Get Mystery Box with random crypto!

....

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemdkunbekelez — .... Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemdkunbekelez — ....
የሰርጥ አድራሻ: @zemdkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 27.66K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው።
ይህ የዩቲዩብ ቻናሌ ደግሞ ሰኔ 6/2012 ዓም ከራየን ወንዝ ማዶ የተከፈተ ነው።
https://www.youtube.com/c/ZemedkunBekele?sub_confirmation=1
እንደ ፌስቡክ፣ እንደ ቴሌግራሙ ሁሉ በዚህ መንደርም ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክ ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 138

2022-08-31 10:35:42 "…ትግሬም ኦሮሞም ሁለቱም ከኢትዮጵያ መጋዘን ባገኙት መሣሪያ ታጥቀው፣ ከኢትዮጵያ ባንኮች ባገኙት ገንዘብ ደምቀው ነው ዛሬ እንዲህ አምሮባቸው ዊኒጥ፣ ዊኒጥ የሚሉት። እናም አሜክስዬ መጀመሪያ መልክህን፣ አሰላለፍህን አስተካክልና ቆንጆ ሁን። ዱንቡሽብሽ፣ ለማለት፣ ቦምቦሊኖ ለመምሰል። ኡሙንዱኖኢሹ ለመባል መጀመሪያ የጎጠኝነት፣ የመንደርተኝነት ቅጭጭትህን ታጠብ። አንድ አማራ ሁን። ቡራቡሬ ዜብራ ቀለምህን አስወግድ። ማድያትህን አጥፋ። ከዚያ ለሙያው ከጎረቤቶችህ ልምድ ትወስዳለህ። ከጎፈንድሚም አትጠብቅ።

"…አትሽሽ። መከላከያው ስለሸሸ አትሽሽ። ሸሽተህስ ተከትለውህ ከመጡ የት ይለቁሃል። ውርደቱ፣ ስቃዩ፣ እንግልቱ እንደው አይለቅህ። በአጭር ደስታ አትዘናጋ፣ በአጭር ችግርም አትፈታ። የዘመናት ልምድህን ተጠቀም። በመንደር አለቃ፣ በጎበዝ አለቃ ሃገር ያጸናህ መሆንህን አስታውስ፣ ድሮም ዛሬም አንተን ከፈጣሪህ በቀር ምድራዊ ሃይል አንተን የሚረዳ እንደሌለ ዕወቅ። ድሮም አባቶችህ መድኅናቸው፣ አምባ መጠጊያቸው የሰማይ የምድር ፈጣሪ ልዑል እግዚአብሔር እንጂ የትኛውም ሃገር እንዳልነበርም ዕወቅ። ተረዳ። የውስጡንም፣ የውጩንም ጠላትህን ለማሸነፍ መልክህን አንደወጥ አድርገው።

"…ይኸውልህ በወሎ በኩል ብቻ ወረውህ አይቆሙም። አይረኩም። በጎንደርም፣ በሸዋም፣ በጎጃምም መሞከራቸው አይቀርም። ይሄን ሁሉ መቋቋም የምትችለው አንድ ስትሆን ብቻ ነው። ማን አንድ ያድርገን አትበለኝ። አንድ የሚያደርግህን ጀግና አምጠህ ውለድ። የራስህን ቼጉቬራ፣ በላይ ዘለቀ፣ ንጉሥ ሚካኤል፣ ቴዎድሮስና ምኒልክ እህህ ብለህ አምጠህ ውለድ። አምጥ አልኩህ። ለአንተ ከአንተ በላይ መድኃኒት፣ መፍትሄም የሚሰጥህ የለም። መድኅን ከሌላ ስፍራ አትጠብቅ። የራስህን ጀግና ራስህ አምጠህ ውለድ።

"…መሪ እንደሌህ ዐውቃለሁ። መሪ ይወለዳል። መሪ አምጠህ የምትወልደው አንተው ነህ። መሪ ውለድ። ሀሰን ከሪሙ፣ ምሬ ወዳጆ የሰበሰቡትን ኃይል እያየህ አይደል? ከነችግሩ፣ ከነ ሴራው፣ ከነ ተንኮሉ እሱን ታግሰው እኮ ነው ዐማሮች የተሰባሰቡት። አዎ ተሰባሰብ። ይሄ የወሎ ጉዳይ ነው አይመለከተኝም አትበል። ወሎን ካለፈ ጎንደርም፣ ጎጃምም፣ ሸዋም እኮ ይፈታል። አንድ ሁን። የዐማራ ጭንቅላቱ፣ ራሱ አንድ ነው በል። አንድ ዐማራ ለሁሉም ዐማራ፣ ሁሉም ዐማራ ለአንድ ዐማራ በል። ይሄ የእለተ ረቡዕ የጠዋት ምክሬ ነው። የቀረውን ቀኑን ሙሉ ስንወያይ እንውላለን።

#ማስታወሻ፦ የምሥራቅ ዐማራ ፋኖ ትክክለኛ የባንክ አካውንት ካለ ይሰጠኝ። የስልክ ቁጥራቸውም ጭምር። በውጭ ሃገር ታማኝ የዐማራ ወኪል ካላቸውም የጎፈንድሚ ይከፈትና እኔም የበኩሌን በትበት ልበልላቸው። አሁን ለምሥራቅ ዐማራ ፋኖም፣ የዐማራ ልዩ ኃይልም፣ ሳይሸሽ ከሁለቱም ጋር እየመከተ ላለው ወታደር የሚያስፈልገው ድጋፍ ነው። ምግብ ከሌለ እንዴት ሊቋቋመው ይችላል?

"…ወዲህ በሉ የምሬ ወዳጆና የሀሰን ከሪሙን የፋኖ አካውንት…!!

• ቆይቼ የአስተያየት መስጫውን ሳጥን ሰንዱቁን እከፍተዋለሁ። በጨዋ ደንብ ትወያያለህ። እምቢ ብለህ ክፍት አፍን እከፍታለሁ የምትል ካለህ አጠናግሬ እልክሃለሁ። ከዚያ በሌላ ሲም ካርድ ትከታተለኛለህ።
5.5K views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:35:42 "መልክ ከቤት ሙያ ከጎረቤት !!

• ጦማሯ ረጅም ናት። ርዝመቷ ግን በስልክ ስታነቧት ነው። ጨክናችሁ ውኃ እየተጎነጫችሁ፣ እያዛጋችሁ፣ እየተንጠራራችሁም፣ እያፋሸካችሁም ቢሆን እንደምንም አንብቧት። መልካም ንባብ።

"…ወዳጄ መጀመሪያ መልክ ከቤት ይስጥህ እንጂ ሙያውን ከጎረቤት ትማረዋለህ። ይሄ ደግሞ በጣም ቀላል ነው። ሙያ ከጎረቤት ለመማር ወጪ አይጠይቅም። አያደክምም። ምርምርም የለበትም። ለዐማራ በአሁን ሰዓት የሚያስፈልገው መልክ ነው። የሚወደድ፣ የሚስብ፣ ሸጋ የሆነ መልክ። በፌር ያልተነካካ፣ በኬሚካል በቀለም ያላበደ መልክ። መልክ ስልህ አይን፣ ቅንድብ፣ ከንፈር፣ ደረት፣ ዳሌ፣ ሽንጥ፣ ተረከዝ፣ ቁርጭምጭሚትና አገጭ እያልኩህ አይደለም። መልክ የምልህ ዐማራዊ መልክ። ሸዋ፣ ወሎ፣ ጎንደር፣ ጎጃም ሳይሆን አንድ ዐማራዊ መልክ። ልክ እንደ ትግሬ፣ ልክ እንደ ኦሮሞ ወንድም ጎረቤቶችህ ያለ መልክ። አዲግራቴ፣ ዓድዋ፣ ሽሬ፣ መቀሌ የሚል ታርጋ የተለጠፈበት መልክ ሳይሆን አንድ ትግሬ የሚሉት አይነት መልክ። ወለጋ፣ ባሌ፣ ጅማ፣ ሰላሌ፣ አሩሲ፣ ኢሉአባቦራ፣ ሀረርጌ፣ ሆሮጉዱር ሳይል አንድ ኦሮሞ ይሉት አይነት መልክ ይዞ አንድ ላይ ለጋራ ዓላማ እንደቆመው እንደ ኦሮሞ አይነት ይኑርህ እንጂ ሙያውን ከጎረቤት ትማረዋለህ። መልኩ ካለህ ሙያው ቀላል ነው ከጎረቤት ይቀሰማል። ይለመዳል።

"…አንዳንድ ዐማሮች እኛ እኮ በፋኖነት፣ በልዩ ኃይልነት ብንሰለጥንም መሣሪያ ግን የለንም። በምን ሠርጋችንን እናደምቃለን። ገንዘብም እኮ የለንም ሲሉ ተደብቄ እሰማቸዋለሁ። እውነት ነው ሁለቱም ላይኖርህ ይችላል። መጀመሪያ ግን መልክ ይኑርህ፣ ሰልጥን፣ በኮባም፣ በከዘራም ሰልጥን። የዐማራ አንገቱ አንድ ይሁን እንጂ ቀለብህንና መሳሪያህን የምታገኝበትን ሙያ ከጎረቤቶችህ ትማራለህ። ልምድም ትወስዳለህ። ልምድ መውሰድ እኮ ግሩም ነው። ተዘርፍጠህ፣ ተጎልተህ ተቀምጠህ መልክ ብቻ ይዘህ ሙያ ከሌለህም ዋጋ አይኖርህም። ቆሞ ቀር ሆነህ ትቀራለህ። ኧረ ጋሽ መልኬ ከጎረቤትህ ሙያ ተማር እንጂ። እህዕ? ኦነግ ገንዘብ ከየት እንዳገኘ ጠፍቶህ ነው? ሳትሰማስ ቀርተህ ነው?

"…ጃፓን እንዴት አደገች ብለህ ሩቅ ሠፈር ብትሆንም ስለ ጃፓን ሥልጣኔ ካልተመራመርክ፣ ካልጠየቅክ እንዴት ታድጋለህ? ጩጬ ሆና ሳለ እስራኤል እንዴት ጉልቤ ሆነች ብለህ ካልጠየቅ እንዴት ይገባሃል? ስለ ፑቲን የህይወት ታሪክ ሳታጠና ስለ ጃልመሮም፣ ስለ ደጺም ሳታውቅ እንዴት ፎለቲካው ይገባሃል? እህእ… መልክ ቢኖራቸውም ሙያ ስለሌላቸው ሃገር አልባ ስለሆኑት ኩርዶች እንዴት ሃገር አልባ እንደሆኑ ከወዲሁ ካልተማርክ ምን ዋጋ አለህ? አዎ መጀመሪያ መልክህን አንድወጥ አድርገህ አሳምር። ሙያው አለህ ባይኖርህም እንኳ ከጎረቤቶችህ ትማራለህ። ደግሞም ተማር። አትስነፍ።

"…ኦነግ ሸኔ እንዴት መልኩን አሳመረ ብለህ መጀመሪያ ጠይቅ? ቀጥሎ ገንዘብ ከየት አመጣ ብለህም ጠይቅ። ኦነግ ሩቅ እኮ አይደለም። በመርከብ አትሄድ፣ የሮጲላ ትኬት አያስቆርጥ፣ ቪዛ አያስጠይቅ፣ ቅርብ እኮ ነው ግድግዳችሁ አንድ የሆነ ጎረቤትህ እኮ ነው። ሳትሰንፍ ጠይቀው። እንዴት ገንዘብ አገኘህ ብለህ ጠይቀው። እሱ ባይነግርህ ግን እኔ እነግርሃለሁ። አንዳንድ ሰው ምቀኛ ነው። አይነግርህም። የምትበልጠው ይመስለዋል። ይኸውልህ ኦነግ ዲታ የሆነው ወደ 23 የሚጠጉ የኢትዮጵያ ባንኮችን በሃላል ዘርፎ ነው። እነ ዐቢይ አሕመድ፣ እነ ሽመልስ አብዲሳ ያስታጠቁት በዚህ መልክ ነው። ያውም የአንተው ገልቱዎች ደመአ መኮነን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ተመስገን ጡሩነህ፣ ዳግማዊት ሞገስ፣ አገኘሁና ላቀ አያሌው እያዩ ነው ፈረንካ ከባንክ የወሰደው። እነ ግብፅ፣ ዓረብ ሃገራት፣ ለኪስ ከሚሰጡት ውጪ በተጨማሪ ነው ኦነግ በላቡ፣ በጉልበቱ፣ በትበት ብሎ የታጠቀው። ይኸውልህ መጀመሪያ አንድወጥ ዐማራዊ መልክ ይኑርህ እንጄ ሙያ ከጎረቤት ነው መማር የምልህም ለዚህ ነው። ይሄ ሌብነት አይደለም። ይሄ በመሪዎች ቡራኬ ለኦነግ የተበረከተ ስጦታ ነው። ጥሎሽ ጭምር ነው። መሪዎች ልጆቻቸውን በዚህ መጠን ደብዳቤ ጽፈው ሰጥተው ሲያደራጁ ደስ ይላል።

"…ወያኔንም ተመልከት። መጀመሪያ ብጥስጥስ ያለውን መንደሬነት፣ ዓድዋ ሽሬ፣ አክሱም፣(ዓሽዓ) ነትን አጠፋች። አዲግራት፣ መቀሌነትንም አጥፍታ አንድ የትግሬነት መልክ ፈጠረች። መልኳን በአደስም፣ በደንደስም አሳመረች። አነ ትግራዋይ፣ አነ ተጋሩ የሚል መፈክርም ፈጥራ በዚያ መፈክር ጥላ ስር ሁሉንም ኮሎኮለች። ትግርኛ አቀላጥፎ ይናገር እንጂ ለሌላው ደንታ አልነበራትም። ወሎዬው ጌታቸው ረዳን፣ ጎንደሬውን አሉላ ሰለሞንን ፈረንካ፣ ሴትና ቡሌ አቅርባ በግድ የትግሬ መልክ አሰጠች። አንዴ ተጋሩ፣ አንዴ ባትጋሩኝ፣ እያለች ቆይታም ትግራዋይ የሚል ማንነት ፈጥራ መልኳን አንድወጥ አድርጋ አሳምራ አሰለፈች። የሚቀረው ሙያ ነበር። ሙያውን ከየት እንደተማረች ባይታወቅም ከመጀመሪያው ከመነሻዋ ባንክ በመስበር የጀመረችውን የሌብነት ሙያ አሳድጋ ለትንሽ ጊዜ የኢትዮጵያ ዕድር ሊቀመንበር በነበረች ጊዜ እድሩን ሠርቃ ከበረች። ከኢትዮጵያ ዕድር የቀራት አልነበረም ነው የሚባለው። ማንኪያ ነሽ፣ መርከብ ነሽ፣ ሮጲላ ነሽ። የቀራት አልነበረም። መከላከያውን ከነነፍሱ ትግሬ ምድር ወስዳ ተከለች። ልጆቿን በሙሉ በኢትዮጵያ ዕድር ስም በምታመጣው ብድር እና ዕዳ ዲታ አስደረገች። የኢትዮጵያን ዕድር ዘርፋ፣ በኢትዮጵያ ዕድር ሃብት፣ በኢትዮጵያ ብድር እና ዕዳ እስከ አፍንጫዋ ድረስ ታጠቀች። ግምጃ ቤቷም፣ ሊቀመንበሯም እርሷ ስለነበረች እናም ዛሬ በሰፈሩ ውስጥ እምቡር፣ እምቡር፣ ዊኒጥ፣ ዊኒጥ ስትል ትታያለች። እንዲህ በትበት ብላ ነው ወዩሂዊ ዛሬ ድረስ በቀረርቶም፣ በፉከራም እንደ ቄብ ዶሮ የምታስካካብን። መልክ ይኑርህ። አንድወጥ መልክ ይኑርህ።

"…እደግመዋለሁ እናም ዐማራ መጀመሪያ መልክ ይኑርህ። በደንብ ታጠብ። ይሄን የጎጠኝነት፣ የሰፈር፣ የመንደር ማድያትህን ፈግፍገህ አስለቅቅ። ዐማራ የሚለውን አንድ የሚያደርግህን ቅባት ደጋግመህ ተቀባ። በአናትህ ላይ ከተቀባኸው ወደ ውስጥህ ዘልቆ ይገባል። አትዘበራረቅ፣ እኔ ጎንደሬ የቴዎድሮስ ልጅ፣ እኔ ወሎዬ የንጉሥ ሚካኤል፣ እኔ ጎጃሜ የበላይ ዘለቀ፣ እኔ ሸዋዬ የምኒልክ ዘር እያልክ አራት ቦታ አትሰንጠቅ። አራት ቦታ ቆመህ አታቅራራ። በአንድ ላይ ፎክር፣ በአንድ ላይ አውራ። በአንድ ላይ ተነሥ። በአንድ ላይ ዝመት፣ በአንድላይ ድል ታደርጋለህ። የጎጥ ጭቅቅትህን በደንብ ታጥበህ ልክ እንደጎረቤትህ እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ዐማራዊ መልክህን አሳምር። ኦሮሞ ከባሌ አምጥቶ ሰላሌ ላይ ሰው ሲሾም ሰላሌ ኦሮሞ ተሾመ እንዲባል እንጂ የባሌ ሰው መጣብኝ እንዳይል ነው የደረጉት። አንተም ከእሱ ተማር። የሆነ ሰው ሲሾም ዐማራ ይሁን እንጂ የእኔ ሰፈር ሰው አይደለም ብለህ አትወብራ። መልክህን አሳምር። ሙያም ከጎረቤት ተማር። ትግሬም እንደዚያው ነው። ዓድዋ በሙሉ ትግሬ ላይ ሲሾም ትንፍስ የሚል የለም። ተማር ከትግሬ። ተማር ከኦሮሞ።
5.0K views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:03:35
"…ከዋግኽምራ… !!

"…በስም የተጠቀሳችሁ ባንኮች በሙሉ በከተማዋ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር ሳይገጥም፣ ከ70 ሺ በላይ ስደተኛ ባለባት ከተማ ባንኩን ዘግታችሁ ወደ አዲስ አበባና ባህርዳር የፈረጠጣችሁ ነውረኞች በአስቸኳይ ወደ ክልሉ መጥታችሁ አገልግሎት መስጠት እንድትጀምሩ ተብላችኋል…!! ይሄ ደስ ይላል…!!

"…ላሊበላ፣ ወልድያ፣ መርሳ፣ ሃይቅ፣ ኮምቦልቻ እና ደሴም እንዲህ አይነት ወንድ ከንቲባ ቢኖራቸው ብዬ ተመኘሁ። ምኞት ነው።

"…እየተመኛችሁ…!!
2.3K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 18:03:35
አዲስ አበባ…!!

"…የኖህ ዘመንን ይመስላል ዘመኑ። የጥፋት ውኃ እስከአንገቱ እየደረሰ የሚጨፍር፣ የሚዘሙት ትውልድ የነበረበትን የኖህ ዘመን ይመስላል።

"…የኦሮሚያ ነፃ አውጪ ግንባሩ (ኦነጎ) ፕሬዘዳንት የኢትዮጵያ ባህልና ስፖርት ሚንስትሩ ኦቦ ቀጄላ መርዳሳ፣ የአዲስ አበባ ህዝብ ከርሱንም ፈርሱንም ብሎ የሞለጨው ዘሌ፣ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ( በሙሉ ባለሥልጣናቱ ኦሮሞ መሆናቸው ይሰመርበት) የወሎና የትግሬን ሴቶች በሚሊኒየም አዳራሽ ሰብስበው። ለራባቸው ትንሽ አምባሻ ሰጥተው ሲያስጨፍሯቸው ውለዋል።

"…ትግሬና ዐማራ በሰሜን ይጨፋጨፋል። በዚህ ሰዓት ምህላ ይዞ አቤት እግዚኦ እንደማለት የብልፅግና መንግሥት ካድሬ የሆነው የአዲስ አበባ የትግሬና የዐማራ ሴት ቀሚሷን ገልባ አሸንድዬ፣ ሶለል ወለል ትልልኛለች። ኧረ ኤዲያ…!!

"…እነ ቀጀላ፣ እነ አበቤ በሳቅ ፍርስ ይላሉ። የትግሬና የዐማራ ሴት ወጧ እንዳማረላት ሴት ፀጉሯን ተቆንድዳ አሸሼ ትልልኛለች። ደሴ በስደተኛ ተጨናንቋል። ዘመዶቻቸው ጭንቀት ላይ ናቸው። እነዚህ ገተቶች እዚህ ከተማውን በዝላይ፣ በከበሮ የጦዙታል። ይሄኔ እኮ የሆነ ዘመዷ በዚህ ሰዓት እየሞተ ነው።

"…ኩሾች አልተቻሉም…!! በይ ዝለይ የሚዘል አጋንንት እስኪዘልብሽ። ሰው እንዴት ማሰቢያውን እንዲህ ይነጠቃል?

• ይህ ነጭ ነጯን የዘመዴ ቃል ነው። ይህን በማለቴ የሚከፋህ ካለህ በአናትህ ተተከል። ኬሬዳሽ…!!

"…የዐማራና የትግሬ ሴቶች እየዘለላችሁ…!!
2.2K views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:36:03
"…ደሴ ነው። ከቆቦ፣ ከወልድያ፣ ከመርሳ ነቅሎ ወደ አዲስ አበባ ለመትመም በደሴ ማለፊያ አጥቶ የቆመ የመኪና ብዛት ነው።

"…ከህዝቡ እኩል ተተኳሽና ወታደሩን ይዞ የሚሸሸው የብርሃኑ ጁላና የዐብይ አሕመድ መከላከያም ማለፊያ አጥቶ ለአሩሲዋ እመቤት እየተሣለ ነው። ገጭቷቶ ሳያጣምማች ኧረ አሳልፉት በማርያም…!!

"…የዐማራ ልዩ ኃይል፣ የዐማራ ፋኖና የኢትዮጵያ ልብ ያላቸው የአባታቸው ልጆች የሆኑ ጀግኖች የመከላከያ ሠራዊት አባላት ግን እስከአሁን ወልድያን አላስደፈሩም። እየተዋደቁ ነው። ሰው ስንቅ እንዳያቀብላቸው ግን ተሰዶ ደሴ ገብቷል። ተተኳሽ መከላከያው የወዞ ሸሽቷል። ስንቅ ደግሞ ህዝቡ ሸሽቶ ለቋል።

"…የዐቢይ አህመድ መንግሥት ያሸንፋል እያላችሁ ለምታዝጉኝ ካድሬዎች ምላሼ አዎ ያሸንፋል። መጀመሪያ ግን ዐማራ በድጋሚ መድቀቅ አለበት። መሾቅ አለበት፣ እንዳይነሣ ተደርጎ መወቀጥ አለበት። መንከራተት አለበት። ተቅበዝባዥ መሆን አለበት። ከዚያ ቀላል ነው ትግሬን በዐማራ ምድር ያጭደዋል። እኔ አያሸንፍም፣ ማሸነፍም አይችልም አላልኩም። ይችላል ነገር ግን መጀመሪያ መድቀቅ አለበት።

የቴሌግራም ቻናሌ ነው። http://t.me/ZemedkunBekeleZ

ይሄ ደግሞ የምንወያይበት የቴሌግራም ቻናሌ ነው https://t.me/zemede_Discussion

ይሄ ደግሞ መልእክት የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው +49 1521 5070996

"…ቆይቼ እመለሳለሁ…!!
4.0K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:36:03
ወልቃይት…!!

"…በድኑ ብአዴን ዛሬ ሰሜን ጎንደር ከትሟል። ግርማ የጅብጥላም ለስለላ በዐቢይ አሕመድ ወደ ወልቃይት ተልኳል። እንዲያው ይውጣላችሁ ተብለው እሱና ይልቃል ከፍ አለ ማርሽ ቀያሪዎች የሚል ታፔላ ተለጥፎላቸዋል። ህዝቡ እንዲህ ያደረገ አይመስለኝም። ያው በድኑ ካድሬ ነው እንዲህ የሚያደርገው።

"…በወልቃይት የሰሊጥ መሬት ሲከፋፈል የከረመው የብልፅግና ካድሬ አሁን ጨንቆታል። ዐብይ አሕመድ ለነጮቹ ያስቸገሩኝ ዐማሮቹ ናቸው በማለት እንደመፍትሄ ወልቃይትን ለማስለቀቅ ደሴን አውድሞ በመያዣነት አስይዞ ለመደራደር ከጫፍ ደርሷል። እናም የዛሬው የወልቃይት ጉብኝት ሰሞኑን ምላሹን መጠበቅ ነው።

"…ባለፈው ሳምንት ሙሉ ብአዴን የከረመው ዋግኽምራና ወልድያ፣ ቆቦ ነበር። ሳምንት ሳይሞላው ህወሓት ወልድያጫፍ፣ ቆቦን ያዘች። አሁን ደግሞ ግልብጥ ብለው የት ሄዱ ወልቃይት። ነጭ ወርቅ ሰሊጥ ሊበላ? አፈር ያስበላችሁ የአባቴ አምላክ አለ አጎቴ ሌኒን።

"…የብአዴንን የመኪና ብዛት ተመልከቱ። የአንዱን ዋጋ አስልታችሁ ምቱት። ወያኔ ስትመጣ የሚፈረጥጡትም በዚሁ ነው። ካድሬ ነዳጅ አይጎድልበት፣ ደሞዝ አይቀርበት። አይርበው፣ አይጠማው። አይቸግረው ከባድ ነው።

"…የሚመሩት ህዝብ ደግሞ ከቆቦ ተነሥቶ ኮምቦልቻ ድረስ በእግሩ ገብቷል። የዐማራ መሪዎች ደንታቸው አይደለም። ከምን አያልቅም።

"…የዐማራ ህዝብ ደግሞ አቤት አድርጎ ብአዴንን እንዴት እንደሚፈራ አትጠይቁኝ። መድኃኔዓለምንም፣ አሏህንም አይፈራም እነሱን የሚፈራውን ያህል። የማንም ልቃሚ ልቅምቅም በአናቱ ላይ ሲጸዳዳበት ዝም ብሎ አፍንጫውን ይዞ የሚቀመጠው ዐማራ ብቻም አይደለም ለነገሩ። ኦሮሞም፣ ትግሬም፣ ደቡቡም ነው። እሱ ነገር ይገርመኛል። ብአዴኖች ዘና በሉ… ዐማሮች እየተሰደዳችሁ…!! አይዞኝ።

"…ቆይቼ እመለሳለሁ…!!
3.8K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:36:03
"…ቅዱስ ላሊበላ አሁን…!!

"…ደብረ ሮሀ ቅዱስ ላሊበላ እስከአሁኗ ሰዓት ድረስ የተፈጠረ ነገር የለም። ነገር ግን ህዝቡ በድንጋጤ ውስጥ ነው ያለው። ምክንያቱም ከዚህ በፊት የደረሰበት ፈተና ተመልሦ እንደገና እንዳይመጣ በማሰብ በጭንቀት ላይ ነው ያለው። የሚገኘው።

"…ህዝቡንን ጭንቀት ላይ የጣለው ደግሞ ራሱ መንግሥት ነው። ህዝቡ እንዲደናገጥ እና ከከተማዋ  እንዲወጣ እየገፋፋ ያለው መንግሥት ራሱ ነው። ህዝቡ በወሬ አልወጣ ሲለው አሁን ምን አደረገ መሰላችሁ የዐብይ መንግሥት በላሊበላ የሚገኙ ባንኮች ብር እንዳይደርሳቸው አድርጎ አስሮ አስቀመጣቸው። ባንክ ቤቶቹ አገልግሎት መስጠት ካቆሙ ቆዩ። ገንዘቡን በሙሉ የባለፈው ሳምንት አካባቢ አሸሽተዋል። በእነሱ የተነሣ ህዝቡ እየተደናገጠ ይገኛል።

"…ባንኮች ብር የለም በማለት ህዝቡ ሙሉቀን ሜዳላይ እየተጉላላ ነው የሚውለው። በጣም ለተጨነቀ ሰው፣ ሲያለቅስ ለሚውል ሰው ለአንዳንዱ፣ 500ም፣ 1ሺም ግን ይሰጣሉ። ይሄ የምታየው ሰልፍ ብር ለማውጣት ነው። ሌላው አሸባሪ የመከላከያ ሠራዊቱ ነው። የመከላከያ ሠራዊቱ በግልጽ አፉን አውጥቶ ከተማዋን ለቃችሁ ውጡ ማለት ነው የቀረው። ሲሮጥ ብታየው ቀነኒሳ ምንድነው ትላለህ? አሁን ወልደያ ደርሰዋል፣  በግዳን በኩል እየመጡ ነው ብሎ ራሱ ለራሱ እየነገረ ይፈረጥጣል። በዚያ ላይ ባንኮች እንደዚህ ዓይነት ነገር ሲያደርጉ ህዝቡ እየፈራ ከከተማው እየወጣ ይገኛል።

"…እንደኔ እንደኔ በህዝቡ በልፈርድም ባይሰደድ እና ባለበት በቄዬው ይቆይ ዘንድ እመክራለሁ። እስከአሁን የተሰደደው ህዝብም አዲስ አበባን ያቆሽሻል ተብሎ ስለሚታሰብ እነ አዳነች አቤቤ ድርሽ አያደርጉትም።

"…ቆይቼ ደግሞ ወልቃይት እወስዳችኋለሁ። ከዚያ ያገኘሁትን አስቂኝ መረጃ ጀባ እላችኋለሁ። ጎንደሬ ተጠንቀቅ። ነቅተህ ጠብቅ።

"…እመለሳለሁ…!!
3.3K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:36:03
"…ቅዱስ ላሊበላ

"…ደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላም ደውያለሁ። የጽሑፍም፣ የቪድዮ መረጃም ከወዳጆቼ ደርሶኛል። እናም ከእኔ ከዘመዴ ከሃረርጌው መራታ ነጭ ነጯን ለመስማት ተዘጋጁ!

"…በነገራችን ላይ በሚደርሱኝ መረጃዎች ላይ ዘመድኩን በቀለ የሚለውን ማኅተም ማሳረፌ እነ ኢቲቪን፣ እነ የዩቲዩብ ሸቃሎችን ሳይቀር አደብ አስገዝቷል። እኔ በግሌ እየተፋለጥኩ የማመጣውን መረጃ ልክ እነሱ እንዳገኙት አድርገው መሸቀሉም ቀርቷል። ምንጭ አልጠቅስ ቢሉ የግዳቸውን ቪድዮውንም ሆነ ፎቶውን ሲለቁት ስሜን አብረው ይለቋታል። ኤት’አባክ…ህእ

#ማስታወሻ፦ አሁን በጀርመን የምትኖሩ የላይካ ካርድ ብትልኩልኝ ደስ ይለኛል። የእኔ ወጪዬ እሱ ብቻ ነው። ሃገርቤት በዩሮ መደወል ከባድ ነው። እኔ ደግሞ ገንዘብ አገኝባቸው የነበሩት መንገዶች ሁሉ ዩቲዩብ አድርቆብኛል። መረጃ ቲቪ፣ ራስ ሚዲያ፣ ኢትዮ ቤተሰብ ላይ ትልኩልኝ የነበረው ገንዘብ በሙሉ አጅሬ ዩቲዩብ ሁላቸውንም በእኔ ምክንያት አባርሮ ምንም የለኝም። አሁን የሚጎድለኝ የሞባይል ካርድ ብቻ ነው። ካርዱን ገዝታችሁ በውስጥ መስመር ላኩልኝ። ነጭ ነጯን ማለት ይሄም አይደል?

"…ይሄን የጠየቅኩት ወዳጆቼን ነው። የማይመለከታችሁ ጮጋ በሉ። በእውነት በከፍተኛ በጀት፣ በከባድ የሰው ኃይል የሚሠራን ሥራ በአንድ በእኔ በተራ ደንቆሮ ድልብ መሃይም፣ በማልረባ ጭንጋፍ በሆንኩ ሰው ላይ አድሮ እየሠራ ያለው እግዚአብሔር ነው። ይሄ ለሰው የሚቻል አይደለም። ክብሩን ሁሉ መድኃኔዓለም አባቴ ይውሰድ። በማያገባህ ገብተህ አሁንም ቡሃቃና አቦሬ አፍህን እከፍታለሁ የምትል ካለህ እቀስፍሃለሁ። በወሬ ጠኔም አክለፈልፍህሃለሁ።

• የምፈልገው የላይካ ካርድ ብቻ ነው። የ10 ዩሮም ይሁን የ30 የቻላችሁትን ላኩልኝ። ይሄም ራሱ አገልግሎት ነው። ስልክ የምደውልበትን ብቻ እሺ…!

…ቆይቼ እመለሳለሁ…!
3.0K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:36:03
መርሄ እውነት ብቻ ነው…!!

"…እኔ ዘመዴ የሃረርጌው መራታ ቆቱ ምስክርነቴ የታመነ ነው። ደግሞም የጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጅ እኮ ነኝ። ያውም ባለማዕተብ የተዋሕዶ ልጅ የሥላሴ ባርያ የድንግል አሽከር ነኛ። እውነት ብቻ ከሚሰበክባት፣ የሃቅ ምንጭ ከሚፈልቅባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተገኘሁ ባለ ማዕተብ ነኛ።

"…እኔ በግሌ በኢትዮጵያ ሦስት ጠላት ብቻ ነው ያለኝ። አራተኛው ኢዜማን እንኳን እርሱት ገሌ ነው። ህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ/ኦነግ። ጠላት ብዬ የፈረጅኩት እነዚህን 3 ጉግማንጉጎችን ነው። ከዚያ ውጪ ህዝብ ምንአደረገኝ? ምንም። የህዝብ ጠላት የለኝም።

"…የምጽፈው ነገር በሙሉ ህዝብን የሚጠቅም ነው። ካድሬን ግን ያበሳጫል። ደም ያሸናል። ወሃቢይን ያስመልሰዋል። የብልጽግና ጴንጤን ጨጓራ ይልጣል። አንዳንድ ጎጋ ሀ ገደሉዎችን ያንተፋትፋል። በእነሱ ብዙም አላዝንም። ሲገባቸው ይነቃሉ። እኔ እንደ ናትናኤል ጋሽ ደርቤ እንድጽፍ፣ እንደ ስዩም፣ እንደ ሙክታሮቢች እንድበጠረቅ የሚፈልጉ አሉ። ነገርኩህ እኔ ባለማዕተብ ነኝ። እውነቱን እነግርሃለሁ የመሸበት አድራለሁ።

"…እኔ ዘመዴ ተከተለኝ አላልኩህም። የወሬ ጠኔ ይዞህ እየተክለፈለፍክ የመጣኸው አንተው ነህ። ከመጣህ ደግሞ ሥነሥርዓት ትይዛለህ እንጂ ይሄን አቦሬ ቡሃቃ አፍህን እንድትከፍትብኝ አልፈቅድልህም። በብሎክባን ሰይፌ እቀስፍሃለሁ። አንት የቁጭራ ልጅ። ማንም ሁን ማን በሌላ ሲም ካርድ ትከታተለኛለህ። ሃላስ…

የቴሌግራም ቻናሌ ነው። http://t.me/ZemedkunBekeleZ

ይሄ ደግሞ የምንወያይበት የቴሌግራም ቻናሌ ነው https://t.me/zemede_Discussion

ይሄ ደግሞ መልእክት የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው +49 1521 5070996

"…የትም እንዳትሄዱ። እመለሳለሁ ጠብቁኝ…!
3.0K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 15:36:03
ከርታታው ዐማራ…!!

"…ይህ የምታዩት ህዝብ ጠባቂ፣ ተከላካይ፣ አደራጅ አጥቶ እንደ ኩርድ ህዝብ በገዛ ሃገሩ እንዲሰደድ የተፈረደበት ህዝብ ነው። የፖለቲካ መሪ፣ የለውም። የሚያደራጀው ብቅ ሲል ወይ ይገደላል። ወይ ይታሠራል። ከምር የሚያሳዝን ህዝብ ነው።

"…የዐማራ ፋኖ ከክላሽ ውጪ ሌላ መሳሪያ የለውም። ጥይት እንኳ ከመከላከያ እየገዛ ነው የሚጠቀመው። መከላከያ ሲፈረጥጥ ያንኑ ገዝቶ የሚዋጋበትን ተተኳሽ እንኳ አያገኝም። መድፍ መያዝ አይፈቀድለትም። ከክላሽ እና አንዳንዴ ከብሬን ውጪ ከባድ መሳሪያ ለዐማራ ልዩ ኃይል እንኳ አይፈቀድለትም። ሲያጠቃ መከላከያ አለቃው ይሆናል። ተመለስ ይለዋል። እምቢ ካለ በመድፍ፣ በድሮን ይፈጀዋል።

"…መከላከያ የመሸሽ፣ የመፈርጠጥ ፈቃድና መብትም አለው። በትግሬና በዐማራ ጦርነት ምን አገባኝ የሚለው የኦሮሞ ወታደር ነፍ ነው። አጋጣሚ ሲያገኝ ከነሙሉ መሳሪያው ለህወሓት እጁን ይሰጣል። ፋኖና የዐማራ ልዩ ኃይሎች ግን ህዝባቸውን ትተው ወዴት ይሽሹ? ክላሽ ይዘው ይፋለማሉ። ክብር ለዐማራ ልዩኃይልና ለዐማራ ፋኖ።

"…ሌላው ህዝቡ ያላወቀው ነገር በመከላከያ ውስጥ የዐማራ ወታደር ከባድ መሳሪያ እንዲተኩስ አይሰለጥንም። ክልክል ነው። ክላሽ ብቻ ነው። ወያኔ ታንክ፣ ቢኤም፣ ዲሽቃ ሁሉም ተዋጊ ይጠቀማል። ይሄ ሌላኛው ክፍተት ነው። ዐማራ በመከላከያ ውስጥ የሚያስፈልገው ክላሽ ይዞ እንዲጠበጠብ ብቻ ነው።

"…አስቂኙ ነገር ደግሞ ልዩኃይሉና ፋኖው በጦርነት ወቅት የሚገናኙት በሞባይል ነው። ፋኖ በጣም ካጠቃ ፍርዬ ከአዲስ አበባ ኔትወርኩን ታጠፋለች። አለቀ። በምን ይግባቡ? ፋኖ ሬድዮ እንዲኖረው አይፈቀድም። ከዚያ ይቆረጣሉ። ያፈገፍጋሉ። አንዳንዴም ህወሓት የመከላከያውን ልብስ አልብሳ ትመጣለች። ዐማራ አክባሪ ነው። መከላከያ መስሎት ግቢ ይላታል።

"…ጠብቁኝ እመለሳለሁ…!!
3.0K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ