Get Mystery Box with random crypto!

በመጨረሻም የቤት ነገር…!! '…ከወራት በፊት በህልውና ዘመቻው የተሰው የዘማች ወታደር ቤተሰቦች | ....


በመጨረሻም የቤት ነገር…!!

"…ከወራት በፊት በህልውና ዘመቻው የተሰው የዘማች ወታደር ቤተሰቦችን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ትሰበስባለች አሉ። ካሜራ ደግና፣ በህዝቡ ሁሉ ፊት ለሟች ወታደሮች ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ቁልፍ ትሰጣቸዋለች። ዜናውም ተሠራ። ዓለሙ ሁሉ ምን አይነት ደግ መንግሥት ነው የመጣው ብሎ ተደመመ። እንዲያውም በምርጫው ማሸነፍ አለባቸው አለና ብልፅግናን መረጠ።

"…መሸ፣ ነጋ፣ ብዙ ወራት አለፉ። የሟች ወታደሮች ቤተሰቦች ቁልፋቸውን ይዘው ቤታቸውን ሊረከቡ ከንቲባ አዳነች ጽ/ቤት መጡ። እስከ አሁን ቤቱ አልተሰጠንም እኮ ብለውም አቤት አሉ። ሂዱና በየወረዳችሁ፣ በየክፍለ ከተማችሁም ጠይቁ ተባሉ። የሟች ወታደሮች ቤተሰቦችም ሄዱ። ጠየቁም። ምን ቢሏቸው ጥሩ ነው። "ሂዱ ጥፉ። ድራሽ አባታችሁ ይጥፋ። ሁለተኛ እዚህ ድርሽ ትሉና ውርድ ከራሴ ብለው አበሻቅጠው ያባርሯቸዋል። በሁኔታው ግራ የተጋቡት የሟች ወታደር ቤተሰቦችም ጠየቁ። "ታዲያ ቁልፉን ለምን ሰጣችሁን? መለሱላቸው። ቁልፉንማ የሰጠናችሁ ለዜና ሽፋን ነው። ለምርጫ ቅስቀሳ። ስታስቡት ለዚያ ሁሉ ለረገፈ ወታደር ቤተሰብ ቤት ተሰጥቶ ይዘለቃል እንዴ? አድዮስ።

"…መሸ ነጋ ስንተኛው ወር ላይ ደግሞ ሌላ የቤት ዜና ከቺሳ አለ። የወለጋው የ5ሺ ዐማራን ዕርድ የሚያስቀይስ አጀንዳ ቢባል፣ ቢባል ጠፋ። ፓትርያሪኩ ሊኮበልሉ ነው። ዝም ህዝቡ። ሱዳን ወረረችን ጭጭ ህዝቡ፣ ደቡብ ሱዳን ጂንካ ደረሰች። ወይ ንቅንቅ። አጀንዳዬን አልቀይርም ብሎ ገገመ። ናትናኤል መኮንን በዚህ፣ ቶማስ ጃጀው በዚያ፣ ሱሌማን አብደላ በዚያ ቢል ወይ ፍንክች። በመጨረሻም የኮንዶሚንየም ካርታ ተሳበች። ተመዘዘች። ከዚያ ዕጣ ወጣ ተባለ። አዳሜም ጮቤ ረገጠ። ወለጋንም ረሳ። ግን ጥቂት ሰው ሆነ የተሸወደው። እነ አዳነች ተበሳጩ። ተበሳጩና ወጣ ያሉትን ዕጣ መልሰው ስበው አልወጣም። አይንህ ይውጣ። ልትበላ ያምርሃል። ምደረ ነፍጠኛ ሁላ ብለው አዕምሮውን ዠልጠው ሽባ አድርገው አስቀመጡት።

"…እኔ ግን አጀንዳዬን አልቀይርም…!!

• ኮንዶሚንየም ነው? …ኤኤኤለም…!!

#እምቢ
#በቃ
#amhara_under_attack
#Amhara_lives_matter
#Amharagenocide_in_oromiya