Get Mystery Box with random crypto!

﷽ዚክረ መንዙማﷺ

የቴሌግራም ቻናል አርማ zekr_menzuma — ﷽ዚክረ መንዙማﷺ
የቴሌግራም ቻናል አርማ zekr_menzuma — ﷽ዚክረ መንዙማﷺ
የሰርጥ አድራሻ: @zekr_menzuma
ምድቦች: ሙዚቃ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.48K
የሰርጥ መግለጫ

የኛን #You_Tube ቻናል ለማግኝት ይሄን ይጫኑ⬇️👇
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube
ጥያቄ ወይም አስተተያየት ካላቹ በቦት
@ZEKR_MENZUMA_bot ተጠቅመዉ ያድርሱን✍️
የመውሊድ ሀድራ ቪዲዮ በድምፅ የተቀዳ መንዙማ ያላቹ ላኩልን
{ @ZEKR_MENZUMA_bot }

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-09-16 10:28:42
https://youtube.com/shorts/ShLwAtgSP-s?feature=share
3.0K views07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 08:52:14 ሱረቱል ካህፍ || በሰፍዋን ሸይክ አህመዲን


2.7K views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 20:44:06
በሚገርም የድምፅ ቀለም ድምፅ መረዋው ሙዐዝ ሀቢብ የመንዙማዎች ቁንጮ የሆነውን ሙከረሙ መንዙማ እንሆ ተለቋል








2.7K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 08:46:07
ሀያቴን ለእርሶ ብያለዉ ጀባ || መታየት ያለበት የልጆች መንዙማ || ማሻአላህ በሏቸዉ || ጀማሉል አለም || ZEKR MENZUMA & NESHIDA TUBE









3.2K views05:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 20:54:28 ሀያቴን ለእርሶ ብያለዉ ጀባ || መታየት ያለበት የልጆች መንዙማ || ማሻአላህ በሏቸዉ || ጀማሉል አለም || ZEKR MENZUMA & NESHIDA TUBE









2.8K views17:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 13:28:53 ጎህ ቀደደ። የሱብሒ ሰላት በነቢያችን ሰዐወ ኢማምነት ተሰገደ...ልክ ረሱል ሰዐወ ሲያሰላምቱ ከደጅ በኩል ከፍ ባለ ድምፅ፦ «አዋጅ!!! አቡል ዓስን በኔ ከለላ አስገብቼዋለሁ....» የሚል ጥሪ መስጅዱን አስተጋባ።

«ሰዎች የሰማሁትን ሰማችሁ...?» በማለት ረሱል ሰዐወ ጠየቁ።
«አዎን አንቱ ያላህ መልዕክተኛ ሰምተናል» የሰሀቦቹ ምላሽ ነበር።

ከወደኋላ በኩል ዘይነብ ንግግሯን ቀጠለች፦ «አንቱ ያላህ መልዕክተኛ! አቡል ዓስ የአክስቴ ልጅ ከመሆኑም ባሻገር የልጆቼ አባት ነው፤ ከለላዬን ሰጥቼዋለሁ»

ነቢያችን ቁጭ ካሉበት ብድግ አሉ፤ ከሰሓባዎች ፊትም ቆሙ፦ «ሰዎች ሆይ! ይህ ሰው ዝምድናው አላታለለኝም። አወራኝ፣ እውነትም ነገረኝ። ቃል ገባልኝ፤ ቃሉንም ሞላልኝ።

ፍቃዳችሁ ከሆነ ንብረቱን መልሳችሁለት እሱንም ብትለቁት እኔ እደሰታለሁ፤ ግና እንቢ ካላችሁ ያሻችሁን አድርጉ። አልወቅሳችሁም፣ ሀቁ የናንተ ነው።» ብለው ንግግር አደረጉ።

«አንቱን ካስደሰተማ ንብረቱን እንሰጠዋለን፤ እንለቀዋለንም።» በማለት ታዛዥነታቸውን አስመሰከሩ።

ረሱልም ሰዐወ «ዘይነብ! ከለላ የሰጠሽውን ሰው ከለላ ሰጥተናል።» ብለው ሸኟት። ገና ቤቷ ከመግባቷ በሯ ተንኳኳ፤ ረሱል ነበሩ፦ «ልጄ! ጥሩ አስተናግጂው። የልጆችሽ አባት ነው፤ የአክስትሽም ልጅ ነው። ነገር ግን እንዳትቀራረቡ እስኪሰልም እሱ ላንቺ እርም ነው» ብለው መከሯት።

ያለ ምንም ማስተባበያ «እሺ የአላህ መልዕክተኛ» ብላ መለሰችላቸው። በሩ ተዘጋ፤ ወደ አቡል ዓስ ዞር ብላ፦ «መለያየትን እንዲህ እንደቀላል ተመለከትከውን...? ምናለ ብትሰልም» በማለት ታግባባው ጀመር።

«በፍፁም» የአቡል ዓስ ምላሽ ነበር።

አቡል ዓስ ንብረቱ ተመልሶለት ወደ መካ ተመለሰ። ልክ ከተማዋን እንደገባ ሰዎችን ሰብስቦ፦ «ሰዎች ሆይ! ይኸው ንብረቶቻችሁ።እኔ ጋር የቀረ ንብረት አላችሁ? » በማለት ጠየቀ።

«በመልካም ተመንዳ፤ ቃልህን ሞልተኻል።» ብለው መለሱለት።

እዚያው መሃላቸው ቁሞ፦ «አሽሀዱ አላ ኢላሃ ኢለላህ....» በማለት እስልምናን በይፋ ተቀበለ።

ጉዞ ወደ ነቢዩ ሰዐወ መገኛ መዲና....

ሌሊት ላይ ከመዲና ደረሰ።
«ያረሱለላህ! ትናንት ከለላዎን ሰጡኝ፤ እኔም ዛሬ ከልቤ እስልምናን ተቀብዬ መጥቻለሁ።» አላቸው።

ንግግሩን ቀጥለ፦ «አንቱ ያላህ መልዕክተኛ! ዘይነብን ዳግም ልቆራኛት ይፈቅዱልኛል...?»

እጁን ያዝ አደረጉት'ና፦ «ና ተከተለኝ።» ብለው ከዘይነብ ደጃፍ አደረሱት።
በሌሊት በሯ ተንኳኳ፤ ስትከፍተው አባትዋ እና ተናፋቂ ባሏ በር ላይ ናቸው።

«የአክስትሽ ልጅ ዳግም ካንች ጋር እንዳቆራኘው ጠይቆኛል። ፍቃደኛ ነሽ?» በማለት አባቷ ጠየቋት።

የደስታ ፊቷ ቀልቶ ምትለው ቢጠፋት ፈገግ አለች። ዳግም ከስድስት አመታት በኋላ ፍቅር ፍቅሯን አቀፈች።

አንድ የፍቅር ህዳሴ አመት ተቆጠረ። አቡል ዓስ ፅጌረዳዋን አሽትቶ ሳይጠግብ ሞት ነጠቀው።

ረሱል ሰዐወ ሲያፅናኑትም፦ «ያ ረሱለላህ! ወላሂ እኔ ያለሷ ዱንያን አልችልም» እያለ እዬዬ ይል ነበር።

አንድ ሙሉ የሀዘን አመትን ካሳለፈ በኋላ አቡል ዓስ ፍቅሩን ተከትሎ ወዳሸለበችበት እሱም አሸለበ።

ፍቅርም መዝገቡ ተዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት ተመለሰ!

Sefwan sheik Ahmedin
_________________________________

ምንጭ፦
صور من حياة الصحابة عبد الرحمن رأفت الباشا

የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCW7Mi9alF-Wnl9MRyll7g5A

Facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

Join Tg
https://t.me/ZEKR_MENZUMA
3.1K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-13 13:28:05 አቡል ዓስ ወደ ረሱላችን ሰዐወ ሂዶ፦ «ትልቋን ልጅህን ዘይነብን እንድትድረኝ እጠይቅሀለሁ» አላቸው።
#አደብ

እሳቸውም፦ «ፍቃዷን ሳላረጋግጥ አልድርህም» አሉት።
#ህግ

ረሱላችን ሰዐወ ወደ ልጃቸው ዘይነብ ሂደው፦ «የአክስትሽ ልጅ እኔ ዘንድ መጥቶ አንችን ለምኖኛል፤ ባልሽ እንዲሆን ትፈቅጃለሽ ወይ?» ብለው ጠየቋት።አፍራ ፈገግ በማለት አጎነበሰች።
#ሀያእ

ጋብቻቸው ተፈፅሞ አስደናቂውን የትዳራቸውን ህይወት ሊጀምሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ።
#ስኬት

አባቷ በነብይነት ሲበሰር ዕውነተኝነቱን ያመነችው ልጅት ዘይነብ ባሏ ለንግድ ጉዞ በሄደበት እስልምናን ተበብላ ጠበቀችው።
#ዕምነት

ልክ ከጉዞው ተመልሶ እቤቱ ሲገባ፦ «ትልቅ የምስራች ይዠልሀለሁ» ስትለው ምንም ሳይል ትቷት ከቤት ወጣ።
#አክባሪነት

ልጅት ዘይነብ ደንግጣ ባሏን እየተከተለች በመውጣት፦ «አባቴ በነብይነት ተልኳል፤ እኔም ሰልሚያለሁ» ስትለው
«ታድያ መጀመሪያውኑ አትነግሪኝም ነበር» ብሎ መለሰላት።

ልጅት ዘይነብም፦ «አባቴን ፍፁም አላስተባብልም፤ እሱም አይዋሽም። እኔ ብቻም ሳልሆን እናቴ እና እህቶቼም ጭምር ነን የሰለምነው» ብላ ንግግሯን ቀጠለች።
#አቋም

«የአጎቴ ልጅ ዐሊይ ሰልሟል፤ የአጎትህ ልጅ ዑስማንም እንደዝያው...ጓደኛህ አቡ በክርም ከኛው ነው» በማለት አብራራችለት።

እሱም፦ «እኔ እንደሆን ሚስቱን ለማስደሰት ሲል የጎሳውን ሀይማኖት ትቶ ሰለመ ተብሎ እንዲወራብኝ አልሻም። ይቅርታ አድርጊልኝ'ና አባትሽም ቢሆን ቀጣፊ እንዳልሆኑ አውቃለሁ» አላት።
#የሰከነ_ውይይት

እሷም፦ « እኔ ይቅር ካላልኩህ ማን ይልሀል?...ነገር ግን ዕውነት እስኪገለፅልህ ድረስ እረዳኻለሁ።» አለችው።
#መናበብ

(ለ20 አመታት ያህል ቃሏን ጠብቃ አብራው ቆየች።)

ዘይነብ በእስልምናዋ፤ ባሏ በክህደቱ ላይ ፀንተው ትዳራቸውን ባሟሟቁበት ግዜ ከመካ ወደ መዲና የሚደረገው የስደት ጉዞ ተደነገገ።

ልጅት ዘይነብም ወደ አባቷ ዘንድ ሂዳ፦ «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! እዚሁ ከባሌ ጋር እንድቀር ይፈቅዱልኛል» ስትል ጠየቀቻቸው።
#ፍቅር

ፈቀዱላትም።
#እዝነት

ሙስሊሞች ከመካ ወደ መዲና ተሰደው ልጅት ዘይነብ እዚሁ መካ ላይ ከባሏ ጋር ቀረች። ከግዜያት በኋላ ሙሀመድን ሰዐወ እና የመካ መሳፍንቶችን በአንድ የጦር ሜዳ ላይ የምታፋጥጠው የበድር ዘመቻ ቀጠሮዋ ቀረበ።

የልጅት ዘይነብ ባለቤት አቡል ዐስ'ም ከመካ መሳፍንቶች ተርታ ተሰልፎ የሚስቱን አባት ሊዋጋ ወሰነ።

ባለቤቷ አባቷን ሊዋጋ ሄደ፤ እሷ ቤቷ ቁጭ ብላ እያለቀሰች፦ «አላህ ሆይ! የድል ጮራህ ፈንጥቃ ልጆቼን የቲም እንዳታደርግብኝ ስፈራ፤ አባቴንም እንዳላጣው ሰጋሁ» ስትል ትውላለች።
#ምርጫ_አልባ

የበድር ጦርነት ዘመቻ ተጀመረ፤ በድር የድል ዙፋኗን ለሙሀመድ ሰዐወ ሸልማ፤ የመካ መሳፍንቶችን አስክሬን ከጦርነት አውድማው በመበተን የተቀሩትን መሳፍንት በሙሀመድ ሰዐወ ምርኮኛ አድርጋ የጦር ድንኳኗን አፈረሰች።

የጦርነት ዜናው የመካ መንደሮችን አጥለቀለቀ፤ ልጅት ዘይነብ ዜናውን ለመስማት ወጣ ብላ፦ «አባቴ እንዴት ሆነ...?» ስትል ትጠይቃለች። «ድልን ተጎናፅፏል» ስትባል ሱጁድ ትወርዳለች።

ከሱጁዷ ብድግ ብላ፦«ባለቤቴስ እንዴት ሆነ...?» ብላ ስትጠይቅ «የሙሀመድ ምርኮኛ ሁኗል» የሚል መርዶ ትሰማለች።

«እንግዲህ ባለቤቴን የምቤዥበት መስዋዕተ-ምትክ ወደ መዲና እልካለሁ» ብላ ትወስናለች።
#ብልሀት

ውድ ባለቤቷን ከተማረከበት ነፃ ለማስወጣት የምትቤዥለትን ውድ እቃዎች ስታሰላስል ከእናቷ ከዲጃ በኩል የተሰጣትን የአንገት ሀብል ብቁ ሆኖ ታያት'ና ወሰነችበት።

የባሏን መቤዥያ ይዞ ወደ መዲና የሄደው የባሏ ወንድም ልክ መዲና ሲገባ ሙሀመድን ሰዐወ ቁጭ ብለው መቤዥያዎችን እየተረከቡ ምርኮኞችን ሲለቁ ደረሰ።

እሱም ከዘይነብ የተረከበውን የባለቤቷን መቤዥያ ከሙሀመድ ሰዐወ ዘንድ ከተደረደሩት መቤዥያዎች መሀል ቁጭ አደረገ።

ሙሀመድም ሰዐወ መቤዥያዎችን ሲቆጥሩ በመሀል የድሮ የወጣትነት የፍቅር ዘመናቸውን የሚያስታውሳቸውን አንድ የአንገት ሀብል ተመለከቱ። ውድ ሟች ሚስታቸው ትዝ አለቻቸው።

በለሰለሰ ድምፅ፦ «ይህ የማን ነው...?» ሲሉ ጠየቁ።

«ይህ የአቡል ዓስ መቤዥያ(መስዋዕተ-ምትክ) ነው።» ተብሎ ተነገራቸው።
«ይህ የከዲጃ ሀብል ነበር» ብለው እቀረቀሩ።

አንገታቸው ዝቅ አለ፣ ፍቅርት ከዲጃ ትዝታዎቿ ከመቃብር በላይ ዳግም ህያው ሆነው የነቢዩን ጉንጮች በእንባ አራሳቸው።

ፊታቸውን ጠራርገው ከዙርያዎቻቸው የተሰበሰቡትን ሰሀቦች እየተመለከቱ፦ «ይህ ሰው በዝምድና ተቆራኝተነዋል፤ ፍቃዳችሁ ከሆነ እንፍታው...? ለዘይነብም ሀብሏን እንመልስላት...?» በማለት ጠየቁ።
#መተናነስ

«አዎ ይመለስ አንቱ ያላህ መልዕክተኛ» የሰሀባዎች ምላሽ ነበር።
#ስነስርአት

መልዕክተኛው ሰዐወ አቡል ዓስን አስጠሩት፦ «ይህን ሀብል ለዘይነብ መልሰህ ስጣት "በከዲጃ ሀብል አትጫወችብኝ" በላትም» ብለው ለቀቁት።

ዳግም ጠሩት፦ «አንተ አቡል ዓስ! አንዴ ለብቻህ ላናግርህ...?» ወደ ዳር ወሰዱት.....

«ይኸውልህ አቡል ዓስ! አላህ በካፊሮች እና በሙስሊሞች መካከል እንድለያይ አዞኛል። ስትመለስ ልጄን ትልክልኝ...?» በማለት ጠየቁት።

«እሺ እልካለሁ» አለ።
#ወንድነት

ጉዞውን ቀጠለ...፤ በመዲና እና በመካ መካከል ያሉትን በረሃዎች አቋርጦ የመካ ከተማ መዳራሻዎች ላይ ሲቀረብ ሚስቱ ዘይነብ ልትቀበለው ወጥታ አገኛት።

ገና ሲገናኙ፦«ልለይሽ ነው» ብሎ አስደነገጣት።
«ወዴት ነው የምትለየኝ...?» ድንጋጤ ፊቷ ላይ እየተነበበ።

«እኔ አይደለሁም የምለይሽ፤ አንቺ ነሽ የምትለዪኝ። ወደ አባትሽ እልክሻለሁ» አላት።
#ቃል_ኪዳን

ድንጋጤዋ እየጨመረ፦ «ለምን...?» አለችው።
«እንድንለያይ ተወስኗል'ና ወደ አባትሽ ትመለሻለሽ» አላት።

«እባክህ ስለም'ና አብረን እንሂድ» ስትል ተማፀነችው።
«በፍፁም» የሱ ምላሽ ነበር።

ሁለት ልጆቿን ይዛ የአባቷ መገኛ ወደሆነችው መዲና ተመመች። ልክ መዲና ገብታ ከአባቷ ጓዳ ከማረፏ ነበር የትዳር ጥያቄዎች ይጎርፉላት የጀመረው።

ምንም እንኳን ለ 6 ተከታታይ አመታት የትዳር ጥያቄዎች ከትላልቅ ሰሀባዎች ቢቀርቡላትም የባሏን የ"ይመለሳል" ተስፋ የሰነቀችው ዘይነብ በብቸኝነቷ ፀንታ ጠበቀች።

ከ 6 አመታት በኋላ ከመካ ወደ ሻም ከሚሄዱት የሲራራ ነጋዴዎች ጋር አንድ ላይ በመሆን አቡል ዓስ ጉዞ ጀመረ።

በጉዞ ላይ ሳሉ ከውስን ሰሀባዎች ጋር መዲና ላይ ፊት ለፊት ተገጣጠሙ። ንብረታቸው መካ ላይ ተወርሶ የግር ሳት የሆነባቸው ሰሀባዎችም ያገኙትን እድል ተጠቅመው የጫኑትን ግመሎች ማረኩባቸው።

ሰዓቱ ከሱብሒ በፊት ነው፣ የነቢዩ ሰዐወ ከተማ ነዋሪያን ቤታቸው ገብተው ከተማዋ ፀጥ...ብላለች። በዚህ መሀል አቡል ዓስ የዘይነብን ቤት አጠያይቆ በውድቅት ሌሊት በሯን አንኳካ።

ልክ በሯን ከፍታ እሱ መሆኑን ስታረጋግጥ፦ «ሰልመህ ነው የመጣኸው...?» በማለት ጠየቀችው።
#ተስፋ

«ኧረ አምልጬ ነው የመጣሁት...» ብሎ መለሰላት።
ጥያቄዋን ይቀበላት ዘንድ በስስት እያየችው፦ «እና ትሰልማለህ...?» አለችው።

«በፍፁም...» ብሎ ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ መለሰላት።
በዲን ማስገደድ የለም'ና «እንግዲያውስ አብሽር እንኳን ደህና መጣህ የልጆቼ አባት፣ የአክስቴ ልጅ....» ብላ አስገባችው።
#ውለታ
2.6K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-11 21:48:05
#ሼይህ_አብዱልወሀብ
የሚገርም ሀድራ መንዙማ መታየት ያለበት ሀድራ ይሄን ይጫኑ











facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886
3.8K viewsedited  18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 21:42:17 ታላቅ የሀገራችን ኡለማ ሀጅ ሙሀመድ ራፊዕ ረሂመሁላህ
=========
በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሀረም መስጂድ (መካ) ዒማም
የሆኑትን ሸይኽ አብዱራህማን ሱደይስን ያስቀሩ፣ያስተማሩ
ታላቅ ኢትዮጵያዊ አሊም ሸይኽ ሙሀመድ ራፊዕ(ረሂመሁላህ)
ማን ናቸው?
-
የዒልም ጎተራ የሆኑት ሸይኽ ሙሀመድ ራፊዕ ረሂመሁሏህ
★★★★★★★★★★
ሀጂ ሙሀመድ ራፊዕ በ1898 አመተ ልደት አካባቢ በደቡብ
ወሎ በቃሉ ወረዳ በገርባ ከተማ የሁለት ሰዓት የእግር መንገድ
የሚያስኬድ እርጎየ ተብሎ በሚታወቅ የገጠር መንደር ተወለዱ።
በልጅነታቸው በተወለዱበት አካባቢ አህመዲያ በሚባሉ ሸይኽ
ቅዱስ ቁርዓንን ቀሩ ።
ቁዱስ ቁርዓንን እንዳጠናቀቁ የፊቂህ ትምህርት በታላቁ ሸይኽ
ላይ በሸህ ሙሀመድ ሷዲቅ በጎጃም ( በደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ
የምትገኝ የኢልም መንደር ) ለተከታታይ አስራ አንድ ዓመታት
የፊቅህ ትምህርት በጥልቅ ተማሩ ።
በወሎ በሚገኙ ታላላቅ የዓረብኛ ቋንቋ ሊቃውንት ዘንድ
በመሄድም ለረጅም ዓመታት የነህው ፣ የሶርፍ ፣ የበላጋ ፣
የመንጢቅና የመሳሰሉትን የዓረብኛ ቋንቋ መስኮች በሰፊው
ተምረዋል ።
ከዚያም ወደ ራያ አካባቢ በማቅናት በግብፁ አል አዝሃር
ዩኒቨርሲቲ ተመርቀው ከመጡት የሀዲስ ሊቅ ሙፍቲ ሙሀመድ
ሲራጅ ( ሙፍቲ ራያ ) ዘንድ በመሄድ ለተወሰነ ጊዜ ሀዲስ አጠኑ

በመቀጠልም በሸኻቸው ጠቋሚነት ወደ ሱዳን ሀገር በማቅናት
ከታላላቅ ዓሊሞች ፣የተውሒድ ፣ የሀዲስ ፣ የፊቅህና የተፍሲር
ትምህርቶችን በሚገባ ተከታትለዋል ።
በ1944 ዓ•ል ሀጅ ለማድረግ ወደ መካ ባቀኑበት ወቅት ታዋቂ
በሆነው የመካ ዳረል ሀዲስ ለአምስት ዓመታት ሀዲስን ተማሩ ።
በሀዲስ ሲልሲላ እጅግ ዝነኛ የነበሩት ዓሊም ሸህ ሙሀመድ አል
ፓኪስታኒ ላይ ኩቱቡ ሲታን አጠናቀቁ ።
ከዚያም በመቀጠል በሳዑድ አረቢያ የወቅቱ ሙፍቲ በነበሩት
ሸይኽ አብዱል ዓዚዝ ኢብኑ ባዝ ጋባዥነት መካ መስጂደል
ሀረም ውስጥ ለተከታታይ አስራ አንድ ዓመት አስተማሩ
(አስቀሩ)።
መድረሰተል ሙሀጂሪን በተባለ ታዋቂ ት/ት ቤት የማይነጥፍ
ዕውቀታቸውን አካፈሉ።
በእርሳቸው ተምረው ለቁም ነገር ከበቁት መካከል
የሳዑዲ አረቢያ የፓርላማ ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ሷሊህ
ኢብን አብዱሏህ ኡወይድ እና
የታላቁ ሀረም መስጂድ ዒማም ሸይኽ አብዱራህማን
ሱደይስ ተጠቃሽ ናቸው ።
ከአስራ ስድስት ዓመታት የመካ ቆይታ በኋላ በሸህ አለዊ አባስ
አልማሊክ " መካና መዲና ላይ ዳረል ሀዲስ አለ ፣ ኢትዮጵያ
ሄደህ ዳረል ሀዲስ መመስረት አለብህ " የሚል ምክር
ተሰጥቷቸው ምክሩንም በመቀበል ወደሀገራቸው ኢትዮጵያ
በመመለስ ወደ ተወለዱበት የገጠር ከተማ በመግባት ሀዲስን
ማስተማር ጀመሩ ።
በርካታ ደረሶች ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች እርሳቸው
ወዳሉበት ቦታ በማቅናት ሀዲስን መቅሰም ጀመሩ ።
ሆኖም ከደርግ አብዮት ጋር በተያያዘ በሀገራችን በነበረው
አለመረጋጋት ደረሶቻቸው ተበተኑ ።
በዚህ ጊዜ ትልቅ ሸይኽ የሆኑትና የሸህ ዒሣ ሀምዛ ልጅ የሆኑት
ሺህ አለቃ ሱልጣን ቡታጅራ አካባቢ በተሰራው መስጂድ ሀዲስ
እንዲያስተምሩ በላኩላቸው መልዕክት መሰረት ወደ አዲስ አበባ
አቀኑ ።
አዲስ አበባ እንደገቡም ሀጂ ዘይኑ (ራህመቱላሂ አለይህ)
አግኝተዋቸው እርሳቸው ቤት ሀዲስ እንዲያስተምሩ አደረጉ ።
የወቅቱ የእስልምና ጉዳዮች ሊቀ መንበርና መስራች እንዲሁም
የታላቁ አንዋር መስጂድ ዒማም ሀጂ ሙሀመድ ሳኒ ሀቢብ
(ራህመቱላሂ አለይህ) ጥሪ አድርገውላቸው በታላቁ አንዋር
መስጂድ ውስጥ ማስተማር (ማስቀራት) ጀመሩ ። ክፍል ሁለት ይቀጥላል ።
#ዚክረ_መንዙማ ፔጁን ላይክና ሸር ያድርጉና እውቀተወን ያዳብሩ
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886
1.2K views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 21:42:12
ታላቅ የሀገራችን ኡለማ ሀጅ ሙሀመድ ራፊዕ ረሂመሁላህ
=========
በአሁኑ ወቅት የታላቁ ሀረም መስጂድ (መካ) ዒማም
የሆኑትን ሸይኽ አብዱራህማን ሱደይስን ያስቀሩ፣ያስተማሩ
ታላቅ ኢትዮጵያዊ አሊም ሸይኽ ሙሀመድ ራፊዕ(ረሂመሁላህ)
ማን ናቸው?
-
1.1K views18:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ