Get Mystery Box with random crypto!

የልዩነቴ ዋጋ! ልዩ ሰው መሆኔ ሁለት አይነት ዋጋን ያስከፍለኛል፡፡ ከሁለቱ አንዱን የመምረጥ መብ | የስኬት መንገድ አሐዱ ሬድዮ 94.3

የልዩነቴ ዋጋ!

ልዩ ሰው መሆኔ ሁለት አይነት ዋጋን ያስከፍለኛል፡፡ ከሁለቱ አንዱን የመምረጥ መብቱ ግን አለኝ፡፡

አንደኛው ዋጋ፣ ፈጣሪ የሰጠኝን እኔነቴንና ራሴን በመሆኔና እንዲሁም የማምንበትን እውነት በመኖሬ ምክንያት ያንን የማይቀበሉ ሰዎችን ሲለዩኝና እንደእነሱ ስላልሆንኩኝ ሲቃወሙኝ የምከፍው ዋጋ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ሰዎችን የማጣት ዋጋ ነው፡፡

ሌላኛው ደግሞ ልዩነቴን ላልተቀበሉ ሰዎቸ ስል ራሴን ትቼ እንደሌላው ሰው ለመኖር በመሞከሬ የምከፍለው ዋጋ ነው፡፡ ይህ ዋጋ ራስን የማጣት ዋጋ ነው፡፡

ለሰዎች ብሎ ማንነትን ትቶ መሄድ እጅግ የከፋ ዋጋ ያስከፍላ፡፡ ራስን ሆኖ በመኖር ግን ምንም እንኳን ሰዎች ባጣቸውና ሰዎች ቢቃወሙኝ ራሴንና ዓላማዬን አገኛለሁ፡፡ ምንም እኳን ከእነሱ ጋር ባልስማማም፣ ከራሴ ጋር ግን እስማማለሁ፡፡

የብዙ ሰዎች ማሕበራዊ ችግርና ቀውስ ያለው እዚህ ላይ ነው፤ ሌላውን ሰው ላለማጣት ሲሉ ራሳቸውን ማጣታቸው!

እንግዲህ ምረጡ! ለሰው ብላችሁ ማንነታችሁን ትታችሁ በመሄድ ሰዎችን አግኝታችሁ በሂደቱ ራሳችሁን ማጣት ይሻላችኋል ወይስ ማንነታችሁን ኖራችሁ በሂደቱ አንዳንድ ሰዎችን አጥታችሁ ራሳችሁን ብታገኙ?

ለመደምደም ያህል፡- ራስንና ያመኑበትን መኖር አላስፈላጊ ሰዎችን ከሕይወታችሁ የማጥራት ከፍተኛ አቅም አለው!