2022-09-02 12:27:51
ታዋቂዋ የአለም ሀብታም ዲዛይነር እና ፀሀፊ ክሪስዳ ሮዲሪጌዝ በካንሰር በሽታ ከመሞቷ በፊት ማስታወሻዋ ላይ እንዲህ ብላ ፅፋ ነበር !
1 _ በዓለም ላይ አሉ ከሚባሉ ውድ መኪናዎች ውስጥ አንዱ በኔ ገራጂ የተቀመጠ ነው ። አሁን ግን በዊልቸር ነው የምንቀሳቀሰው !
2 _ቤት ውስጥ በምርጥ ዲዛይነሮች የተሰሩ ውድ የሆኑ የሚያምሩ ልብሶች እና ጫማዎች አሉኝ ! አሁን ግን ከሆስፒታል በተሰጠኝ ስስ ጨርቅ ነው ገላዬን የሸፈንኩት !
3 _ ባንክ አካውንቴ ላይ ከበቂ በላይ ገንዘብ አለኝ ግን እሱን አሁን ልጠቀምበት አልችልም !
4 _ ቤቴ ፓላስ የሚባል አይነት ነው ግን እኔ አሁን ሆስፒታል ውስጥ በምትገኝ ትንሽዬ አልጋ ላይ ነው የተኛሁት !
5 _ ካንዱ ባለ አምስት ኮኮብ ሆቴል እንዳሻኝ ወደ አንዱ ባለ አምስት ኮከብ ሆቴል እንሸራሸር የነበርኩ ሴትዮ አሁን እዛው ሆስፒታል ውስጥ ካንዱ የላቦራቶሪ ክፍል ወደ ሌላኛው ላቦራቶሪ ክፍል መመላለስ ግዴታዬ ነው !
6 _ በየቀኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ፈርሚልን ብለው እንዳላስጨነቁኝ አሁን ግን የሚያክመኝ ዶክተር እንኳን አንድም ቀን ፊርማዬን ጠይቆኝ አያውቅም !
7 _ ፀጉሬን የማስውብበት ውድ የተባሉ ሰባት አይነት አልማዞች እና ወርቆች ነበሩኝ አሁን ግን ይህንን ማድረግ አልችልም ምክንያቱም ፀጉር የለኝም !
8 _ በግል አውሮፕላኔ አለም ላይ የፈለኩበት ቦታ ብቻዬን መሄድ እችል ነበረ አሁን ግን ለመናፈስ ስፈልግ እንኳን የግድ የሁለት ሰዎች እርዳታ ያስፈልገኛል
9 _ በቀን በቀን ብፌ በሚባል አይነት የተመረጡ ምግቦችን እመገብ ነበር አሁን ግን በቀን ሁለት ፍሬ ታብሌት እና ትንሽ ጠብታ ጨው ነው ማታ የምወስደው ነው ምግቤ !
ይሄ ሁሉ ሀብት እና ድሎት ግን እኔን ከበሽታዬ ሊያድነኝ አልቻለም
እውነተኛ ህይወት ማለት ከፈጣሪ ጋር መኖር ፣ ለትዕዛዛቱም መገዛት ነው ።
269 views09:27