Get Mystery Box with random crypto!

ዐባይ በግእዝ ድርሳናት አዘጋጅ፦ መርሻ አለኸኝ አሳታሚ፦ አ.አ ዮንቨርሲቲ ፕሬስ ዐባይ በግእዝ | የስኬት መንገድ አሐዱ ሬድዮ 94.3

ዐባይ በግእዝ ድርሳናት
አዘጋጅ፦ መርሻ አለኸኝ
አሳታሚ፦ አ.አ ዮንቨርሲቲ ፕሬስ

ዐባይ በግእዝ ድርሳናት የተሠኝው ይህ መጽሐፍ በሥድስት ምዕራፎች የተከፈለ ሲሆን ዐባይ በጥንታዊ መዛግብት በገድሎች በመጻሕፍት/ በድጓ /በመዝሙር /በቅኔ /በሊቃውንት ስለ ዐባይ የተነገሩትን አሰባስቦ የያዘ ጥናታዊ ጽሑፍ ነው። በገጽ 335 የሚጠናቀቅ እና የመሽጫ ዋጋው 208 ብር ነው ።

መልክዐ ዐባይ
ሰላም ለፅንሰትከ ለኢትዮጵያ እምከርሣ
ወለልደትከ ሰላም በሐቅለ ሰከላ አሶሳ።
ባኮስ ግዮን ዘትጥሕር ከመ አንበሳ
አመ ኮነ ዜና ስምከ ለኢትዮጵያ ሞገሳ
በማየ ሕይወት ተጠምቀ ዘበልየ ሕዋሳ።

ትርጕም
ስለ ኢትዮጵያ ማሕፀን ለመፀነስህ ሰላምታ ይገባል፡፡ በአሶሳና ሰከላ በረሐ ለመወለድህም ሰላምታ ይገባል።
እንደ አንበሳ የምታገሣ ባኮስ ዐባይ ሆይ! በስምህ ለኢትዮጵያ ክብሯ በኾነ ጊዜ፣ የረጀው ሰውነቷ በሕይወት ውኃ ተጠመቀ።

Eneho books - እነሆ መጻሕፍት ዘወትር በልዩ ቅናሽ።
4ኪሎ ምኒልክ ት/ቤት ፊት ለፊት ከሮሚና ዝቅ ብሎ።

ይህ የእነሆ መጻሕፍት የቴሌ ግራም ቻናላችሁ ነው የተለያዩ አዳዲስ መጻሕፍት ይተዋወቁበታል። የእነሆ መጻሕፍት ግብዣችን ጥቆማ ይቀርብበታል።

https://t.me/enhobooks
https://t.me/enhobooks
https://t.me/enhobooks