Get Mystery Box with random crypto!

የስኬት መንገድ አሐዱ ሬድዮ 94.3

የቴሌግራም ቻናል አርማ yesketmengedme — የስኬት መንገድ አሐዱ ሬድዮ 94.3
የቴሌግራም ቻናል አርማ yesketmengedme — የስኬት መንገድ አሐዱ ሬድዮ 94.3
የሰርጥ አድራሻ: @yesketmengedme
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.23K
የሰርጥ መግለጫ

በስኬት መንገድ ላይ እያንዳንዷ እርምጃችን ወደ ግባችን ታቀርበናለች!!

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 13:50:22 https://www.facebook.com/ahaduradio/videos/792759125180225/
122 views10:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 00:03:52
190 views21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 00:03:44 የህይወት ፅናት
መፅናት ምን አንደሆነ ብዙም በይገለፅልኝም ሁልጊዜም በእየለቱ ትክክለኛውን ሙሉ ሰው ለመሆን ከራሴ ጋር እሟገታለሁ ።
#በእየለቱ እራሴን ማሸነፍ ፈልጋለሁ ግን አልችልም ይህን ስል ደግሞ ያን በማድረጌ እለት ከእለት እምሳሳትበትን አመለካከቴን እና ከሰውነት ሚዛን እሚያወረድኝን ችግሬን እቀንሳለሁ ።
#ምን ለማለት ፈልጌ መሰላቹሁ በመሞከር ውስጥ እራሴን በመገንባት ሂደት ላይ በየቀኑ አንዳንድ ችግሮችን እየቀረፍኩ ነው ማለት ነው ።
#እውነታው የሰው ልጅ ባንድ ጊዜ ሊለወጥ አይችልም ያንንም ግልፅ ሆኖ በጉዞዬ አይቼዋለሁ በጣም እሚገርመው ነገር ትልቁ ድክመቴ ለኔ ቀጠሮ ነበር ማድረግ እምፈልገውን ነገር በጊዜና በሳሀቱ ለማድረግ ተነሳሽነት ያንሰኛል ።
ለኔ ያ ነው ትልቁ ድክመት ነገር ግን በህይወት ውስጥ ከህልምህና ከራዕይህ የበለጠ አንተነትህ ላይ ትልቁ ማስተዋል ያለብህ ነገር ውሳኔህንና ተነሳሽነትህን በውስጥህ ይበልጥ ጎልቶ መውጣት እንዳለበት ልትገነዘብ ይገባል ።
# ሌላው ደግሞ የሰው ልጅ የተስፍና የነገ ውጤት ሲሆን ዛሬን ግን በአግባቡ ሳንጠቀም ነገ ላይ ሆነን ምንም ልንለውጠው እምንችለው ነገር እንደማይኖር ልትገነዘቡ ይገባል ።
# ወደነገህ ዛሬን በተግባር ውስጥ ሆነህ ስትደረስ ቀጣዮ ምዕራፍ ተዘጋጅቶ ይጠብቅሀል ።
#ስለዚህ በጉዞህ ውስጥ ትልቁን ድርሻ እሚወስደው አሁን ላይ ሆነህ እምትወስነው ውሳኔህ ነው ይበልጥ ነገን ወደፊትን እንድትናፍቅ እሚያደርግህ
#ተመልከት ወዳጄ መሬት ታርሶ እህል ከማብቀሉ በፊት ቅድመ ዝግጅት ገበሬው እሚያደርግ ይሆናል ,,,,,,,,,,,,,,,*
ምንም እንደሆነ ማብራራት አይጠበቅብኝም ለሁሉም ሰው ግልፅ ነው ብዬ ስለማስብ
#ከታች እምታየው ምስል የሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ ፎቶ ነው ብዙ ድሎችን ለሀገሩና ለአለም ማሳየት ችሏል ከዛ በፊት ግን አስቀድሞ በዙ የትንፍሽና የአቋም መለኪያ ከራሱም ሆነ ከፌደሬሽኑ ብቁ መሆንን ለማሳየትና እዚህ ደረጃ ለመድረስ በጣም ብዙ እሚባሉ ለሊቶችን እራሱ ላይ ሙከራ አድርጓል ።
#አየህ አንተም እራስህ ላይ ያለህ እምነት ሙሉ መሆኑን አንተና አንተ ብቻ ልትረዳው ይገባል ።
#ያን ደግሞ ከውስጥህ ላይ ካገኘህው አንተ ተለውጠሀል ማለት ነው ብዙ ከባድ እምትላቸውን የህይወት ውጣ ውረዶች እንደምታሸንፍቸው እርግጥ ነው።
አመሰግናለሁ
ይቀጥላል ,,,,,,,,,,,,,
ፀሀፊ አብዱ ገለቱ (አዲስ ገፅ )
መልካም ዛሬ
197 views21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:24:16 አእምሮ ማግኔት ነው!
ስለ በረከቶች ካሰብክ በረከትን ይስባል፤
ስለ ችግር ካሰብክ ችግሮችን ይስባል።
ሁልጊዜ ጥሩ ሀሳቦችን አዳብር
አዎንታዊ እና ብሩህ አመለካከት ይኑርህ!
379 views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 21:22:59 1. ምስጋና

አመስጋኝ የሆኑ ሰዎች ምስጋና ቢስ ከሆኑ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ “ተመስገን” በሉ ሲባሉ “ምን ምስጋና የሚገባው ነገር አለና” የሚሉ አሉ፡፡ ግን ብዙ “ተመስገን የሚያስብሉ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ቆም ብለን ብናስብ በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡

2. ቀና ማሰብ

ቀና አሳባዎች ቀና ከማያስቡ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ ደስተኛ መሆን ከፈለግን “ይሆናል፤ ይቻላል፤ ይሳካል፤ ለበጎ ነው ወዘተ” ማለትን እንለማመድ፡፡ የእውነት እንደዚያ ካደረግን ለውጡን እናየዋለን፡፡

3. ከልክ በላይ ማሰብ እና ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ማቆም

“ከልኩ አያልፍ” ትል ነበር አያቴ፤ ሃሳብ ከልክ በላይ እንደገባት ወይንም አጠገቧ ያለ ሰው ከልክ በላይ እንደተጨነቀ ሲሰማት፡፡ ሺህ ዓመት አይኖርም፡፡ ሁሉም የሚያጭደው የዘራውን ነው፡፡ ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር የተረጋገጠ ራስን የማሰቃያ መንገድ ነው፡፡ ሰው እንደቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ ሊኖር አይገባም፡፡

4. ደግነት

ደግ መሆን ይቅርና ሰዎች ደግ ስራ ሲሰሩ መመልከት እንኳን ደስተኛ እንደሚያደርግ ሳይኮሎጂስቶች አረጋግጠዋል፡፡ ደስታ ከህይወታችን እንደ ራቀ ሲሰማን አንዱ መልሶ ማቅረቢያ ስልት መልካም ስራ መስራት ነው፡፡ በርካታ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች አሉ፡፡ ወደዚያ ጎራ ብሎ አንድ መልካም ነገር አድርጎ መመለስ ደስታን አጭዶ መመለስ ነው፡፡

5. መልካም ማኅበራዊ ግንኙነት

“ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው” ብለው አበው ጨርሰውታል፡፡ የልባችንን የምናዋየው የልብ ወዳጅ ዘመድ አንዱ የደስታ ምንጭ ነው፡፡ የሚያሳስበንን ነገር ከውስጣችን አውጥተን መናገር ጭንቀትን ይቀንሳል፡፡

6. ይቅርታ

“ቂም መቋጠር ማለት መርዝ ጠጥቶ ሌላኛው ሰው እንደሚሞት ማሰብ ነው” ይባላል፡፡ ይቅርታ የምናደርገው ከሁሉ በፊት ለገዛ ራሳችን ደህንነት ነው፡፡ ማህተመ ጋንዲ “ደካማ ሰው ይቅር ብያለሁ ማለት አይችልም፡፡ ይቅርታ የጠንካራ ሰው መገለጫ ነው” ይላሉ፡፡ ይቅር ብያለሁ ማለት በመንፈስ የበላይ መሆን ነው፤ መብለጥ ነው፤ ገናና የሞራል ከፍታ ላይ መውጣት ነው፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ደስታን ወደ ህይወታችን የምንጋብዝበት መጥሪያ ካርድ ነው፡፡

7. የምንወደውን ነገር ማድረግ

8. ያቀድነውን ዕቅድ እውን ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ

ያሰቡትን ማሳካት በራሱ ትልቅ ደስታን ይፈጥራል፡፡ ሁልጊዜ ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ ከሆንን ግን ደስታ ውስጣችን አይለመልምም፡፡ የጀመርነውን ነገር ዳር የማድረስ ልምዱ ይኑረን፡፡ የምንኖረው የአማራጮች ዓለም ውስጥ ነው፡፡ ብዙ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮች ተችለው የምንመለከትበ ዓለም፡፡

10. ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት

ከሲኦል ቢያድነንም ባያድነንም ወደ ቤተ-እምነት መቅረባችን ደስታን ይገዛልናል እንጂ ደስታችንን አይነጥቀንም፡፡ ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ደስተኛ እንደሚያደርጉ በጥናት ጭምር ተረጋግጧል፡፡

11. ሰውነታችንን መንከባከብ

አእምሮአችን ከአካላችን ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ነው፡፡ ጤናማ የሆነ ብቻ ሳይሆን የተዋበ ሰውነት እንዲኖረን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ፣ ስፖርት መስራትና በተለያየ መንገድ ጥረት ማረግ አለብን፡፡
359 views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 12:06:05 ሰላም ድንቆች
ቀናችንን በምስጋና በጥሩ አስተሳሰብ በአዎንታዊ ቃላት እንጀምር።
*እኔ ድንቅ ነኝ
*እኔ ፍቅር ነኝ
*እኔ ሰላም ነኝ
*እኔ ጠንካራ ነኝ
*እኔ ተወዳጅ ነኝ
*እኔ ጀግና ነኝ
*እኔ ቅን ነኝ


መልካም የስኬት ቀን
322 views09:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:19:32 የልዩነቴ ዋጋ!

ልዩ ሰው መሆኔ ሁለት አይነት ዋጋን ያስከፍለኛል፡፡ ከሁለቱ አንዱን የመምረጥ መብቱ ግን አለኝ፡፡

አንደኛው ዋጋ፣ ፈጣሪ የሰጠኝን እኔነቴንና ራሴን በመሆኔና እንዲሁም የማምንበትን እውነት በመኖሬ ምክንያት ያንን የማይቀበሉ ሰዎችን ሲለዩኝና እንደእነሱ ስላልሆንኩኝ ሲቃወሙኝ የምከፍው ዋጋ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ሰዎችን የማጣት ዋጋ ነው፡፡

ሌላኛው ደግሞ ልዩነቴን ላልተቀበሉ ሰዎቸ ስል ራሴን ትቼ እንደሌላው ሰው ለመኖር በመሞከሬ የምከፍለው ዋጋ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ራስን የማጣት ዋጋ ነው፡፡

ለሰዎች ብሎ ማንነትን ትቶ መሄድ እጅግ የከፋ ዋጋ ያስከፍላ፡፡ ራስን ሆኖ በመኖር ግን ምንም እንኳን ሰዎች ባጣቸውና ሰዎች ቢቃወሙኝ ራሴንና ዓላማዬን አገኛለሁ፡፡ ምንም እኳን ከእነሱ ጋር ባልስማማም፣ ከራሴ ጋር ግን እስማማለሁ፡፡

የብዙ ሰዎች ማሕበራዊ ችግርና ቀውስ ያለው እዚህ ላይ ነው፤ ሌላውን ሰው ላለማጣት ሲሉ ራሳቸውን ማጣታቸው!

እንግዲህ ምረጡ! ለሰው ብላችሁ ማንነታችሁን ትታችሁ በመሄድ ሰዎችን አግኝታችሁ በሂደቱ ራሳችሁን ማጣት ይሻላችኋል ወይስ ማንነታችሁን ኖራችሁ በሂደቱ አንዳንድ ሰዎችን አጥታችሁ ራሳችሁን ብታገኙ?

ለመደምደም ያህል፡- ራስንና ያመኑበትን መኖር አላስፈላጊ ሰዎችን ከሕይወታችሁ የማጥራት ከፍተኛ አቅም አለው!
391 views17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 14:47:10 ዐባይ በግእዝ ድርሳናት
አዘጋጅ፦ መርሻ አለኸኝ
አሳታሚ፦ አ.አ ዮንቨርሲቲ ፕሬስ

ዐባይ በግእዝ ድርሳናት የተሠኝው ይህ መጽሐፍ በሥድስት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን ዐባይ በጥንታዊ መዛግብት በገድሎች በመጻሕፍት/ በድጓ /በመዝሙር /በቅኔ /በሊቃውንት ስለ ዐባይ የተነገሩትን አሰባስቦ የያዘ ጥናታዊ ጽሑፍ ነው። በገጽ 335 የሚጠናቀቅ እና የመሽጫ ዋጋው 208 ብር ነው ።

መልክዐ ዐባይ
ሰላም ለፅንሰትከ ለኢትዮጵያ እምከርሣ
ወለልደትከ ሰላም በሐቅለ ሰከላ አሶሳ።
ባኮስ ግዮን ዘትጥሕር ከመ አንበሳ
አመ ኮነ ዜና ስምከ ለኢትዮጵያ ሞገሳ
በማየ ሕይወት ተጠምቀ ዘበልየ ሕዋሳ።

ትርጕም
ስለ ኢትዮጵያ ማሕፀን ለመፀነስህ ሰላምታ ይገባል፡፡ በአሶሳና ሰከላ በረሐ ለመወለድህም ሰላምታ ይገባል።
እንደ አንበሳ የምታገሣ ባኮስ ዐባይ ሆይ! በስምህ ለኢትዮጵያ ክብሯ በኾነ ጊዜ፣ የረጀው ሰውነቷ በሕይወት ውኃ ተጠመቀ።

Eneho books - እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ።
4ኪሎ ምኒልክ ት/ቤት ፊት ለፊት ከሮሚና ዝቅ ብሎ።

ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል።

https://t.me/enhobooks
https://t.me/enhobooks
https://t.me/enhobooks
318 views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 08:47:44 ሰላም ዉድ የስኬት መንገድ ፕሮግራም ቤተሰቦቻችን ቀናችንን በማመስገን ጀምረን ልዩ እና ያማረ ቀን እናድርገዉ።
እኔ ሠላም ነኝ
እኔ ጤና ነኝ
እኔ ፍቅር ነኝ
እኔ ባለፀጋ ነኝ
እኔ አላማ አለኝ እያልን ያሉንን በረከቶች እያሰብን በማመስገን ቀናችንን ስኬታማ ቀን እናድርገዉ። ይህን ቻናል በቅንነት ያጋሩ https://t.me/yesketmengedme
315 views05:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 16:44:00 https://www.facebook.com/100641816074055/posts/112848231520080/?mibextid=RuouPlR5776KdJDD
324 views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ