Get Mystery Box with random crypto!

1. ምስጋና አመስጋኝ የሆኑ ሰዎች ምስጋና ቢስ ከሆኑ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ “ተመስገ | የስኬት መንገድ አሐዱ ሬድዮ 94.3

1. ምስጋና

አመስጋኝ የሆኑ ሰዎች ምስጋና ቢስ ከሆኑ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ “ተመስገን” በሉ ሲባሉ “ምን ምስጋና የሚገባው ነገር አለና” የሚሉ አሉ፡፡ ግን ብዙ “ተመስገን የሚያስብሉ ብዙ ነገሮች እንዳሉ ቆም ብለን ብናስብ በዙሪያችን ሞልተዋል፡፡

2. ቀና ማሰብ

ቀና አሳባዎች ቀና ከማያስቡ ሰዎች የበለጠ ደስተኛ ናቸው፡፡ ደስተኛ መሆን ከፈለግን “ይሆናል፤ ይቻላል፤ ይሳካል፤ ለበጎ ነው ወዘተ” ማለትን እንለማመድ፡፡ የእውነት እንደዚያ ካደረግን ለውጡን እናየዋለን፡፡

3. ከልክ በላይ ማሰብ እና ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር ማቆም

“ከልኩ አያልፍ” ትል ነበር አያቴ፤ ሃሳብ ከልክ በላይ እንደገባት ወይንም አጠገቧ ያለ ሰው ከልክ በላይ እንደተጨነቀ ሲሰማት፡፡ ሺህ ዓመት አይኖርም፡፡ ሁሉም የሚያጭደው የዘራውን ነው፡፡ ራስን ከሌሎች ጋር ማወዳደር የተረጋገጠ ራስን የማሰቃያ መንገድ ነው፡፡ ሰው እንደቤቱ እንጂ እንደጎረቤቱ ሊኖር አይገባም፡፡

4. ደግነት

ደግ መሆን ይቅርና ሰዎች ደግ ስራ ሲሰሩ መመልከት እንኳን ደስተኛ እንደሚያደርግ ሳይኮሎጂስቶች አረጋግጠዋል፡፡ ደስታ ከህይወታችን እንደ ራቀ ሲሰማን አንዱ መልሶ ማቅረቢያ ስልት መልካም ስራ መስራት ነው፡፡ በርካታ የግብረ ሰናይ ድርጅቶች አሉ፡፡ ወደዚያ ጎራ ብሎ አንድ መልካም ነገር አድርጎ መመለስ ደስታን አጭዶ መመለስ ነው፡፡

5. መልካም ማኅበራዊ ግንኙነት

“ለሰው መድኃኒቱ ሰው ነው” ብለው አበው ጨርሰውታል፡፡ የልባችንን የምናዋየው የልብ ወዳጅ ዘመድ አንዱ የደስታ ምንጭ ነው፡፡ የሚያሳስበንን ነገር ከውስጣችን አውጥተን መናገር ጭንቀትን ይቀንሳል፡፡

6. ይቅርታ

“ቂም መቋጠር ማለት መርዝ ጠጥቶ ሌላኛው ሰው እንደሚሞት ማሰብ ነው” ይባላል፡፡ ይቅርታ የምናደርገው ከሁሉ በፊት ለገዛ ራሳችን ደህንነት ነው፡፡ ማህተመ ጋንዲ “ደካማ ሰው ይቅር ብያለሁ ማለት አይችልም፡፡ ይቅርታ የጠንካራ ሰው መገለጫ ነው” ይላሉ፡፡ ይቅር ብያለሁ ማለት በመንፈስ የበላይ መሆን ነው፤ መብለጥ ነው፤ ገናና የሞራል ከፍታ ላይ መውጣት ነው፤ ይህ ብቻ ሳይሆን ደስታን ወደ ህይወታችን የምንጋብዝበት መጥሪያ ካርድ ነው፡፡

7. የምንወደውን ነገር ማድረግ

8. ያቀድነውን ዕቅድ እውን ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ

ያሰቡትን ማሳካት በራሱ ትልቅ ደስታን ይፈጥራል፡፡ ሁልጊዜ ሩቅ አሳቢ ቅርብ አዳሪ ከሆንን ግን ደስታ ውስጣችን አይለመልምም፡፡ የጀመርነውን ነገር ዳር የማድረስ ልምዱ ይኑረን፡፡ የምንኖረው የአማራጮች ዓለም ውስጥ ነው፡፡ ብዙ የማይቻሉ የሚመስሉ ነገሮች ተችለው የምንመለከትበ ዓለም፡፡

10. ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት

ከሲኦል ቢያድነንም ባያድነንም ወደ ቤተ-እምነት መቅረባችን ደስታን ይገዛልናል እንጂ ደስታችንን አይነጥቀንም፡፡ ሃይማኖት እና መንፈሳዊነት ደስተኛ እንደሚያደርጉ በጥናት ጭምር ተረጋግጧል፡፡

11. ሰውነታችንን መንከባከብ

አእምሮአችን ከአካላችን ጋር በእጅጉ የተሳሰረ ነው፡፡ ጤናማ የሆነ ብቻ ሳይሆን የተዋበ ሰውነት እንዲኖረን የተመጣጠነ ምግብ በመመገብ፣ ስፖርት መስራትና በተለያየ መንገድ ጥረት ማረግ አለብን፡፡