2022-08-15 20:35:06
"አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል:-
‹‹አንድ ሰው በጀመዓ (በህብረት) የሚሰግዳት ሶላት ከስራ ቦታው ወይም ከቤተሰቡ ከሚሰግድባት ሶላት ከሀያ ሶስት እስከ ሰላሳ ብልጫ አላት ይህም የሚሆነው በተሟላ መልኩ ውዱዕ ከፈፀመና ከዚያም
ሰላትን እንጂ ሌላን ባለመሻት ከቤቱ የወጣበት አላማ ሶላት ብቻ ሆኖ ወደ መስጊድ ከመጣ ነው::
ወደ መስጊድ በሚያደርገው ጉዞ በእያንዳንዱ እርምጃ አንድ ደረጃ ከፍ ይደረግለታል:: በዚያችው እርምጃ አንድ ኃጢአት ይታበስለታል መስጊድ እስኪገባ ድረስ መስጊድ ከገባ በኋላ መስጊድ ውስጥ ለመቆየቱ
ምክንያት ሶላት ብቻ እስከሆነች ድረስ ሶላት ውስጥ እንዳለ ይቆጠርለታል ከእናንተ አንዳቹ የሰገደበትን ቦታ እስካለቀቀ ሰዎችን እስካላወከና ውዱእ እስካልፈታ መላይኮች አላህ ሆይ! ምህረትን ለግሰው አላህ ሆይ! ጸጸቱን ተቀበለው እያሉ ዱዓ ያደርጉለታል፡፡››
(ቡኻሪና ሙስሊም የሐዲሱ ቃል የሙስሊም ነው)
- ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበዉታል"
==========================================
Share share share share share share share
38 viewsቢስሚላሂ, 17:35