2022-09-04 16:20:18
መረጃ ቴሌቭጅንን በተመለከተ…!!
"…መረጃ ቴቭ ማለት እነ ኤልያስ ክፍሌ የሳታላይት የአየር ሞገዱን ገዙና በዚያ ላይ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ የተለየ ሃሳብ አለን የሚሉ፣ በመንግሥት የፖለቲካ ቋት ውስጥ በሚተላለፉ የአየር ሞገዶች ውስጥ ሃሳባቸውን ለመግለጽ የማይፈቅድላቸው ኢትዮጵያውያን ሃሳባቸውን በነፃነት ይገልጹ ዘንድ የተከፈተ የሳታላይት ጣቢያ ነው።
"…መረጃ ቴቪ ለትርፍ ያልተቋቋመ እና ከየትኛውም የሃገር ውስጥና የውጭ ሃገር ተቋማት የገንዘብ ድጋፍ የማይደረግለት የቴሌቭዥን ጣቢያ ነው። እናም እስከ ቅርብ ዓመታት ድረስ ሁለት ደጋግ ባልና ሚስት ኢትዮጵያውያን እስከ ግማሽ ሚልዮን ዶላር አውጥተው በአየር ላይ ለማቆየት ሙከራ አድርገዋል። ጣቢያው ሃገር ቤት ገብቶም ሥራ ጀምሮ ነበር። መንግሥት ልክ እንደነ ኢሳት የካድሬ ሥራ ካልሠራህልኝ ውጣ፣ ድራሽ አባክ ይጥፋ ብሎ አስወጥቶታል።
"…የእኔን ከዩቲዩብ መባረር ተከትሎም መረጃ ቲቪ ለእኔ የአየር ሰዓት በነፃ ሰጥቶኝ ስንቀሳቀስበት ቆይቻለሁ። ወደፊትም በህይወት እስካለን ድረስ ይቀጥላል። መረጃ ቲቪ በዩቲዩብ ላይ ብቻ የሚታዩትን ኢትዮ 360 ዎችንም በነፃ የአየር ሰዓት ሰጥቶ ይንቀሳቀሱበት ዘንድ ዕድል የፈጠረ በአይነቱ የተለየ የቴሌቭዥን ጣቢያ ነው። የእኔ ዘመዴ ነጭ ነጯም ሆነ የኢትዮ 360 ዎቹ ፕሮግራም የተፈቀደልን በነፃ ነው። በመረጃ ቴቪላይ የአየር ሰዓት ከፍሎ ፕሮግራሙን የሚሠራ የለም። በነጻ ነው። ብዙዎች መረጃ ቴቪ የሁለታችን ሁላ ይመስላቸዋል።
"…እናም ከዓመት በፊት ጀምሮ እነዚያ ባለሃብቶችን ለማገዝ በመፈለግ የአየር ሰዓትንና አንዳንዳድ የቴክኒክ ወጪዎችን ብቻ ለመሸፈን የሚያስፈልገውን ወርሃዊ ዶላር ከኢትዮ ቤተሰብ ሚዲያና ከኢትዮ 360 ጋር በመተባበር በጎፈንድሚ እየተሰበሰበ ስንከፍል ቆይተናል። አሁን ባለፈው ሳምንት መከፈል የነበረበት ክፍያ ባለመከፈሉ ምክንያት የመረጃ ቲቪ ክፍያ እስኪፈጽም ድረስ ለጊዜው ተቋርጧል።
"…ምንአልባት ዛሬ እኔ፣ ሀብታሙ አያሌውና ብሩክ ይባስ በምናቀርበው የጎፈንድሚ ስብሰባ ላይ የምናገኘው ብር መረጃን ያስቀጥለዋል።
"…በመረጃ ቴቪ ለዋልድባዎች ከ23 ሚልየን ብር በላይ ተሰብስቦላቸዋል። በመረጃ ቴቪ ቅዱስ ፓትርያሪኩ የታፈነ ድምጻቸው ተሰምቶበታል። በመረጃ ቲቪ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃሳባቸውን ገልጸውበታል። መረጃ ቲቪ ለሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከእነ ኢቢሲ፣ ከእነ ፋናና ዋልታ በተለየ መልኩ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ሆኖ አገልግሏል። በወለጋ የታረዱ ዐማሮችን በድፍረት ለዓለም ህዝብ ያሳየው የመረጃ ቴቪ ብቻ ነው። እናም መረጃ ማለት ለገዢው ፓርቲ ኮሶ እሬት ለህዝቡ ደግሞ አማራጭ የመረጃ ምንጭ ነው።
"…እናም የመረጃ ፕሮግራም የተቋረጠው በዚህ ምክንያት ነው። የመንግሥትም የማንም እጅ የለበትም። ባልዋሉበትማ አልከሳቸውም። ችግሩ የገንዘብ ችግር ነው። አውቃለሁ ብዙ እናቶች፣ አባቶች፣ ወንድሞች፣ እህቶች መርሀ ግብራችንን እንደሚጠብቁ። ብዙ ፖለቲከኞችም እንደሚጠብቁ። ወዳጅም ጠላትም ምን ተባለ ብሎ እንደሚጠብቅ አውቃለሁ። እንዲያውም ዛሬ የግርማ የሺጥላን የቤተሰብ አገዛዝ የምዘረግፍበት ቀንም ነበር። እናም ለዛሬ አልተሳካም። ዛሬ ባይሳካም ነገ ይቀጥላል። ይሳካልም።
"…ይኸው ነው…!!
1.6K views13:20