ናት፡
የእውነት ዘብ ጠባቂ ወጣቷ ኮረዳ፡
ለእምነቷ የቆመች ይህች ነች አራዳ፡
የጥመት መፍለቂያ…
ቢድዐ ማሥታወቂያ ያልሆነች ኮረጆ፡
እህቴማ እርሷ ነች የሱናዋ ቆንጆ፡
88 viewsቢስሚላሂ, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 20:06:11 ሚቅዳድ ኢብኑ መዕዲየክሪብ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብሏል ‹‹አንድ ሰው በእጁ (ሰርቶ ለፍቶ) ካገኘው የተሻለ ምግብ አልተመገበም፡፡ ነቢዩሏህ ዳውድ (አ.ሰ) ይመገቡ የነበሩት ሰርተውና ደክመው ያገኙትን ብቻ ነው፡፡››

ሐዲሱን ቡኻሪ ዘግበውታል

‹‹ መልካምና አስደሳች ምግብ ላብን አንጠፍጥፈውና ሰርተው፣ ደክመው የሚያገኙት መሆኑን ነው፡፡
‹‹ ይህ ሀዲስ ሰዎች ስራ ሰርቶ እንዲኖሩ የሚያበረታታና የሚያነሳሳ ነው፡፡



Share share share share share
106 viewsቢስሚላሂ, 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-27 19:37:41 አቡ ኡማመህ ሱደይ ኢብኑ ዐጅላን አል-ባሂሊይ (ረ.ዐ) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የመሰናበቻ ሀጅ ዕለት ተከታዩን ንግግር ሲያሰሙ ሰምቻለሁ በማለት አስተላልፈዋል፡- ‹‹አላህን ፍሩ፤ አምስት ወቅት ሶላቶችን ስገዱ፤ የረመዷንን ወር ፁሙ፤ ከገንዘባችሁ ዘካን ስጡ፡፡ መሪዎቻችሁን ታዘዙ፤ ጌታችሁ ያዘጋጀላችሁን ጀነት ትገባላችሁ፡፡››

ሐዲሱን ቲርሚዚይ ዘግበውታል

‹‹ የተጠቀሱትን ተግባራት ማከናወን አላህን የመፍራት ምልክት መሆኑን፡፡
‹‹ መሪው ወይም መንግስት ወደ ወንጀል እስካላዘዛችሁ ድረስ መሪዎቹን መታዘዝ፡፡



Share share share share share share share
149 viewsቢስሚላሂ, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 22:24:05 አቡ ሁሬይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት አንድ ሰው የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ቀረበና፡- ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሆይ! ይበልጥ ሎጎዳኘው የሚገባኝ ሰው ማንነው?›› አላቸው፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹እናትህ›› አሉት፤ በድጋሚ ‹‹ከዚያስ ቀጥሎ ማንነው?›› አላቸው፤ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹እናትህ›› አሉት፡፡ ሰውዬው ‹‹ከዚያስ ቀጥሎ?›› አላቸው፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹እናትህ›› አሉት፡፡ (ለአራተኛ ጊዜ) ‹‹ከዚያስ ቀጥሎ?›› አላቸው፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹አባትህ› አሉት፡፡

ሐዲሱን ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

በሌላ ዘገባ ደግሞ ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ይበልጥ ልጎዳኘው የሚገባኝ ሰው ማንነው?›› ብሎ ጠየቃቸው፡፡ ነብዩም (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹እናትህ ከዚያም እናትህን ከዚያም እናትህን ከዚያም የቅርብ ዘመድህን ከዚያም የቅርብ ዘመድህን›› አሉት፡፡

‹‹ እናት ከልጁ መወለድ እስከ ሞቱ ድረስ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለችና የምትከፍልም በመሆኗ ከፍተኛ አትኩሮት ለመስጠት ነው፡፡
‹‹ የእናት ደረጃ ከአባት የበለጠ ከፍተኛ ስፍራ እንዳለው ማሳያ ነው፡፡



Share share share share share share share share share share
143 viewsቢስሚላሂ, 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ