Get Mystery Box with random crypto!

የህይወት ፅናት መፅናት ምን አንደሆነ ብዙም በይገለፅልኝም ሁልጊዜም በእየለቱ ትክክለኛውን ሙሉ | የስኬት መንገድ አሐዱ ሬድዮ 94.3

የህይወት ፅናት
መፅናት ምን አንደሆነ ብዙም በይገለፅልኝም ሁልጊዜም በእየለቱ ትክክለኛውን ሙሉ ሰው ለመሆን ከራሴ ጋር እሟገታለሁ ።
#በእየለቱ እራሴን ማሸነፍ ፈልጋለሁ ግን አልችልም ይህን ስል ደግሞ ያን በማድረጌ እለት ከእለት እምሳሳትበትን አመለካከቴን እና ከሰውነት ሚዛን እሚያወረድኝን ችግሬን እቀንሳለሁ ።
#ምን ለማለት ፈልጌ መሰላቹሁ በመሞከር ውስጥ እራሴን በመገንባት ሂደት ላይ በየቀኑ አንዳንድ ችግሮችን እየቀረፍኩ ነው ማለት ነው ።
#እውነታው የሰው ልጅ ባንድ ጊዜ ሊለወጥ አይችልም ያንንም ግልፅ ሆኖ በጉዞዬ አይቼዋለሁ በጣም እሚገርመው ነገር ትልቁ ድክመቴ ለኔ ቀጠሮ ነበር ማድረግ እምፈልገውን ነገር በጊዜና በሳሀቱ ለማድረግ ተነሳሽነት ያንሰኛል ።
ለኔ ያ ነው ትልቁ ድክመት ነገር ግን በህይወት ውስጥ ከህልምህና ከራዕይህ የበለጠ አንተነትህ ላይ ትልቁ ማስተዋል ያለብህ ነገር ውሳኔህንና ተነሳሽነትህን በውስጥህ ይበልጥ ጎልቶ መውጣት እንዳለበት ልትገነዘብ ይገባል ።
# ሌላው ደግሞ የሰው ልጅ የተስፍና የነገ ውጤት ሲሆን ዛሬን ግን በአግባቡ ሳንጠቀም ነገ ላይ ሆነን ምንም ልንለውጠው እምንችለው ነገር እንደማይኖር ልትገነዘቡ ይገባል ።
# ወደነገህ ዛሬን በተግባር ውስጥ ሆነህ ስትደረስ ቀጣዮ ምዕራፍ ተዘጋጅቶ ይጠብቅሀል ።
#ስለዚህ በጉዞህ ውስጥ ትልቁን ድርሻ እሚወስደው አሁን ላይ ሆነህ እምትወስነው ውሳኔህ ነው ይበልጥ ነገን ወደፊትን እንድትናፍቅ እሚያደርግህ
#ተመልከት ወዳጄ መሬት ታርሶ እህል ከማብቀሉ በፊት ቅድመ ዝግጅት ገበሬው እሚያደርግ ይሆናል ,,,,,,,,,,,,,,,*
ምንም እንደሆነ ማብራራት አይጠበቅብኝም ለሁሉም ሰው ግልፅ ነው ብዬ ስለማስብ
#ከታች እምታየው ምስል የሻለቃ ሀይሌ ገብረስላሴ ፎቶ ነው ብዙ ድሎችን ለሀገሩና ለአለም ማሳየት ችሏል ከዛ በፊት ግን አስቀድሞ በዙ የትንፍሽና የአቋም መለኪያ ከራሱም ሆነ ከፌደሬሽኑ ብቁ መሆንን ለማሳየትና እዚህ ደረጃ ለመድረስ በጣም ብዙ እሚባሉ ለሊቶችን እራሱ ላይ ሙከራ አድርጓል ።
#አየህ አንተም እራስህ ላይ ያለህ እምነት ሙሉ መሆኑን አንተና አንተ ብቻ ልትረዳው ይገባል ።
#ያን ደግሞ ከውስጥህ ላይ ካገኘህው አንተ ተለውጠሀል ማለት ነው ብዙ ከባድ እምትላቸውን የህይወት ውጣ ውረዶች እንደምታሸንፍቸው እርግጥ ነው።
አመሰግናለሁ
ይቀጥላል ,,,,,,,,,,,,,
ፀሀፊ አብዱ ገለቱ (አዲስ ገፅ )
መልካም ዛሬ