Get Mystery Box with random crypto!

ወልቃይት…!! '…በድኑ ብአዴን ዛሬ ሰሜን ጎንደር ከትሟል። ግርማ የጅብጥላም ለስለላ በዐቢይ አሕ | ....

ወልቃይት…!!

"…በድኑ ብአዴን ዛሬ ሰሜን ጎንደር ከትሟል። ግርማ የጅብጥላም ለስለላ በዐቢይ አሕመድ ወደ ወልቃይት ተልኳል። እንዲያው ይውጣላችሁ ተብለው እሱና ይልቃል ከፍ አለ ማርሽ ቀያሪዎች የሚል ታፔላ ተለጥፎላቸዋል። ህዝቡ እንዲህ ያደረገ አይመስለኝም። ያው በድኑ ካድሬ ነው እንዲህ የሚያደርገው።

"…በወልቃይት የሰሊጥ መሬት ሲከፋፈል የከረመው የብልፅግና ካድሬ አሁን ጨንቆታል። ዐብይ አሕመድ ለነጮቹ ያስቸገሩኝ ዐማሮቹ ናቸው በማለት እንደመፍትሄ ወልቃይትን ለማስለቀቅ ደሴን አውድሞ በመያዣነት አስይዞ ለመደራደር ከጫፍ ደርሷል። እናም የዛሬው የወልቃይት ጉብኝት ሰሞኑን ምላሹን መጠበቅ ነው።

"…ባለፈው ሳምንት ሙሉ ብአዴን የከረመው ዋግኽምራና ወልድያ፣ ቆቦ ነበር። ሳምንት ሳይሞላው ህወሓት ወልድያጫፍ፣ ቆቦን ያዘች። አሁን ደግሞ ግልብጥ ብለው የት ሄዱ ወልቃይት። ነጭ ወርቅ ሰሊጥ ሊበላ? አፈር ያስበላችሁ የአባቴ አምላክ አለ አጎቴ ሌኒን።

"…የብአዴንን የመኪና ብዛት ተመልከቱ። የአንዱን ዋጋ አስልታችሁ ምቱት። ወያኔ ስትመጣ የሚፈረጥጡትም በዚሁ ነው። ካድሬ ነዳጅ አይጎድልበት፣ ደሞዝ አይቀርበት። አይርበው፣ አይጠማው። አይቸግረው ከባድ ነው።

"…የሚመሩት ህዝብ ደግሞ ከቆቦ ተነሥቶ ኮምቦልቻ ድረስ በእግሩ ገብቷል። የዐማራ መሪዎች ደንታቸው አይደለም። ከምን አያልቅም።

"…የዐማራ ህዝብ ደግሞ አቤት አድርጎ ብአዴንን እንዴት እንደሚፈራ አትጠይቁኝ። መድኃኔዓለምንም፣ አሏህንም አይፈራም እነሱን የሚፈራውን ያህል። የማንም ልቃሚ ልቅምቅም በአናቱ ላይ ሲጸዳዳበት ዝም ብሎ አፍንጫውን ይዞ የሚቀመጠው ዐማራ ብቻም አይደለም ለነገሩ። ኦሮሞም፣ ትግሬም፣ ደቡቡም ነው። እሱ ነገር ይገርመኛል። ብአዴኖች ዘና በሉ… ዐማሮች እየተሰደዳችሁ…!! አይዞኝ።

"…ቆይቼ እመለሳለሁ…!!