Get Mystery Box with random crypto!

....

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemdkunbekelez — .... Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemdkunbekelez — ....
የሰርጥ አድራሻ: @zemdkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 27.66K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው።
ይህ የዩቲዩብ ቻናሌ ደግሞ ሰኔ 6/2012 ዓም ከራየን ወንዝ ማዶ የተከፈተ ነው።
https://www.youtube.com/c/ZemedkunBekele?sub_confirmation=1
እንደ ፌስቡክ፣ እንደ ቴሌግራሙ ሁሉ በዚህ መንደርም ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክ ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 139

2022-08-30 15:36:02
ባንኮች በወልድያ እና በሙሉ ወሎ…!!

"…የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከኦሮሙማው መንግሥት በተሰጠው መመሪያ መሠረት ባንኩን ዘግቶ ፈርጥጧል። በንግድ ባንክ ገንዘባቸውን አስቀምጠው አንሰደድም ብለው በቀዬአቸው የተቀመጡ ዐማሮች ችግር ላይ ወድቀዋል። የመንግሥቱ ዋነኛ ዓላማ ዐማራን ማድቀቅ ስለሆነ ይኸው እየተተገበረ ነው። ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንኳን አሁንና በደኅናውም ጊዜ ከሱማሌ ክልል ለተፈናቀሉ ኦሮሞዎች ግማሽ ቢልዮን ብር ሲሰጥ፣ ለዐማሮቹ 4ሚልዮን ነበር ሰጥቶ ለዐማራ ያለውን ንቀት ያሳየው። ህዝቡ ግን ያሳዝናል። በወልድያ ባንክ ቤቱን ከቦ ቆሞ ያለቅሳል።

"…በዚያው ጎን ደግሞ ዓባይ ባንክ ከከተማው አልወጣም። እስከአሁን ለደንበኞቹ አገልግሎቱን እየሰጠ ነው። ዐማራ የራሱን ተቋማት በዚህ መልክ ቢያደራጅ የማንም መጫወቻ አይሆንም ነበር። በወልድያ ዓባይ ባንክ በካዝናዬ ያለው ብር እስኪያልቅ መጥታችሁ ውሰዱ ብሏል። በኋላ እንዳይቸግራቸው ማለት ነው።

• ለጎንደርና ለባህርዳር እንዲሁም ለደብረ ማርቆስ የታቀደውን ዕቅድ ይዤ እመለሳለሁ። በተለይ ሦስቱ ከተሞች በኦሮሙማው ብልፅግና የተደገሰላችሁን የጥፋት ድግስ መመከት ትችሉ ዘንድ በተጠንቀቅ ራሳችሁን ጠብቁ በተለይ። ደብረ ማርቆሶች በመርጦ ለማርያም በኩል አይናችሁን አትንቀሉ።

"…እመለሳለሁ…!!
3.4K views12:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 18:19:07
እንኳን ደስ አላችሁ…!!

"…ብዙ ደክሜበታለሁ…ብዙም ለፍቼበታለሁ…በብዙዎችም ተሰድቤበታለሁ…ተነቅፌበታለሁም…ከብዙዎችም ጋር ክፉ ደግ ተነጋግሬበታለሁ… ጥቂት ወዳጀቼንም አጥቼበታለሁ… አሐዱ ባንክ።

"…ብዙዎች ተስፋ እንዲሰንቁበትም በብዙ ወትውቻለሁ… ብዙዎችም ይሄ መራታ ምንአባቱ ነው የሚለፈልፍብን ብለው ሳይንቁኝ ቃሌን አምነው… ድምጼንም ሰምተው፣ ገንዘባቸውንም ሆጨጭም ፎጨጭም አድረግው የባንኩ ባለቤትም ሆነዋል። ከሃገረ እንግሊዝ ካስገባኋት ባለ 10 ሚልዮኗ ብር እህቴ ጀምሮ በማዳም ቤት በእሳት እስከሚቃጠሉት እህት ወንድሞቼ በገፍ ወደ እዚህ ባንክ ጎርፈዋል። በሁሉም ደስተኛ ነኝ።

"…ያለ ሳንቲም ክፍያ አይንህ ውስጥ የገባ ቆሻሻ ጠርጎ በማያወጣልህ፣ መንገድ ምራኝ ብትለው በማይሰማህ ዓለም ውስጥ እየኖርን እኔ ግን ይህን ሁሉ በማድረጌ ዜሮ አምስት ሳንቲም፣ ጢና፣ ዱንቡሎ ፈረንካ ኮሚሽን አላገኘሁበትም። የቦርድ አባላቱ ሰብስበው ሲያናግሩኝ የነገርኳቸውም ይሄንኑ ነበር። በዚህ ጉዳይ ላይ በዙም በነበረን ውይይትም ላይ ለደቂቃዎች ያህል ትንፋሻቸውን ውጠው በድን እስኪመስሉ ድረስ ነበር ድንጋጤን ያወረድኩባቸው። በዚህም ደስተኛ ነኝ። የስልክ ካርድ እየለመንኩ በፔይፓል ሙሉልኝ እያልኩ በማገለግልበት ምድር ላይ ሚልዮን ብሮችን መናቄም የጉራ አይምሰላችሁ። ፆሩ ስለተነቀለልኝ ነው።

"…በአንተ ውትወታ ነው አክስዮኑን የገዛነው፣ ባንኩ ከምን ደረሰ? እያላችሁ ስትወተውቱኝ የኖራችሁ ጓደኞቼ በሙሉ ባንኩ ይኸው ሥራውን ጀምሮላችኋል። ተጠቀሙበት። ገንዘባችሁን ቆጥቡበት። በጎደለው እየሞላችሁ ከፍከፍም አድርጉት። አትርፉበትም።

"…ከእረፍቴ መልስም ግን እኔ ግን አጀንዳዬን አልቀይርም…!! 5 ሺ ሰው በታረደበት ምድር ላይ እሱን ረስቼ በፌካፌካም ኮንዲሚንየም ወሬም አጀንዳዬን አልቀይርም።

"…በሉ ወደ እረፍቴ ልመለስ…!
3.8K views15:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 14:57:03 "ለቴሌግራም ጓደኞቼ በሙሉ…!!

"…ከዛሬ ጀምሮ ቢያንስ ለአንድ ሳምንት ከዚህ መንደር ዘወር ማለት አማረኝ። አሰኘኝም። እናም ድንገት ብታጡኝ መታፈንም፣ መደለልም እንዳልተፈጸመብኝ እና በሰላም መሆኑን እንድታውቁ ይሁን። አዎ ከምር በእውነት ስለ እውነት ለትንሽ ቀን ዘወር ማለትን ወደድኩ። ማክሰኞ በራስ ሚዲያ፣ ሐሙስ በኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያ፣ እሁድ በመረጃ ቲቪም ብቅ አልልም። 24/7 ቀንና ሌሊት ያለመታከት ዋይ ዋይ እሪሪሪ ኡኡም፣ ቁቁም ስል የምታወቅ አደንቋሪ፣ በጥባጭ፣ ረብሸኛው የሐረርጌ መራታ ቆቱው እኔ ዘመዴ ድንገት ዝም ስል በኢንተርኔቱ ዓለም ያሉ ሐሰተኛ ነቢያት እንዲህና እንዲያ ሆኖ ነው እያሉ እንዳያውኳችሁ ነው ይህችን አጭር ማስታወሻ መጻፌ።

"…በእኔ ለጥቂት ቀን ከዚህ መንደር መጥፋት የሚናደዱብኝ፣ ቅር የሚሰኙብኝ፣ የሚበሰጩብኝ፣ እንደ ጠላት የሚያዩኝ ሁላ ሳይቀር ቅር እንደሚላቸው ይገባኛል። ምክንያቱም ከዚህ ቀደም ለሁለት ሦስት ቀናት ያህል በጠፋሁ ቁጥር "አንተ መራታ ምን አባህ ሆነህ ነው ዝም የምትለው?" በማለት የሚወተውቱኝ ለወትሮው ይድፋህ፣ አንት ሰይጣን፣ አንት አሸበርቲ፣ አሸባሪ፣ ፀረ ልማት፣ ፀረ ምንጥስዮ፣ ቅብጥርስዮ የሚሉኝ እነዚያው ወገኖች እንደነበሩ ስለማውቅ ነው። ከዚህ በፊት በጀርመን ችግር በገጠመኝ ጊዜ ቢያገኙኝ ዘልዝለው ይበሉኛል የምላቸው ሰዎች እንዴት ደውለው ሳይቀር መልካሙን ሁሉ እንደተመኙልኝ፣ እንዳንተ ሳይሆን ለልጆችህ ስንል ነው እያሉ በልጆቼ ሰበብ ለእኔ ሲጨነቁልኝ እንደነበር ስለማውቅ ነው። ሙጂብ አሚኖ ሳይቀር ነው መጥፋቴ የሚረብሸው። በነገራችን ላይ ሙጂብ ሰሞኑን ጸሎተኛ ሆነብኝሳ። አይ ጎንደር…!!

"…አሁን በህይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ማረፌ ነው። ለቤተሰቦቼም ጭምር እረፍት ልሁናቸው። እዚሁ ጀርመን የሆነ ሐይቅም ወንዝም፣ ተራራም ካለ ይዤአቸው ወጣ ገባ ልበል እስቲ። በሳምንት 3 ቀን ከጓደኛዬ ጋር የማደርገውን የራየን ወንዝ ዳር የ20 ኪሜ የእግር ጉዞ ወደ 42 ኪሜ ላሳድገው። መልካሙ ነገር በየትኛውም የጀርመን ግዛት ለ3 ወራት በ9 ዩሮ የፈለጋችሁበት ሂዱ ብሎናል የጀርመን መንግሥት። እናም እኔም ሽው እልም ልበል እስቲ። ጥፍት ልበል።

"…ፌስቡክ አልጠቀምም። ቴሌግራም ላይ አልጽፍም። ከዚህ ፔጅ ሌላ በስሜ የሚተላለፉ ማናቸውም መልእክቶች የእኔ አይደሉም። ደግሞም ስለ እኔ አብዝታችሁም ባይሆን ድንገት ትዝ ስላችሁ ለጸሎት በቆማችሁ ጊዜ አክሊለ ገብርኤል ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡኝ። በሰላም እስክመለስ ድረስ በያላችሁበት… አጀንዳዬን ግን አልቀይርም…!!

"…ሰላም ቆዩኝ…!!
11.6K views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 14:57:03
10.0K views11:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 08:04:30
በመጨረሻም የቤት ነገር…!!

"…ከወራት በፊት በህልውና ዘመቻው የተሰው የዘማች ወታደር ቤተሰቦችን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትሰበስባለች አሉ። ካሜራ ደግና፣ በህዝቡ ሁሉ ፊት ለሟች ወታደሮች ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ቁልፍ ትሰጣቸዋለች። ዜናውም ተሠራ። ዓለሙ ሁሉ ምን አይነት ደግ መንግሥት ነው የመጣው ብሎ ተደመመ። እንዲያውም በምርጫው ማሸነፍ አለባቸው አለና ብልፅግናን መረጠ።

"…መሸ፣ ነጋ፣ ብዙ ወራት አለፉ። የሟች ወታደሮች ቤተሰቦች ቁልፋቸውን ይዘው ቤታቸውን ሊረከቡ ከንቲባ አዳነች ጽ/ቤት መጡ። እስከ አሁን ቤቱ አልተሰጠንም እኮ ብለውም አቤት አሉ። ሂዱና በየወረዳችሁ፣ በየክፍለ ከተማችሁም ጠይቁ ተባሉ። የሟች ወታደሮች ቤተሰቦችም ሄዱ። ጠየቁም። ምን ቢሏቸው ጥሩ ነው። "ሂዱ ጥፉ። ድራሽ አባታችሁ ይጥፋ። ሁለተኛ እዚህ ድርሽ ትሉና ውርድ ከራሴ ብለው አበሻቅጠው ያባርሯቸዋል። በሁኔታው ግራ የተጋቡት የሟች ወታደር ቤተሰቦችም ጠየቁ። "ታዲያ ቁልፉን ለምን ሰጣችሁን? መለሱላቸው። ቁልፉንማ የሰጠናችሁ ለዜና ሽፋን ነው። ለምርጫ ቅስቀሳ። ስታስቡት ለዚያ ሁሉ ለረገፈ ወታደር ቤተሰብ ቤት ተሰጥቶ ይዘለቃል እንዴ? አድዮስ።

"…መሸ ነጋ ስንተኛው ወር ላይ ደግሞ ሌላ የቤት ዜና ከቺሳ አለ። የወለጋው የ5ሺ ዐማራን ዕርድ የሚያስቀይስ አጀንዳ ቢባል፣ ቢባል ጠፋ። ፓትርያሪኩ ሊኮበልሉ ነው። ዝም ህዝቡ። ሱዳን ወረረችን ጭጭ ህዝቡ፣ ደቡብ ሱዳን ጂንካ ደረሰች። ወይ ንቅንቅ። አጀንዳዬን አልቀይርም ብሎ ገገመ። ናትናኤል መኮንን በዚህ፣ ቶማስ ጃጀው በዚያ፣ ሱሌማን አብደላ በዚያ ቢል ወይ ፍንክች። በመጨረሻም የኮንዶሚንየም ካርታ ተሳበች። ተመዘዘች። ከዚያ ዕጣ ወጣ ተባለ። አዳሜም ጮቤ ረገጠ። ወለጋንም ረሳ። ግን ጥቂት ሰው ሆነ የተሸወደው። እነ አዳነች ተበሳጩ። ተበሳጩና ወጣ ያሉትን ዕጣ መልሰው ስበው አልወጣም። አይንህ ይውጣ። ልትበላ ያምርሃል። ምደረ ነፍጠኛ ሁላ ብለው አዕምሮውን ዠልጠው ሽባ አድርገው አስቀመጡት።

"…እኔ ግን አጀንዳዬን አልቀይርም…!!

• ኮንዶሚንየም ነው? …ኤኤኤለም…!!

#እምቢ
#በቃ
#amhara_under_attack
#Amhara_lives_matter
#Amharagenocide_in_oromiya
10.2K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 08:04:30
8.7K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 23:01:21
የጥንቃቄ መረጃ ለደሴ መስመር ተጓዦች…!!

"... ዘመዴ እንደምን ከርመሃል? በዛሬው ዕለት ግጭት በተሻለ መልኩ ከነገ ጀምሮ ከሰንበቴ እስከ ባልጪ ባለው ስፍራ የተጓዥ መንገደኞችን እናርዳለን የሚል ውሳኔ #በጤ ላይ እንደወሰኑ መረጃው ደርሶናል። እባክህ መንገደኞች ነገ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳውቅልን። አኔም ይኸው አሳወቅኩ።

"…ጠየቅኩም እናንተስ ምን አደረጋችሁ? መንግሥትስ አያውቅምን? አልኳቸው። የመንገድ ሁኔታው ዝግ እንዲሆን ለማድረግ ለልዩ ኃይሉ መሪ ለኮ/ል ጌታ ለሻለቃዋ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ም/ሳ/ን ደጅዬ አበበ እና ለሻምበል መሪው ሳ/ን ሔኖክ እና ለአጣዬ መንገድ ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ አቶ በድሉ ሸዋፈራ እንዲያውቁ አድርገናል። ማልደው የሚጓዙ አሽከርካሪዎችም እንዲሰሙት የምንችለውን ሁሉ አድርገናል።

"…የዛሬው የጉዳት መጠንስ እንዴት ይገለጻል ብዬም ጠይቄአለሁ። "…ኧረ አይነገርም ዘመዴ። አይነገርም። ባንዲራ የያዘ የዐማራ ልዩ ኃይል ልብስ አልብሰው አምጥተው እኮ ነው የፈጁት። ልክ እንደባለፈው የገበሬው ቤት ሲቃጠል በአማርኛ እያወሩ ቪድዮ እየቀረጹ ነበር። "የክልሉ መሪዎች ከማታ ጀምሮ ሲነገራቸው አታካብዱ፣ ከቁጥጥራችን ውጪ አይደሉም እያሉ ነው ያመሹት።

"…ከልዩ ኃይሉ ውጪ እስከአሁን 7 ዐማሮች ተገድለዋል። ከ50 በላይ ቤት አቃጥለዋል።  ከአርሶ አምባ ማኛ ቀበሌ ዋጌና እና በርሃ የተባሉት መንደሮች፣ ከመንተኬ ሸረፋ ቀበሌ፣ መዲና፣ ጂሌ አምባ፣ ስርጌ፣ ሼህ ኡስማን እና ጀለሌ ዐመድ ሆነዋል። አሁን ብርቂቱን ለማቃጠል እየሄዱ ነው። ከዚያ አጣዬን መልሳችሁ አውድሟት ተብለናል ነው የሚሉት አሉ።

"…የዐማራ ልዩ ኃይል ወንድሙ ፋኖን ሲያሳድድ፣ ሲያስር ከርሞ ዛሬ በግላጭ አገኙት። ማን ይድረስለት። ወይ ዐማራ…!! እንዴት አንድ አዳኝ ያጣል…? ለማንኛውም ተጓዦች ነገን ተጠንቀቁ…!!
8.9K views20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 20:48:10
8.1K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 20:48:09
8.1K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ