Get Mystery Box with random crypto!

....

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemdkunbekelez — .... Z
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemdkunbekelez — ....
የሰርጥ አድራሻ: @zemdkunbekelez
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 27.66K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው።
ይህ የዩቲዩብ ቻናሌ ደግሞ ሰኔ 6/2012 ዓም ከራየን ወንዝ ማዶ የተከፈተ ነው።
https://www.youtube.com/c/ZemedkunBekele?sub_confirmation=1
እንደ ፌስቡክ፣ እንደ ቴሌግራሙ ሁሉ በዚህ መንደርም ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክ ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-02-28 19:49:01
ጥቂት ስለ መሳሪያዎቹ…!!

"…ፔኮኳ ደንግጣ ላይቀርላት ሕዝቡ ላይ ሽብር ለመፍጠር ስትል ድግሷ እንዳማረላት ሴት በቀን ብርሃን መኪና ላይ አስጭና ውር ውር ዊኒጥ ዊኒጥም ስለምትለው የፒኮክ ሚሳኤል ወፏ እንዲህ እያለችኝ ነው።

"…አብይ ሊጨርሰን ነው እንዴ? ምን አስቦ ነው እንዲህ በሃገር ሰላም በዋና ከተማዋ ከባድ መሳሪያ ቀን ከሌሊት እያንጎማለለ የሚያስፈራራን ስትሉ ለነበራችሁም ስለመሣሪያው ስሪት የወፌን መረጃ እነሆ።

"…የሚታዩት የጦር መሣሪያዎች እጅግ ኋላቀር የጦር መሳሪያዎች ናቸው። በሙሉ አየር መከላከያዎቹ ዐማራ ክልል የነበሩ ናቸው። አሁን ነው ተነቅለው ወደዚህ ወደ መሃል ሃገር እንዲመጡ የተደረጉት። የመሳሪዎቹን አቅም ያየን እንደሆነ በሶቪየት ኅብረት ጊዜ ደርግ ያስገባቸው ኋላቀር መሣሪያዎች ናቸው።

"…አንዱ በጣም ትልቁ volga ላውንቸር ይባላል። 40 ኪሎሜትር የሚሄድ ነው። ሁለቱ አነስተኛዎቹ ፒቹራ ሚሳኤል ነው የሚባሉት። 27 ኪሜ ነው ሚሄዱት። ከዚህ ቀደም አፋር ላይ በረሀ ላይ ተሞክሮ ኢላማው ጋር ሳይደርስ መሀል ላይ የወደቀ ነው። አንዱ ደሞ ራዳር ነው 36d six russia serit ራዳር ይሰኛል።

"…ይሄንን ነው እንግዲህ የ7ተኛ ጨው አብይ አህመድ ሕዝብን ለማስፈራራት በቀን በጠራራ ፀሐይ የዛገ ያረጀ የፈጀ ሚሳኤል ቀለም ቀብቶ እየሸለለ ያለው። በመሳሪያ ብዛት ሚያሸንፍ የለም ጥቂት እድሜ ይገዛ እንደሆነ እንጂ አዲስ ነገር እንኳ የለም። ዘመኑ አብቅቷል።

• መልእክቱ እንዳትፈሩት ለማለት ነው። ፒኮካም…!

"…የመላከ አንከርት፣ የአባ ፋኑኤልን እና የደበበን ነገር እንዳልረሳሁት ይታወቅ። እመጣለታለሁ። አልፋታውም።
3.2K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 15:16:28 "…እነ መልአከ አንከርት ግርማን በተመለከተ በ1 ሰዓት የሚያል የድምጽ መልእክቴን አስተላልፌአለሁ።

"…በአጋንንት ቸርቻሪው ግርማ በኩል የአቢይ አሕመድን አገዛዝ ለመቃወም የሚገርም ኅብረት የፈጠሩትን በአሜሪካ የሚኖሩ የተዋሕዶ ልጆችን ለመበታተን ሲባል በእነ ዳንኤል ክስረት የሴራ ፕላን የኢዜማና የግንቦት ሰባትን፣ እንዲሁም በማኅበረ ቅዱሳን ካባ በኢዜማ ቀሚስ ለብልጽግና በተገረዱ ደካሞች አማካኝነት የተፈበረከ ከፋፋይ አጀንዳ ነው።

• ዘበነ ለማ (ኦሮሞ)
• ደበበ እስጢፋኖስ (ኦሮሞ)
• ኤፍሬም እሸቴ (ኦሮሞ)
• ብርሃኑ ጎበና (ኦሮሞ) ነን ባይ የዘመነ ብልፅግና የመቅሰፍቱ በረከት ተቋዳሾችን ዝምታም አጥብቄ አወግዛለሁ።

• በዋሽንግተን የአቢይን አገዛዝ ለማውገዝ የታሰበውን ታላቅ የኦርቶዶክሳውያን ሰልፍ ለማኮላሸት ነው ግርማ ወደ አሜሪካ የመጣው። እነ አቤል ጋሼ፣ እነ ነአምን ዘለቀ እረፉ። እጃችሁን አንሱ።

~ ግርማም በዚያኑ እለት የፈውስ አገልግሎትእሰጣለሁ ብሎ ጠርቷል። ተልእኮው ይሄው ስለሆነ። ከግርማ ሴራ እና ከእናንተ ዓላማ የቱ እንደሚበልጥ እናያለን።

• በተረፈ ኦህዴድ በኦሮሚያ በትናንትናው ዕለት ፈንጂ አፈንድቷል። በጉጂ ዞን የሚጀመረው የኦሮሞ ዐመፅ ከቁጥጥር ውጪ ሊወጣ ይችላል። ለማንኛው የእነ ግርማን ሴራ ሳትንቁ ከፊታችን ላለው የዋንጫ ጨዋታ ተዘጋጁ። ንስሀ፣ ንስሀ፣ ንስሀ። ዐማራም እህልህን በጎተራ ክተት። ቅበርም። በየአብያተ ክርስቲያናቱም የሚገኙ ንዋያተ ቅዱሳቶችህንም ከወዲሁ ሸሽግ ቅበርም።
4.3K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 15:16:28
"…በእኔ መረዳት የአቢይ መንግሥት መቃወም ለጀመረው በአሜሪካ የሚኖሩ የተዋሕዶ ልጆችን ለመከፋፈል ሲባል ከብልጽግናው መንግሥት ተልእኮ ወስደው ክፉ ኢ-ክርስቲያናዊ ሥራ የጀመሩት እነዚህ አካላት ናቸው። ተጠያቂዎቹም እነዚህ ከታች የዘረዘርኳቸው ናቸው። እነርሱም…

• ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
• ዶክተር ቀሲስ ዘበነ
• ደበበ እስጢፋኖስ እና
• ማኅበረ ቅዱሳን ናቸው። ተጠያቂዎቹ እነዚህ ብቻ ናቸው ማለቴ ግን አይደለም። አይቶ ዝም ያለ ሁሉ በምድርም በሰማይም ይጠየቃል።

"…እንዴት…? ለሚለው ደግሞ ከታች ያስቀመጥኩትን የድምፅ መልእክት ተጋበዙልኝ። ሰብሰብ ብላችሁም ስሙልኝ። ይሄ የመጀመሪያዬ ነው። ማሟሟቂያ። ዋናውን የጭቃ ዥራፌን እያየሁ እጨምራለሁ። ዘመኑ ቆሻሻ ከቤተ መቅደስ የማጽጃ ዘመን ነው። እግዚአብሔር ሥራ ላይ ነው።

~ ከ1 ሰዓት በኋላ የአስተያየት መስጫውን ሰንዱቅ እከፍተዋለሁ። ምድረ አጋንንታም ውትፍትፍ ሰው መሳይ በሸንጎ ሁላ ኮመንት ስትሰጪ እየተጠነቀቅሽ። ደጋግመሽ አስበሽ ስጪ። አልያ ግን እቀስፍሻለሁ። አለቀ።
4.0K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 13:01:55
"…ከእኔ ጋር ናችሁ እንቀጥል…?

• ሁለት ቦታ አልረግጥም። በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ ስለሚታየው የጀትና የሮኬት ትርኢት አላወራም። አጅሬ ፒኮክ ደንብራ የምትሆነውን ያሳጣትን ተከትዬ አልንበጫበጭም። እንኳን በደርግ ጊዜ የነበረ ከዐማራ ክልል ተጭኖ ሸዋን ለማስፈራራት በመሃል አዲስ አበባ ለሚንጎማለል፣ በአፋር በረሃ ተሞክሮ የከሸፈ የሶቬት ስሪት ቆሼ ቆረቆንዳ፣ ቀለም ተቀብቶ ውርውር ለሚል አሮጌ መሳሪያ አይደለም የኔቶና የዓረብ ሊግ የጦር ሠራዊት ቢመጣ የተቆረጠን እህል ውኃ አይቀጥልም። የታችኛው የብአዴን ክንፍ ከሌሎች ክልሎች ጋር ወጥሯል። ኦህዴድ ኦነጎች በሌላ በኩል ከትግሬዋ ሂዊ ጋር በድሮ በሬ ሊያርሱ ወጥረዋል። ጨዋታው የዋንጫ ስለሆነ የግድ መሸናነፍ ይጠበቃል። በመደበኛ ሰዓት አቻ ቢለያዩ እንኳ በተጨማሪም ሰዓት ተሞክሮ በዚያም አቻ ቢወጡ የግድ በፍጹም ቅጣት አሸናፊው መለየት አለበት። ከባድ ነው ግን ግድ ነው። ይደፈርሳል ደግሞም ይጠራል።

"…እኔ እንዳልኳችሁ ዛሬ ውሎዬ አሜሪካ ነው። እኔና ወፎቼ የወሰነው እዚያ መዋል ነው። ሰሞኑን በሃገር ጉዳይ አንድ የሆነውን የአሜሪካን ነዋሪ የተዋሕዶ ልጅ ለመበታተን ተልእኮ ወስዶ የዘመተውን ይሄን የጨው ክምር መናድ አለብኝ። ከነከስኩ ሳላደማ እንደማልመለስ ታውቃላችሁ። እናም ሁለት ሰው እንኳ እንዲነቃ ካደረግኩ በቂዬ ነውና ውሎዬ አሜሪካ ነው የሚሆነው።

"…አዲስ ነገር ስላለ አዋሽ ባንክ ላይ የጀመርኩትን ዥለጣም ለዛሬ እገታዋለሁ። አንድ እጅግ አድርጌ ከማከብረው አብሮአደግ ወንድሜ፥ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በአንድ ወንበር ላይ ተቀምጠን የተማርን፣ በሥራውም በሃይማኖቱም የተመሰገነ ወንድሜ ጉዳዩን ጣልቃ ገብቶ ስለተማጸነኝ ለዛሬ አልተነፍስም። ውጤቱን አብረን እናየዋለን። እየጠበቅኩህ ነው መምህር…!

"…እህሳ ከእኔ ጋር ናችሁ ልቀጥል…?
4.2K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 13:01:55
ከምስጋና በኋላ…!

"…አዎ ቁጥሩ ከ3ሺ ያለፈ ሰው እግዚአብሔር ይመስገን ስላለልኝ አሁን በደስታ በቀጥታ ወደተለመደው ዕለታዊ መርሀ ግብሬ እገባለሁ።

"…ዛሬ አሜሪካም ኢትዮጵያም ገባ ወጣ ስንል ነው የምንውለው። ዳንኤል ክብረት ከአቡነ ፋኑኤል ጋር ተመሳጥሮ በአቢይ አሕመድ አገዛዝ ላይ ተቃውሞ ለማሰማት ወደ አደባባይ መውጣት የጀመረውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆችን ለመከፋፈል የተለከውን አጋንንት ቸርቻሪ በክፉ መናፍስት ሊቅ የሆነውን መልአከ አንከርት ግርማን፣ በጊዜ ሂደት እንኳ የእነ በጋሻው ትዝታው የተሃድሶው ኮተት ያለቀቀውን ደበበ እስጢፋኖስንና ሌሎችንም ስዠልጥ ነው የምውለው።

"…እኔ ይህን የማደርገው በግርማ ለሚታጠበውና ለሚጋጠው ለአሜሪካ ሕዝብ አዝኜ አይደለም። ግርማ በሰለጠነ ዓለም ላይ እየኖረ የማይሰለጥን እርጥብ ደነዝ ሰገጤ ካገኘማ ይጠበው። ራቁቱን ያስቀረው። ሲነገረው የማይሰማ ሕዝብ አሜሪካ ኖረ አፍሪካ ይበለው ምንአገባኝ። በአንድ የክፉ መንፈስ ቸርቻሪ፣ ከኢዩ ጩፋና ከእስራኤል ዳንሳ በምንም የማይለይ አጋንንታም ወመኔ ሃይማኖት በሌለው፣ በሰው ችግር እና ህማም ኑሮውን የሚገፋ ሸቃላ ነጋዴ የሌለ አንደኛ ኢንቨስተር በሆነ ሰው መሸወድ ለፈለገ ሕዝብ ሃዘኔታም የለኝ።

"…እኔ ተልእኮዬ በዚህ በአሜሪካ የብርድ ወቅት ዳንኤልና ከአንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን ሴሎች፣ ከአፍቃሬ ነዋዩ ከአቡነ ፋኑኤል ጋር ተመካክሮ በነውረኛው ደበበ እስጢፋኖስ በኩል የአሜሪካንን ህዝብ አንድነት በጭቅጭቅ ለመከፋፈል የተላከውን የብልፅግና አሽከር ግርማንና ተልእኮውን ማክሸፍ ነው። አዳሜ ለምን በአናትህ አትተከልም ለደንታህ ነው። የምጽፈውን በግድ ትጋታታለህ፣ በፔጄ ላይ መጥተህ አቀረሻለሁ ብትል ደግሞ ወገብ ዛላህን ብዬ በወሬ ጠኔ እደፋሃለሁ። ይኸው ነው።

"…ቆይቼ እመለሳለሁ…!
4.0K views10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 09:32:55
ይኸውልህ ወዳጄ…

"…በስድስት ክፉ ነገር ውስጥ ያድንሃል፥ በሰባትም ውስጥ ክፋት አትነካህም። በራብ ጊዜ ከሞት፥ በሰልፍም ከሰይፍ እጅ ያድንሃል። ከምላስ ጅራፍ ትሰወራለህ፤ ጥፋትም ሲመጣ አትፈራም። በጥፋትና በራብ ላይ ትስቃለህ፤ ከምድረ በዳ አራዊትም አትፈራም፤

"…ቃል ኪዳንህ ከምድረ በዳ ድንጋይ ጋር ይሆናልና የምድረ በዳም አራዊት ከአንተ ጋር ይስማማሉና። ድንኳንህም በሰላም እንዲሆን ታውቃለህ፤ በረትህን ትጐበኛለህ አንዳችም አይጐድልብህም። ዘርህም ታላቅ እንዲሆን፥ ትውልድህም እንደ ምድር ሣር እንዲሆን ታውቃለህ። በወራቱ የእህሉ ነዶ ወደ አውድማ እንዲገባ፥ በረጅም ዕድሜ ወደ መቃብር ትገባለህ። ኢዮ 5፥ 19-26

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
4.4K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 09:32:55
“…ስለዚህ የኤርትራ ትግሬንና ሞኙን ዐማራ ስለሚግጥ፣ ስለሚዘርፍ፣ ስለሚያደነዝዝ፣ የኦፒዲኦ ብልፅግና ሠራዊት ከመነሻው ጀምሮ ሴራውን ባውቅ መረጃው ቢኖረኝም አንዳች ነገር ላለመተንፈስ ለራሴ ቃል ገብቼ ዝም፣ ጭጭ፣ ጮጋ ብዬ አርፌ ተቀምጬ ነበር። ዛሬ ግን ብዙዎች ከአማሪካ እየደወሉ "ዘመዴ በማርያም፣ በምትወዳት በእመቤቴ ይቅር በለን። በዚህ ሰውዬ ጉዳይ ብዙ እንናደድብህ ነበር። ዛሬ ግን በዓይናችን በብረቱ አየን። ዘመዴ አንተ ልክ ነበርክ" ሲሉኝ ውለዋል። እንዲያም ሆኖ በልቤ "ይበልህ፣ ይጋጥህ፣ አፈር ከደቼ ያብላህ እያልኩ" በአፌ ግን ኧረ ምን አገባኝ እኔ። እኔ አሁን ሌላ ሥራ ላይ ነኝ በማለት ስመልስ አምሽቻለሁ። በእውነት ከዚህ የተነሣ ዛሬ በቴሌግራም ቻናሌ መጻፍ የሚገባኝን ሳልጽፍ እንዲሁ ስነታረክ ውዬ አምሽቻለሁ።

"…አሁንም ይሄን ማስታወሻ የጻፍኩት መልአከ አንከርት ግርማ ጋር ሄዳችሁ ለፈውስ አንድ አንድ ሺ ዶላር ከፈልን እያላችሁ ስታዝጉኝ የዋላችሁ ጅላፎ ንክር 100 ኪሎ የአሜሪካ ርጥብ ሰገጤዎች እንዳትደውሉልኝ ለማለት ነው። ሰው አሜሪካ ድረስ ሄዶም ካልሰለጠነ፣ ካልነቃ ምን ታደርገዋለህ? ይበልህ፣ ይጠልዝህ፣ ይጋጥህ። ዥልጥ ሁላ። ቱ…! ኧረ እንደው ምን ተሻለኝ በማርያም።

"…ቀሲስ ደበበ እስጢፋኖስ ግን ጠብቀኝ። አንት ከንቱ። ከዚያ ሁሉ ጭንቅ አውጥቼህ፣ ያንን ሁሉ የፍርድ ቤት ክስ እግር ላይ ወድቄ አስቁሜልህ፣ ዛሬ እንዲህ በስመ ኦሮሞነት ለብልፅግና ገረድ ሆነህ ይሄን አጋንንት አከፋፋይ መልአከ አንከርት የሆነ ሰውዬ አምጥተህ የተዋሕዶን ልጆች መጫወቻ እንዳደረግክ ብምርህ አይማረኝ። ዘማሪት ፋንቱ ወልዴን ምስክር ጠርቼ አንተን እንዲህ በድፍረት ከምታረክሰው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አንገትህን ሰብረህ በፀፀት እንድትንገበገብ ያለደረግኩህ እንደሆነ እኔ ዘመዴ አይደለሁም።

• ጠብቀኝ
4.2K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-28 09:32:55
ኡሙንዱኖእሹ…?

"…ወፌ ናት ይሄን ቪድዮ የላከችልኝ።

~ ምንድነው? አለኳት።

• ይኸውልህ ዘመዴ አጅሪት ፒኮክ ከመገናኛ እስከ ጦር ኃይሎች ድረስ መንገድ ዘግታ በዚህ ምሽት ከባድ መሳሪያ በጫኑና በወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የታጀበ ወታደራዊ ትርኢት እያሳየች ነው አለችኝ። አይ የፒፖክ ነገር

~ በዚህ ምሽት ለማን አልኳት።

• እንጃለቱ ብላኝ ቆይ እስኪ ቤተ መንግሥት አካባቢ ልሂድ ብላኝ ነካችው።

"…ለማንኛውም አቢይ ማወቅ ያለበት ነገርየው ማኔ ቴቄል ፋሬስ ነው። ደግሞም “እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፥ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፥ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።” መዝ 127፥1። አለቀ።

"…ዐማራ እህልህን ቆጥብ። የተከመረ የወረቀት ብር ተሸክመህ በኋላ ጣጣ ውስጥ እንዳትገባ። ምንጃር እና ጎንደር እህል በገፍ መሸጥ ማቆማችሁን ሰምቻለሁ። ከወዲሁ ነቄ ለማለታችሁ ምልክት ነው የሚሉ መተርጉማን አሉ። እንዲያ ነው።

"…ወፍ የለም። ቡካቲያም ፒኮካም ሁላ…!
4.3K views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 21:02:59
ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ

፯፦በዳውሮ ሀገረ ስብከት የወልደ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ስብከት ኬላን ወደ መቃኞ ቤተ ክርስቲያን ለመቀየር ገንዘባቸውን ያዋጡ ባለማዕተቦች ስም ዝርዝር።

፩፦ ዓምደ ማርያም     100,000
፪፦ ወለተ ህይወት     100,000
፫፦ ወለተ ዮሐንስ         70,000
፬፦ ጽጌ ማርያም          60,000 ገብረ ኪዳን   
፭፦ ጽጌ ማርያም          50,000 ገብረ ሕይወት
፮፦ ወልደ ቂርቆስ         43,000 ቢንያም
፯፦ ወልደ ጊዮርጊስ      41,000
፰፦ ወለተ ዮሐንስ         40,000 ራሄል 
፱፦ ወልደ ተ/ሃይማኖት  35,000 እህተ ኪዳን
፲፦ ፍቅርተ ዮሐንስ        30,000
፲፩፦ ወለተ ገብርኤል     24,000
፲፪፦ ወለተ ሃና               25,000
፲፫፦ወለተ ማርያም       21,000 ፍቅረ ሥላሴ
፲፬፦ ወለተ ሚካኤል     21,000 ፍቅርተ ዮሐንስ
፲፭፦ ወለተ ኢየሱስ        20,000
፲፮፦ እህተ ሚካኤል          10,000
፲፯፦ እማሆይጽጌ ማርያም  10,000

አጠቃላይ ድምር = 700,000 ብር

~ የነፍስ ዋጋ ያድርግላችሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

• ቃል የገባችሁ ባለማዕተብ ወንድሞች ደውሉልኝ እና የአብያተ ክርስቲያናቱን የባንክ አካውንት ውሰዱልኝ።
3.0K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-27 21:02:58
ሻሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ለሰማዕቱ~

፮፦ዳራማሎ ወረዳ ሻሌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስብከት ኬላን ወደ መቃኞ ቤተ ክርስቲያን ለመቀየር ገንዘባቸውን ያዋጡ ባለማዕተቦች ስም ዝርዝር።

፩ኛ፦ ለዕከ ማርያም       100,000  ዲን መላኩ
፪ኛ፦ ወልደ ጊዮርጊስ       60,000 ትርሲተ ገብርኤል
፫ኛ፦ ወልደ ትንሣኤ         60,000 ወለተ ሥላሴ
፬ኛ፦ ወልደ ቂርቆስ          57,000 ቢንያም
፭ኛ፦ አክሊለ ገብርኤል    50,000 ጸዳለ ማርያም
፮ኛ፦ እህተ ማርያም         50,000 ሳራ
፯ኛ፦ ክንፈ ሚካኤል        50,000 እህተ ወልድ
፰ኛ፦ ምህረተ አብ           50,000 ቲጂ
፱ኛ፦ ፅጌ ማርያም           50,000  ኃይለ ጊዮርጊስ
፲ኛ፦ ወለተ ኢየሱስ          40,000 ፍቅርተ ሥላሴ
፩ኛ፦ ፅጌ ማርያም           40,000  ቲጂ
፲፩፦ ፍቅረ ሥላሴ           30,000 ፍቅርተ ዮሐንስ      
፲፪፦ ኃይል ጊዮርጊስ       20,000  ግዕዝ
፲፫፦ ብርሃነ መስቀል       20,000  ሄኖክ ታምራት 
፲፬፦ መቅደሰ ማርያም     20,000 ብርሃነ ሥላሴ  
፲፭፦ ወለተ ማርያም         11,000 ትእግስት 

በአጠቃላይ 708.000 ብር ተዋጥቷል።  

~ የነፍስ ዋጋ ያድርግላችሁ። እግዚአብሔር ይስጥልኝ።

• ቃል የገባችሁ ባለማዕተብ ወንድሞች ደውሉልኝ እና የአብያተ ክርስቲያናቱን የባንክ አካውንት ውሰዱልኝ።
2.8K views18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ