Get Mystery Box with random crypto!

አቡል ዓስ ወደ ረሱላችን ሰዐወ ሂዶ፦ «ትልቋን ልጅህን ዘይነብን እንድትድረኝ እጠይቅሀለሁ» አላቸው | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

አቡል ዓስ ወደ ረሱላችን ሰዐወ ሂዶ፦ «ትልቋን ልጅህን ዘይነብን እንድትድረኝ እጠይቅሀለሁ» አላቸው።
#አደብ

እሳቸውም፦ «ፍቃዷን ሳላረጋግጥ አልድርህም» አሉት።
#ህግ

ረሱላችን ሰዐወ ወደ ልጃቸው ዘይነብ ሂደው፦ «የአክስትሽ ልጅ እኔ ዘንድ መጥቶ አንችን ለምኖኛል፤ ባልሽ እንዲሆን ትፈቅጃለሽ ወይ?» ብለው ጠየቋት።አፍራ ፈገግ በማለት አጎነበሰች።
#ሀያእ

ጋብቻቸው ተፈፅሞ አስደናቂውን የትዳራቸውን ህይወት ሊጀምሩ ሁለት ልጆችን ወለዱ።
#ስኬት

አባቷ በነብይነት ሲበሰር ዕውነተኝነቱን ያመነችው ልጅት ዘይነብ ባሏ ለንግድ ጉዞ በሄደበት እስልምናን ተበብላ ጠበቀችው።
#ዕምነት

ልክ ከጉዞው ተመልሶ እቤቱ ሲገባ፦ «ትልቅ የምስራች ይዠልሀለሁ» ስትለው ምንም ሳይል ትቷት ከቤት ወጣ።
#አክባሪነት

ልጅት ዘይነብ ደንግጣ ባሏን እየተከተለች በመውጣት፦ «አባቴ በነብይነት ተልኳል፤ እኔም ሰልሚያለሁ» ስትለው
«ታድያ መጀመሪያውኑ አትነግሪኝም ነበር» ብሎ መለሰላት።

ልጅት ዘይነብም፦ «አባቴን ፍፁም አላስተባብልም፤ እሱም አይዋሽም። እኔ ብቻም ሳልሆን እናቴ እና እህቶቼም ጭምር ነን የሰለምነው» ብላ ንግግሯን ቀጠለች።
#አቋም

«የአጎቴ ልጅ ዐሊይ ሰልሟል፤ የአጎትህ ልጅ ዑስማንም እንደዝያው...ጓደኛህ አቡ በክርም ከኛው ነው» በማለት አብራራችለት።

እሱም፦ «እኔ እንደሆን ሚስቱን ለማስደሰት ሲል የጎሳውን ሀይማኖት ትቶ ሰለመ ተብሎ እንዲወራብኝ አልሻም። ይቅርታ አድርጊልኝ'ና አባትሽም ቢሆን ቀጣፊ እንዳልሆኑ አውቃለሁ» አላት።
#የሰከነ_ውይይት

እሷም፦ « እኔ ይቅር ካላልኩህ ማን ይልሀል?...ነገር ግን ዕውነት እስኪገለፅልህ ድረስ እረዳኻለሁ።» አለችው።
#መናበብ

(ለ20 አመታት ያህል ቃሏን ጠብቃ አብራው ቆየች።)

ዘይነብ በእስልምናዋ፤ ባሏ በክህደቱ ላይ ፀንተው ትዳራቸውን ባሟሟቁበት ግዜ ከመካ ወደ መዲና የሚደረገው የስደት ጉዞ ተደነገገ።

ልጅት ዘይነብም ወደ አባቷ ዘንድ ሂዳ፦ «አንቱ የአላህ መልዕክተኛ! እዚሁ ከባሌ ጋር እንድቀር ይፈቅዱልኛል» ስትል ጠየቀቻቸው።
#ፍቅር

ፈቀዱላትም።
#እዝነት

ሙስሊሞች ከመካ ወደ መዲና ተሰደው ልጅት ዘይነብ እዚሁ መካ ላይ ከባሏ ጋር ቀረች። ከግዜያት በኋላ ሙሀመድን ሰዐወ እና የመካ መሳፍንቶችን በአንድ የጦር ሜዳ ላይ የምታፋጥጠው የበድር ዘመቻ ቀጠሮዋ ቀረበ።

የልጅት ዘይነብ ባለቤት አቡል ዐስ'ም ከመካ መሳፍንቶች ተርታ ተሰልፎ የሚስቱን አባት ሊዋጋ ወሰነ።

ባለቤቷ አባቷን ሊዋጋ ሄደ፤ እሷ ቤቷ ቁጭ ብላ እያለቀሰች፦ «አላህ ሆይ! የድል ጮራህ ፈንጥቃ ልጆቼን የቲም እንዳታደርግብኝ ስፈራ፤ አባቴንም እንዳላጣው ሰጋሁ» ስትል ትውላለች።
#ምርጫ_አልባ

የበድር ጦርነት ዘመቻ ተጀመረ፤ በድር የድል ዙፋኗን ለሙሀመድ ሰዐወ ሸልማ፤ የመካ መሳፍንቶችን አስክሬን ከጦርነት አውድማው በመበተን የተቀሩትን መሳፍንት በሙሀመድ ሰዐወ ምርኮኛ አድርጋ የጦር ድንኳኗን አፈረሰች።

የጦርነት ዜናው የመካ መንደሮችን አጥለቀለቀ፤ ልጅት ዘይነብ ዜናውን ለመስማት ወጣ ብላ፦ «አባቴ እንዴት ሆነ...?» ስትል ትጠይቃለች። «ድልን ተጎናፅፏል» ስትባል ሱጁድ ትወርዳለች።

ከሱጁዷ ብድግ ብላ፦«ባለቤቴስ እንዴት ሆነ...?» ብላ ስትጠይቅ «የሙሀመድ ምርኮኛ ሁኗል» የሚል መርዶ ትሰማለች።

«እንግዲህ ባለቤቴን የምቤዥበት መስዋዕተ-ምትክ ወደ መዲና እልካለሁ» ብላ ትወስናለች።
#ብልሀት

ውድ ባለቤቷን ከተማረከበት ነፃ ለማስወጣት የምትቤዥለትን ውድ እቃዎች ስታሰላስል ከእናቷ ከዲጃ በኩል የተሰጣትን የአንገት ሀብል ብቁ ሆኖ ታያት'ና ወሰነችበት።

የባሏን መቤዥያ ይዞ ወደ መዲና የሄደው የባሏ ወንድም ልክ መዲና ሲገባ ሙሀመድን ሰዐወ ቁጭ ብለው መቤዥያዎችን እየተረከቡ ምርኮኞችን ሲለቁ ደረሰ።

እሱም ከዘይነብ የተረከበውን የባለቤቷን መቤዥያ ከሙሀመድ ሰዐወ ዘንድ ከተደረደሩት መቤዥያዎች መሀል ቁጭ አደረገ።

ሙሀመድም ሰዐወ መቤዥያዎችን ሲቆጥሩ በመሀል የድሮ የወጣትነት የፍቅር ዘመናቸውን የሚያስታውሳቸውን አንድ የአንገት ሀብል ተመለከቱ። ውድ ሟች ሚስታቸው ትዝ አለቻቸው።

በለሰለሰ ድምፅ፦ «ይህ የማን ነው...?» ሲሉ ጠየቁ።

«ይህ የአቡል ዓስ መቤዥያ(መስዋዕተ-ምትክ) ነው።» ተብሎ ተነገራቸው።
«ይህ የከዲጃ ሀብል ነበር» ብለው እቀረቀሩ።

አንገታቸው ዝቅ አለ፣ ፍቅርት ከዲጃ ትዝታዎቿ ከመቃብር በላይ ዳግም ህያው ሆነው የነቢዩን ጉንጮች በእንባ አራሳቸው።

ፊታቸውን ጠራርገው ከዙርያዎቻቸው የተሰበሰቡትን ሰሀቦች እየተመለከቱ፦ «ይህ ሰው በዝምድና ተቆራኝተነዋል፤ ፍቃዳችሁ ከሆነ እንፍታው...? ለዘይነብም ሀብሏን እንመልስላት...?» በማለት ጠየቁ።
#መተናነስ

«አዎ ይመለስ አንቱ ያላህ መልዕክተኛ» የሰሀባዎች ምላሽ ነበር።
#ስነስርአት

መልዕክተኛው ሰዐወ አቡል ዓስን አስጠሩት፦ «ይህን ሀብል ለዘይነብ መልሰህ ስጣት "በከዲጃ ሀብል አትጫወችብኝ" በላትም» ብለው ለቀቁት።

ዳግም ጠሩት፦ «አንተ አቡል ዓስ! አንዴ ለብቻህ ላናግርህ...?» ወደ ዳር ወሰዱት.....

«ይኸውልህ አቡል ዓስ! አላህ በካፊሮች እና በሙስሊሞች መካከል እንድለያይ አዞኛል። ስትመለስ ልጄን ትልክልኝ...?» በማለት ጠየቁት።

«እሺ እልካለሁ» አለ።
#ወንድነት

ጉዞውን ቀጠለ...፤ በመዲና እና በመካ መካከል ያሉትን በረሃዎች አቋርጦ የመካ ከተማ መዳራሻዎች ላይ ሲቀረብ ሚስቱ ዘይነብ ልትቀበለው ወጥታ አገኛት።

ገና ሲገናኙ፦«ልለይሽ ነው» ብሎ አስደነገጣት።
«ወዴት ነው የምትለየኝ...?» ድንጋጤ ፊቷ ላይ እየተነበበ።

«እኔ አይደለሁም የምለይሽ፤ አንቺ ነሽ የምትለዪኝ። ወደ አባትሽ እልክሻለሁ» አላት።
#ቃል_ኪዳን

ድንጋጤዋ እየጨመረ፦ «ለምን...?» አለችው።
«እንድንለያይ ተወስኗል'ና ወደ አባትሽ ትመለሻለሽ» አላት።

«እባክህ ስለም'ና አብረን እንሂድ» ስትል ተማፀነችው።
«በፍፁም» የሱ ምላሽ ነበር።

ሁለት ልጆቿን ይዛ የአባቷ መገኛ ወደሆነችው መዲና ተመመች። ልክ መዲና ገብታ ከአባቷ ጓዳ ከማረፏ ነበር የትዳር ጥያቄዎች ይጎርፉላት የጀመረው።

ምንም እንኳን ለ 6 ተከታታይ አመታት የትዳር ጥያቄዎች ከትላልቅ ሰሀባዎች ቢቀርቡላትም የባሏን የ"ይመለሳል" ተስፋ የሰነቀችው ዘይነብ በብቸኝነቷ ፀንታ ጠበቀች።

ከ 6 አመታት በኋላ ከመካ ወደ ሻም ከሚሄዱት የሲራራ ነጋዴዎች ጋር አንድ ላይ በመሆን አቡል ዓስ ጉዞ ጀመረ።

በጉዞ ላይ ሳሉ ከውስን ሰሀባዎች ጋር መዲና ላይ ፊት ለፊት ተገጣጠሙ። ንብረታቸው መካ ላይ ተወርሶ የግር ሳት የሆነባቸው ሰሀባዎችም ያገኙትን እድል ተጠቅመው የጫኑትን ግመሎች ማረኩባቸው።

ሰዓቱ ከሱብሒ በፊት ነው፣ የነቢዩ ሰዐወ ከተማ ነዋሪያን ቤታቸው ገብተው ከተማዋ ፀጥ...ብላለች። በዚህ መሀል አቡል ዓስ የዘይነብን ቤት አጠያይቆ በውድቅት ሌሊት በሯን አንኳካ።

ልክ በሯን ከፍታ እሱ መሆኑን ስታረጋግጥ፦ «ሰልመህ ነው የመጣኸው...?» በማለት ጠየቀችው።
#ተስፋ

«ኧረ አምልጬ ነው የመጣሁት...» ብሎ መለሰላት።
ጥያቄዋን ይቀበላት ዘንድ በስስት እያየችው፦ «እና ትሰልማለህ...?» አለችው።

«በፍፁም...» ብሎ ተስፋ በሚያስቆርጥ መልኩ መለሰላት።
በዲን ማስገደድ የለም'ና «እንግዲያውስ አብሽር እንኳን ደህና መጣህ የልጆቼ አባት፣ የአክስቴ ልጅ....» ብላ አስገባችው።
#ውለታ