Get Mystery Box with random crypto!

....

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemdkunbekelez — .... Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemdkunbekelez — ....
የሰርጥ አድራሻ: @zemdkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 27.66K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው።
ይህ የዩቲዩብ ቻናሌ ደግሞ ሰኔ 6/2012 ዓም ከራየን ወንዝ ማዶ የተከፈተ ነው።
https://www.youtube.com/c/ZemedkunBekele?sub_confirmation=1
እንደ ፌስቡክ፣ እንደ ቴሌግራሙ ሁሉ በዚህ መንደርም ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክ ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-06 17:15:25 ከምስጋና በኋላ…

"ርዕሰ አንቀጽ"

"…የዛሬው የምስጋና ጊዜ ደግሞ እጅግ የተለየ ነው። በ20 ደቂቃ ውስጥ 1ሺ ሰው፣ በ3 ሰዓት ውስጥ 5ሺ ሰው እግዚአብሔር ይመስገን ሲል አየሁ። ከምር ይሄ ተአምር ነው። አለመደነቅም አይቻልም። ቴሌግራም በእጅህ ላይ ባለ ሥልክህ የምትጠቀመው ፕላትፎርም ነው። የምታነበውን፣ የምትሰማውና፣ የምታየውን መልእክት ሁሉ ወደህና ፈቅደህ ወደራስህ የምትጠራው ራስህ ነህ። መንደር መርጠህ የምትገባውም ራስህ ነህ።

"…በዚህም መሰረት አንተ እና አንቺ ወደኸኝም ይሁን የተለየ ሌላ ምክንያት ኖሮህ ወደ እኔ ወደ ዘመዴን ፔጅ መንደር ተንጦልጡለህ የምትመጣው አንተው ራስህ ነህ። የምጽፈውን፣ የምለጥፈውን እንድታይ በካህን አላስገዘትኩህም፣ በፖሊስ አላስገደድኩህም ራስህ በምርጫህ ወደህና ፈቅደህ ነው የምታየኝ የምታነበኝም።

"…ታዲያ ቤቴ ራሱን የቻለ የራሱ የሆነ ሕግ እና መመሪያም አለው። በቤቴ ውስጥ ወያኔም፣ ሸአቢያም፣ ብልፅግናም፣ ኦነግም፣ ኢዜማም፣ ብአዴንም ሆኖ መቀመጥ ይቻላል። ኦሮሞም፣ ትግሬ፣ ዐማራ፣ ጉራጌ፣ ወላይታ ሲዳማ ወዘተም ሆኖ መቀመጥ ይቻላል። የወሃቢይ እስላም፣ ፅንፈኛ ጴንጤ፣ እኔን ጠል ኦርቶዶክስ፣ ተሃድሶም ሆኖ መቀመጥ ይቻላል። ባለሥልጣን፣ ጀነራል፣ ኮሎኔል፣ ኢንጅነር፣ ዶክተር፣ ጋዜጠኛ፣ አንጥረኛ ሆኖ መቀመጥም ችግር የለውም። ዘፋኝ ሁን ዘማሪ፣ ቄስ ሆን ሼክ ፓስተር ለእኔ ደንታዬ አይደለም። ሃብታም ሁን ደሃ ኬሬዳሽ። ምንም ሁን ለደንታህ ነው። ለወሬ ብቻ ጠኔውን ለማስታገስ የሚቀመጥ አለ። ለመሳቅ፣ ለማልቀስ፣ ኮመንት ለማንበብም የሚመጣ አለ። እሱም ችግር የለውም።

"…ክልክሉ ነገር በቤቴ ውስጥ አዛዥ ልሁን ስትል ነው። በእኔም በባለቤቱና በመንደሬ ኗሪዎች ላይ በሌላ ቦታ የለመድከውን ክፍትአፍነትህን እዚህ እሞክረዋለሁ ያልክ እንደሆነ ብቻ ነው። ልቅነትህን እዚያው በለመድክበት። ከርዕስ ውጪ ማውራት፣ በጎንህ የታጠቅከውን ሽጉጥ እየዳሰስክ እንደ ወጠጤ በቤቴ ውስጥ በእኔም ላይ ሆነ በሌላው ላይ መደንፋት፣ ማቅራራት፣ መሸለል ፈፅሞ አይፈቀድም። ከቻልክ በሰላም፣ በጨዋ ደንብ የተጻፈው ነገር ደምስርህን ቢበጥሰውም ነርቭህን ቢነካውም፣ ጥቅምህን ቢጎዳውም ተረጋግተህ ሃሳብህን በጨዋ ደንብ መግለፅ እንጂ በባለጊዜ ነኝ ሙድ ነጭ ቂጡን የጣለ ዱርዬ ነኝ ብለህ፣ በአንጎበር አፍህ እወበራለሁ፣ የቁጭራ ሰፈር ስድብ እሳደባለሁ ማለት በፍጹም አይፈቀድም። አስነጥስህሃለሁ። እቀስፍሃለሁ። ከዚያ ፍርዬ ጋር ሄደህ በሌላ ሲም ካርድ ጨዋ ሆነህ ትቀላቀለኛለህ።

"…በእኔ ፔጅ እኔን ብቻ ልትሰድቡበት የምትችሉት የምፈቅድላችሁ ስድብም አለ። እኔን ብቻ ነው ታዲያ። ማንም የፔጄ ደንበኛ ሌላ ሰው ተሳስቶ መስደብ አይችልም። መሞገት እንጂ። በፔጄ ላይ እኔን በተመለከተ እኔን መስደብ የሚፈልግ ባህላዊ፣ ሃገር በቀል የሆነ እናትን ሳይሆን አባቴን በስሱ መስደብ ይቻላል። "አፍር ያስበላህ፣ አፈር ብላ፣ ሙት ድፍት ያድርግህ የአባቴ አምላክ፣ ምኑ ሙትቻ ነው በአላህ፣ ምናምን ማለት ይቻላል። እንዲያ ብትሉኝ ተአብ የለውም። ከምንአባክንስና፣ አፈር ደቼ ያስበላህና ከመሳሰለ ተወዳጅ ከአካባቢያችን በቀላሉ ከማንኛውም ሰው አፍ ከምናገኛቸው ሃገር በቀል ስድቦች እንጂ ከዚያ የዘለለ ስድብ በፔጄ አይፈቀድም። ባህላዊው፣ ያደግንበት፣ የምርቃት አቻ የሆነ፣ የሰፈር ሰው ሁሉ እንደ ልጁ ተቆጥቶ ሰድቦ፣ ቆንጥጦን እኛን ባሳደገበት ስድብ መሰደብ ብዙም አያመኝም። ደስስም ነው የሚለኝ። ለበዓሉ ድምቀት መኖርም አለበት። ከዚያ ያለፈው ግን አይቻልም። አይፈቀድም።

"…የእኔንም ሆነ የሌላ ሰው አይን የሚያቆሽሽ ስድብ ለሚሳደቡ ሰዎች ጥብቅና ትቆሙ ዘንድ ሳትጠየቁ በስድብ መልስ የምትሰጡ ሰዎችንም አብሬ ነው የምቀስፈው። የማያስቀስፍ ስድብ እንኳ ቢሆን ኮመንታችሁን አነሣዋለሁ። ያለበለዚያ የሚፈጠረው ምንድነው የሚሆነው እኔ ተሳዳቢውን ስቀስፈው ኮመንታችሁ ብቻውን ይቀርና ለተመልካች ግራ ስለሚያጋባ ስታወዛግቡ ስለምትገኙ ነው። ደግሞም እኔ 18 ዓመት ያለፈኝ፣ 50 ዓመት ሊሞላኝ አንድ ፈሪ የቀረኝ የሽማግሌ ፍንዳታ ነኝ። ለእኔ ተደርቦ መልስ መስጠት በፍጹም ነውር ነው። ለነውረኛ እኔ ራሴ እበቃዋለሁ።

"…በተረፈ በፔጄ ላይ የትኛውም ዓይነት ማስታወቂያ መሥራት ክልክል ነው። የታመመ ሰው ይሁን፣ የጠፋ ሰው ይሁን፣ እኔ ያመንኩበት እና ኃላፊነት የምወስድበት የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ካልሆነ በቀር ምንም ዓይነት ማስታወቂያ መጻፍ አይፈቀድም። እቀስፈዋለሁ። የባሕል መድኃኒትም ሆነ የጉዞ መርሃ ግብር፣ የስብሰባ ጥሪ፣ የምንም ምርቃት ማስተዋወቅ ክልክል ነው።

"…ሌላው የሚያስቀስፈው የመንደሬን ነዋሪዎች በውስጥ መስመር መጎንተል ነው። እሱ ነገር ነውር ነው። ይሄም ያስቀስፋል። ጡዘታም አርፈህ ተቀመጥ። የቆንጅዬ ልጁን ፎቶ ፕሮፋይል ፒክቸር አድርጎ የለጠፈን የ60 ዓመት አባት ሴት መስላህ ስትለፋደድ ፈጣሪ ያሳይህ። የ4 ልጆቹን እናት ፎቶ የለጠፈን ባል በውስጥ መስመር መጨቅጨቅ ምን የሚሉት ሰገጤነት ነው? ይሄ ፍጥጥ ያለ ዐመዳም 100 ኪሎ ፋርነት ነው። አጠገብህ ያለችውን አብሮ አደግህን ልከፍ፣ ጀንጅን፣ ጥበስ፣ አግባ፣ ውለድ፣ ብዛ ተባዛ። መሬት ላይ አጠገብህ ያለች ሄዋንን መጀንጀን እና መጥበስ ያቃተህ ገልቱ በአየር ላይ የማታውቀውን ሰው ፎቶ አይተህ መሳፈጥ ምንሼ? ሃኣ…? እረፍ አንት ነውረኛ።

"…በተረፈ በእኔ መንደር ጠዋት ጠዋት ማንኛውም ሰው በተለይ ኦርቶዶክሳዊ የተዋሕዶ ልጅ፣ እኔን በግሌ ይጥላኝ ይውደደኝ ለደንታው ነው እግዚአብሔርን ማመስገን ግን ግዴታው ነው። ሃይሃይ፣ ኬፍኬፍ፣ ሰላምነው? እንዴት ነህ? ፒስነው? የሚሉ የእግዚአብሔርን ክብር የወሰዱ መጤ ቃላትን ለማስወገድ እና የቀደመውን የእግዚአብሔርን ክብር ለመመለስ ሲባል ጠዋት ጠዋት የጀመርነውን እግዚአብሔር ይመስገን የሚለውን ዘመቻም አጠናክረን መቀጠሉ ግድ ነው። ግድ ነው አልኳችሁ ግድ ነው። ምንአባክ እንዳትሆን። እግዚአብሔር ይመስገን ብለህ በመጻፍህ ይሄ አመዳም ሌባ ጣትህ እንዳይቆረጥ ነው። ወጨበሬያም።

"…ይሄ ግዴታ ግን እስላም ጓደኞቼን አይመለከትም። ከፈቀዱ እነሱ የእኔዎቹ እስላሞች ለመጽሐፍ ቅዱሳዊው ጥቅስ ሳይሆን ለሰላምታው አላህምድሊላህ ማለት ይችላሉ። መብታቸውም ነው። ፅንፈኛ ጴንጤ፣ ፅንፈኛ የወሃቢይ እስላም ቢል ባይል ግን ለደንታው ነው። እሱ ስድና ልቅ አፉን ጦመኛ አድርጎ አርፎ ቁጭካለ በቂ ነው። የህወሓት ዲቃሎች፣ የኦነግ ፈዳሎች፣ የብልፅግና ኩሊዎችም እግዚአብሔር ይመስገን ይሉኛል ብዬም አልጠብቅም። በፔጄ የሚበዛው የወሬ ጠኔ ያለበት ራብተኛ እንደሆነም አውቃለሁ። እኔ ከብዙው የወሬ ራብተኛ ይልቅ ጥቂት ተመሳሳይ ላባ ካለን ወዳጆቼ ጋር መብረርን እመርጣለሁ። ይኸው እየበረርኩም ነው። ለአንድ የእግዚአብሔር ሰላምታ 5ሺ ሰው ማግኘት ቀላል የሚመስለው ካለ ሞክሮ ያሳየኝ። ይሄ ፈቃደ እግዚአብሔር ነው። የትንሣኤውን ልጆች መለያ ጊንጊልቻ ነው።

"…እኔ ከእኔጋር መብረር፣ መጓዝ የሚችሉትን ጠዋት ጠዋት በእግዚአብሔር ሰላምታ እያጠራሁ፣ እየለየሁ እጓዛለሁ። ለእኔ እነዚህ አመስጋኞች ለእኔ ዋሴ፣ ጠበቃዬ፣ አማላጆቼም ናቸው። እንዲህ በኃጢአት እንደተጨማለቅኩ እንኳ ብሞት እነዚህ ጠዋት ጠዋት አምላኬን ስሙን ጠርተው እግዚአብሔር ይመስገን ብለው በድፍረት፣ ሳይሳቀቁ፣ ሳይኮሩ፣ ሳይኩራሩ፣ በደስታ የሚያመሰግኑቱ ጓደኞቼ ይዋሱኛል። ጠበቃም ይሆኑኛል። ምንአልባት ገንዘብ የማገኝበት የሚመስላቸውና ዘመድኩን ሀብታም ይሆናል ብለው ለሰላምታው ምላሽ
3.5K views14:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 11:10:50
"…እግዚአብሔር ዓለቴ አምባዬ መድኃኒቴ ነው፤ እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፥ በእርሱም እታመናለሁ፤ ጋሻዬና የረድኤቴ ቀንድ፥ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ፥ መድኃኒቴ ሆይ፥ ከግፍ ሥራ ታድነኛለህ። ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ ከጠላቶቼም እድናለሁ። 2ኛ ሳሙ 22፥ 2-4 “…ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።” 2ኛ ቆሮ 9፥15

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
2.6K views08:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 22:21:28
"…ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር …!!

"…



"…https://rumble.com/v2a54fi-mereja-tv-live-broadcast.html

"…ለመዘግየታችን ይቅርታ እየጠየቅን ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በመረጃ ቲቪ እመጣለሁ ነው። ሰብሰብ ብላችሁ ጠብቁኝማ። ኣ

• ያ ሳምንት ያበጠው ነገር ዛሬ እናፈነዳዋለን። አከተመ።

"…ሻሎም !  ሰላም !
4.2K views19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 18:47:35
አጀንዳዬን አልቀየርኩም…!

"…ነገን የሥራ ቀኔ አድርጌ ዛሬ በዕለተ ሰንበት ይሄን የሃገርና የቤተ ክርስቲያን ሸክም ቆሻሻ ኮተታም ክፍትአፍ ላጽዳው ብዬ ነው። በነገራችን ላይ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባራዋለች። መንፈሳዊ ኮሌጁ ተማሪዎች አጠገብ መድረስ የሌለበት የመርዝ ዕቃ ነው ብሎ አስወግዶታል። በመጥፋቱ ሊጸለይለት የሚገባ ሰው ቢሆንም ልቡሰ ሥጋ አጋንንት ስለሆነ ለመርዳት አይመችም። እንደ እኔ እሱን ወደ ቀልቡ ለመመለስ የደከመም የለም።

"…እደግመዋለሁ ዘሪሁን እውነተኛ ስሙ አይደለም። ስሙ ሰውበሰው እንጂ። ወላጅ አባቱ ሙላቱ አይደለም። ተጫነ (ቂጠታ) እንጂ። አያቱም ግዛው አይደሉም። አቶ በለጠ እንጂ። የዘሪሁን እናት አመለወርቅ በለጠ አባቱም ተጫነ በለጠ ነው። ተጫነ (ቂጣታ) በለጠና አመለወርቅ በለጠ ታላቅና ታናሽ ወንድምና እህት ናቸው። ተጫነ ያስረገዘው ታናሽ እህቱን ነው። የተወለደው ደግሞ ዘሪሁን ነው። ለዘሪሁን እናቱ አክስቱም ነች፣ እናቱም ነች፣ አባቱ አጎቱም ነው አባቱም ነው። አቶ በለጠ ለዘሪሁን አያት፣ ለእናቱና ለአባቱ ደግሞ አባት ናቸው። ወሊሶ ጠጅቤት ተረገዘ ዝዋይ ተወልዶ አደገ።

"…ጎጃምን፣ ጎንደርንና ትግሬን አምርሮ ይጠላል። ወሎ የአሳዳጊ አባቱ የአቶ ሙላቱ ግዛው፣ የአቢይ አህመድ፣ የዳንኤል ክስረት፣ የደመቀ መኮንን፣ የገዱ ሃገር ስለሆነ አይነካውም። እሱ በተለይ ጠላቱ ሦስቱ ናቸው። ከዚህ ተነሥቶ ነው ከገዳ ባንኩ ዋሲሁን ከቃልቻሙ ልጅ ጋር ሆነው የምዕራብ ሸዋ የአድአበርጋ የኦሮሞ የሸዋ ሲኖዶስ ወደ መመሥረት የሄደው። አባ ተክለሃይማኖት ወልዱንም ያሳሳተው ይሄ ሰው ነው። ዘሪሁን ላይ የፈረደበት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምላክ ነው። የእሱ ሃሳብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አፍርሶ እሱ ጠፍጥፎ በሠራቸው ሸርሙጣ ጳጳሳት በኩል ሊበላ ነበር። አፈር ከደቼ ይብላና።

•ድርጅቱ።
5.1K views15:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 17:40:45
"…መጀመሪያ ስለፎቶዋ ምላሽ ልስጠው።

"…ሰውበሰው ተጫነ (ቂጣታ) በለጠ በአሳዳጊ ወሎዬ አባቱ ዘሪሁን ሙላት ተብሎ የሚጠራው ርጉም ይሄን ፎቶዬን ያመጣው ጸበልተኛ እንደሆንኩ ለማሳየት እና ለፀበል ቤት ከቀረበ ብሎ ማምጣቱ ነው። በእሱ ቤት እኔን ማዋረዱ ነው። ታምሜ ፀበል ከሄድኩማ አማኝ እኮ ነኝ። ሳንቲም እያለኝ፣ ሃኪምቤት፣ ሳይንስን ንቄ ፀበል ከገባሁ እኔ እምነቴ እስከአሁን ተፈጥሮአዊ ነው ማለት ነው። ሜካፕም ኬሚካል፣ ማዳበሪያም አልነካውም ማለት ነው። ታድዬ።

"…ፎቶውን የተነሣሁት ደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ነው። ቦታው ደግሞ ሮቢን ደሴት ነው። ቤቷ ደግሞ ታላቁ የነፃነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ የታሰረባት ጠባቧ እስር ቤት ናት። ከጀርባዬ ባለው እስር ቤት ውስጥ የሚታየው ፍራሽ መኝታው፣ የመመገቢያ ሰሃን፣ ትንሽዬ ኮመዲኖ ነው ያለበት። እናም እኔም እድሉ ደርሶኝ አጋጣሚውን አግኝቼ ስጎበኘው ለማስታወሻ የተነሣሁት ፎቶ ነው።

"…የሄድኩት ደርባን ማርያም ቢሆንም ኬፕታውንን መጎብኘት አለብህ ብሎ ወጪውን የቻለኝ ወንድሜ ደጉ ስሜነህ ነው። ደጉ ለእኔ ብቻ ሳይሆን አብሮኝ ለነበረው ለወንድሜ ተሼ ከነልጁ የአውሮጵላንም ሌላሌላውንም ወጪዎች ችሎን ነው የሄድኩት። እናም እጅግ ደስተኛ ነበርኩ። ፎቶውን የለጠፍኩትም እኔው ነኝ፣ የፎቶውም ታሪክ ይሄው ነው።

"…እንዲያውም ዛሬ ሰንበት ነው በዚያውም እግረመንገዴን በደቡብ አፍሪካ በኬፕታውን የነበረኝን አይረሴ ቆይታዬን ለምን በፎቶ ጭምር አላስጎበኛችሁም። ሰውበሰው ተጫነ (ቂጣታ) በለጠም በዚያውም ፎቶዎቼን እያየ እሳት የጎበኘው ላስቲክ ለምን አላስመስለውም። ማርያም አዛኜን አትችለኝም። ከነከስኩ ሳላደማ እንደማልፋታ ቀልብህም፣ ውቃቢህም ሁሉ እንደሚያውቅም ታውቃለህ። አልፋታህም።

"…Incest ታም…!
5.0K views14:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 17:02:26
ሰውበሰው ደግሞ ጠራኝ… ልግባለት እንዴ…?

"…ይሄ ከኋላ ከጀርባ ፊት የመሰለ ገባጣ የብልፅግና የጎባጣ አሽከር የሆነ ሰውዬ ዛሬም አላረፈም አሉኝ። የሌለ ወብርቶ በፉጨት እየጠራኝ ተቸገርኩ እኮ። ምንይሻለኛል በማርያም። እንደምንም ተቸግሬ በስሱ ልግባለት እንዴ…?

•እኔኮ ሰንደል በቀኝ ጆሮው፣ አሪቲ በግራ ጆሮው ሰክቶ የጫት ገራባ በብቱ ይዞ ዶሮ ማነቂያ ለዶሮ ማነቂያ እንዳይንከራተት አስቤለት እንጂ… አንድም ንስሀ እንዲገባ የወንድ በር እየሰጠሁት ነው እንጂ በስሱ የምምዠርጠው አንዴ ዠለጥ ዠለጥ አድርጌ ሳይለት ሞድ ላይ ማድረግ አቅቶች አይደለም። ይሄንን ደግሞ ራሱ ሰውበሰው ይመሰክርልኛል።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=pfbid0bFRd8nJbge2QuvADvTZBxuWn8SL1YQhwvPRXferjUontyVmgQUHv1YGUsn8BL8VXl&id=100075787128315

• በፉጨት ጠርቶኛል ልግባለት ወይስ ይቅር…? እናንት ጓደኞቼ እንዳላችሁ…!
4.7K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 17:02:26
መጠንቀቅ አይከፋም…!

"…የቻይና ኤንባሲ ወፎቼ የቻይና መንግሥት በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ፣ ለሚሠሩ፣ ወይም ለጉብኝት የሚሄዲ እንዲህ የሚል መልእክት የቴሌግራም ቻናል ከፍቶ ማስተላለፉ ተሰምቷል። ብልጥ ከጎረቤቱ ይማራል።

对于因各种原因在埃塞俄比亚工作、访问、生活的中国公民,2023年3月2日至2023年3月12日期间,在埃塞俄比亚治安保障不牢靠,我们已严令禁止外出。 中国驻埃塞俄比亚亚的斯亚贝巴大使馆

For Chinese citizens who work, visit, or live in Ethiopia for various reasons, from March 2, 2023 to March 12, 2023, the security guarantee in Ethiopia is not secure, and we have strictly prohibited them from going out. Chinese Embassy in Addis Ababa, Ethiopia

"…ለቻይና ዜጎች… ከመጋቢት 11 ቀን 2023 እስከ መጋቢት 21 ቀን 2023 ዓም በተለያዩ ምክንያቶች በኢትዮጵያ ለሚሠሩ፣ ለሚጎበኟቸው ወይም ለሚኖሩ የቻይና ዜጎች በኢትዮጵያ ያለው የደህንነት ዋስትና አስተማማኝ ስላልሆነ ወደ ውጭ እንዳይወጡ በጥብቅ ከልክለናል። 

የቻይና ኤምባሲ
በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
4.6K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 14:22:27
አሸባሪው…!

"…ፖሊሶች አንድ እየከነፈ የሚሄድ የራይድ ታክሲ ለፍተሻ ያስቆማሉ። በታክሲው ውስጥም ይሄ አደገኛ አሸባሪ ነበር ከነሽብር ዕቃዎቹ የተገኘው። ኋላላይ በምርመራ እንደተረጋገጠው አሸባሪው ከእነ ቢንላደን ጋር ሁሉ ይገናኝ የነበረና ምድር የምትሽከረከርበትን ዛቢያ ሊሰብር የሚችል ፈንጂ በፌስታል አጭቆ መያዙ ነው የተነገረው።

"…ኑረዲን መሀመድ ይባላል። በልብስ ስፌት የሚተዳደር ኢትዮጵያዊ "አሸባሪ" ነው። ለብዙ ዘመናት ሳይታወቅበት ሃገር ሲያሸብር ኖሮ ሰሞኑን ነው ቀን ጥሎት በጀግናው የኦሮሞ ብልፅግና ሠራዊት ልዩ ኦፕሬሽን በቁጥጥር ስር የዋለው።

"…ለኦሮሞ ፖሊሶች ምስጋና ይንሳቸውና ይሄን አዲስ አበባን ሳያወድማት በፊት ለሽፋን በልብስ ስፌት ሙያ የሚተዳደረውን "አሸባሪ" ይዘው በአሁኑ ሰዓት ማዕከላዊ አስገብተው ቶርች ገልብጠው እየለጠለጡትና ግብረአበሮቹን እንዲጠቁም እያውጣጡት መሆኑ ታውቋል። ኑረዲን በምርመራው ወቅት "ድርጊቱን ያመነ ሲሆን" ከመርማሪ ፖሊሶቹ መካከል አንዱ የወንጀል ድርጊቱን እንዲህ ሲል ገልጿል።

"…ስሟ ለጊዜው ያልተጠቀሰ አንዲት "አሸባሪ" የሴት ዲዛይነር ለ"አሸባሪው" ልብስ ሰፊ ለኑረዲን በሠራቻቸው ጨርቆች ላይ MNTAad12w7 (ሚኒሊክ ጣይቱ ዓድዋ 127ነው አሉ የፈንጂው ስም) ጥልፍ ሠርቶ እንዲሰጣት ትዋዋላለች። ኑረዲንም ጥልፎቹን ሠርቶ ሊያቀብላት እየሄደ ሳለ ነው በቁጥጥር ስር ያዋሉት። ኤትአባታቸው… እሱም እሷም።

"…በአሁኑ የኦሮሞ አስተዳደር ዘመን ዐፄ ምኒልክ ስመጥር የቅኝ ገዢ አውዳሚ ድማሚት መሆናቸው እየታወቀ አሸበርቲዎቹ ኑረዲንና ዲዛይነሯ ምስላቸውን ይዘው በመገኘታቸው ፍርድ ቤት በስቅላት ይቀጣቸዋል ተብሎም ይጠበቃል። የአሸባሪዎቹ ፎቶ ባይደርሰኝም በቁጥጥር ስር የዋለው አደገኛው ፈንጂ ግን የምታዩት ቲሸርት መሆኑ ታውቋል።

• እየተሸበርነ…!
4.9K views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 13:03:42
ከምስጋና በኋላ…

"…3 ሺ ሰው አመስግኗል። አይሞላም ብዬ ስዘናጋ እንደውም 700 ሰው ጭማሪ አሳይቷል። ተመልካች ሁሉ በድፍረት እግዚአብሔር ይመስገን ማለት የጀመረ ይመስለኛል። በእውነት ደስስ ይላል እግዚአብሔር ይመስገን። እንግዲህ ዛሬ እለተ ሰንበትን እንዲሁ እየተጨዋወትን የማታው "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" የሚለው የመረጃ ቲቪ መርሀ ግብሬ እስኪጀምር ድረስ አብረን እንቆያለን።

"…የዛሬውን የእለተ ሰንበት መርሀ ግብሬን ምጀምረው በቅርቡ መላዋን አዲስ አበባ ሊያጠፋ የሚችል MNTAad12w7 የተባለ አደገኛ ፈንጂ ይዞ ጥፋት ሳያደርስ በኦሮሚያ ፎሊሶች በቁጥጥር ስር ስለዋለ በሃይማኖቱ የእስልምና እምነት ተከታይ ስለሆነ አሸባሪ ሶዬ ሰበር ዜና ነው። እናም ጠብቁኝ። መረጃውን ላደረሱኝ ፖሊሶችም ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው።

"…ጠብቁኝ ቆይቼ እመለሳለሁ።
4.9K views10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-05 11:03:37
"…እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ማዳኔ ሊመጣ ጽድቄም ሊገለጥ ቀርቦአልና ፍርድን ጠብቁ ጽድቅንም አድርጉ። ይህን የሚያደርግ ሰው ይህንንም የሚይዝ የሰው ልጅ፥ እንዳያረክሰው ሰንበትንም የሚጠብቅ እጁንም ክፋት ከማድረግ የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።

"…እግዚአብሔር ሰንበቴን ስለሚጠብቁ ደስ የሚያሰኘኝንም ነገር ስለሚመርጡ ቃል ኪዳኔንም ስለሚይዙ ጃንደረቦች እንዲህ ይላልና፦ በቤቴና በቅጥሬ ውስጥ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች ይልቅ የሚበልጥ መታሰቢያና ስም እሰጣቸዋለሁ፤ የማይጠፋም የዘላለም ስም እሰጣቸዋለሁ።” ኢሳ 56፥ 1-5

“…የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ።” ዘጸ 20፥8 “…ደግሞ፦ ሰንበት ስለ ሰው ተፈጥሮአል እንጂ ሰው ስለ ሰንበት አልተፈጠረም፤” ማር 2፥27 ማቴ 12፥8 “…ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤” ማቴ 24፥20 

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
5.1K views08:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ