Get Mystery Box with random crypto!

ሁስነል ኹሉቅ

የቴሌግራም ቻናል አርማ yeresulnfkrmeglecha — ሁስነል ኹሉቅ
የቴሌግራም ቻናል አርማ yeresulnfkrmeglecha — ሁስነል ኹሉቅ
የሰርጥ አድራሻ: @yeresulnfkrmeglecha
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 467
የሰርጥ መግለጫ

የጥሩ ጸባይ ፍቅር መግለጫ

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-07 22:48:02 አረፋህ ሊመን አረፈህ!!

ነገ ቤት የማፅጃ ወይ መጋረጃ የማውረጃ ቀን አይደለም። የኢድ ሸመታም ሆነ የመዝናኛ እንዲሁ!

ነገ አላህ የሰማይ ባለሟሎች ላይ በአረፋ ሰዎች የሚኩራራበት፤ የሰው ልጆች ከእሳት በገፍ ነፃ የሚባሉበት ከሁሉ በላይ ዱአዎች በሙሉ ተቀባይነት የሚያገኙበት እለት ነው።

ለይለቱል ቀድር ባትታወቅ የውሙ አረፋ ትታወቃለች። በለይለቱል ቀድር መላእክት ቢወርዱ በአረፋ አላህ (እሱን በሚመጥን አወራረድ) የሚወርድበት ነው!

ነገ አላህ በጊዜ ፀጋ ላጣቀማችሁ አንድ to do list ላካፍላችሁ

ጠዋት

ከፈጅር በፊት ከለይሉ ጥቂቱን መስገድ፣ ስሁር መመገብ እና ኢስቲግፋር ማብዛት!

ከሰላት በኋላ ቀጥታ ተክቢራ መጀመር ከዛም ፀሀይ እስክትወጣ ቁርአን፣ተህሊል፣ተህሚድ በአጠቃላይ በዚክር ማሳለፍ(አዝካረ ሰባህ ሳይረሳ)

ፀሀይ ስትወጣ የፀሃይ መውጣትን ሰላት እዛው ከመስገጃችን ሳንነሳ በመከወን ከረሱሉ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሀጅ የማድረግን ምንዳ እንዲጎናጸፍ

ለቀን ኢባዳ ያግዘናል ብለን ካሰብን መጠነኛ እኝቅልፍ እንተኛ። ስንነሳ በትንሹ 4 ረክኣ ሰላተ ዱሃ እንስገድ!

ከሰአት

ከዝሁር ሰላት በኋላ ቁርዐናችንን እንቀራለን። የአረፋ ኹጥባ(ከመስጂደ ነሚራህ የሚተላለፈውን) መልእክት በጥብቅ መከታተል

ልባችንን ሊያረጥብ የሚችል መፅሐፍ ወይም ቪድዮ እየተመለከትን እራሳችንን እናርጥብ!

ከአስር በጥሎ እንዲሁ በቁርአን እና በዚክር መግሪብ 1 ሰአት አቅራቢያ እስኪቀረው ማሰለፍ!

የእለቱ ወሳኝ ሰአት ይህ ነው።

የተሰበረ የሚጠገንበት፤ የታመመ የሚፈወስበት፤ ተስፋ የቆረጠ ተስፋው ነፍስ ሚዘራበት ድንቅ ሰአት!

ዱኣ!!! ዱኣ ብቻ!

በዚህ ቀን ከእሳት ነፃ አለመባል ኪሳራ ነው። ምኞት ኖሮን ምኞታችንን ሳናሳካ መቅረት ቂልነት ነው!

ነገ አላህ አልመረጥንም እና እየተመለከታቸው ከሚኮፈስባቸው ጌታቸውን ለማላቅ በነጭ ተውበው ከአረህማን ድግስ ከሚታደሙት አልሆንም!

"አረፋ ተራራ ላይ መቆም ያልቻለ
አላህ ያሳወቀው ድንበር ላይ ይቁም

ሙዝደሊፋ ላይ ማደር ያልቻለ
በአላህ ትእዛዝ ላይ ይደር...ያቀርበዋልና!

ሚና ላይ እርዱን መከወን ያልቻለ
ምኞቱን ይረድ! ከፍ ይላልና።

ወደ ቤቱ በርቀት ምክንያት መድረስ ያልቻለ
ከደም ስሩ ቅርብ ወደ ሆነው የቤቱ ጌታ ይከጅል!" ኢብኑ ረጀብ






  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄
1.3K viewsSulle man ثايهن, 19:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 19:49:08 #ኸሚስ_ከአረፋ ለይል ጋ ገጠመልን

የዳና ሀሪማ የመጀመሪያ-ዙር ተማሪዎች

አንድ ዕለት ሼህ አህመደ-ዳንይ ተመስጠው፣ ፊታቸውን ለፈጣሪ አስጥተው፣ ቁጭ ብለው ነበር። ከተከታዮቻቸው ጥቂቶቹ፣ ወደ እርሳቸው ገቡ።
ጥርስ ሙሉ ፊታቸውን እየመገቡ -«ሼሆቹ! አረዳው(ባላገሩ) አርባ ጊደሮችን በስጦታ አስረክቧል። "ዱዓ አድርጉልን"ም ብሏል።» አሉ።

ሼህ አህመድ ደርባባነታቸውን አከሉ። አልተከፉም፣ አልተደሰቱም - «እንዲያ አደረጉ?» ብለው የሰባ ገረሜታ አቀበሉ። ወዲያው ባለጊደሮቹ እንዲጠሩ አስደረጉ። ሰዎቹ ተሰበሰቡ።

«አርባዎቹን ጊደሮች፡ በአርባ ልጆች ቀይሩልኝ?» አሏቸው። «ላስተምራቸው። ለእርሻ፣ ከብት ለመጠበቅ፣ ወንዝ-ወርዶ ውሃ ለመቅዳት ስትፈልጉ ወደ እናንተ ይመጣሉ። ከዚያ በተረፈ ጊዜያቸው ከእኔው ያሳልፋሉ። በዚህ ተስማሙኝ?» አጥብቀው ጠየቋቸው፣ ሼህ አህመድ።ለልባዊ ምኞታቸው እውኔታ ተማፀኗቸው።

ባላገሮቹ ጊደሮቹን ወሰዱ። የተጠየቁትን በ‹መርሃባ› ፈቀዱ። ልጅ ልጆቻቸውን እያመጡ አስረከቡ።

የሼህ አህመድ፣ በዳና የመጀመሪያ-ዙር ተማሪዎቻቸው ሆኑ - እኒያ አርባ ልጆች። የተማሩት የቁርአን ነቢብ ብቻ ነበር። ከእርሳቸው ንጥር ግብርና ምግባር ግን፣ አንፀባራቂውን እስልምና ይዋሀዱት ጀመር። እንዳለ ቀዱት። ሳያስቀሩ ወሰዱት።

ሼህ አህመድ ሆን ብለው ነበር ወጥመዱን የጣሉት። አንዱን ትውልድ በጥበብ አጠመዱት። ልጆች ወደ ወላጆቻቸው ሲሄዱ ነቀፌታ ተደፋፈሩ። መረን የለቀቀ ተግባራቸውን - «ይህንንማ ሼሆቹ ወንጀል ነው ብለዋል፡ እርሱንማ ክልክል መሆኑን አስተምረዋል» እያሉ ተቃወሙ። ወላጆችም «እርሳቸው ካሉማ» በማለት፣ ወደ ሼህ አህመድ ማምራት ጀመሩ። ጥያቄ እየያዙ፣ በአጥጋቢ መልስ እየወዙ እምነታቸውን እንደገና ተማሩ። በሼህ አህመድ ጥበብ!

ዳናዎች ቅፅ ፩ ፡ ኸድር ታጁ
ገፅ 93



 


                             
                                
                                      
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ




  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄
52 viewsSulle man ثايهن, 16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 21:41:27 ሰሓባዎች ሶርያ አካባቢ የጦር ዘመቻ ሂደው በነበረበት ወቅት በግዜው የነበረው
ከሊፋ ዑመር ረዐ ሊጎበኛቸው ፈልጎ ከመዲና ወደ ሻም ተጓዘ።
እንደ አጋጣሚ ሆና የምሳ ሰአት ላይ ከሊፋው ከሰራዊቱ መገኛ ደርሶ አቀባበል
ተደረገለት። የጦሩ መሪ የነበረውም አባ ኡበይዳ ረዐ ከሊፋውን ለምሳ ይዞት ወደ
ድንኳኑ ወሰደው።
ከሊፋው እና የጦሩ መሪ ከድንኳኑ ስር ሁነው ምሳ አቅራቢዎቹን በመጠባበቅ ላይ
ሳሉ አቅራቢዎቹ ወደ ከሊፋው ጠጋ ብለው፦‹‹የሰራዊት ምሳ እናቅርብልህ ወይስ
የጦር አዛዡን›› ሲሉ ጠየቁት።
ከሊፋው ግራ በመጋባት፦‹‹እስቲ ሁለቱንም አምጡልኝ›› አላቸው።
ሁለቱንም አመጡለትና በመጀመርያ የሰራዊቱን ምግብ ከፊቱ አቀረቡለት።
ከሊፋው ከፊቱ የቀረበለትን የሰራዊቱን ምግብ ሲመለከት ስጋ፣ መረቅ፣ እና
አትክልት በስጋ ተፈርፍሮ ፍፁም ቅንጡ የሆነ ምግብ ተመለከተ።
ግራ እየተጋባ፦‹‹እስቲ የጦር አዛዡን ምግብ አምጡልኝ›› ብሎ ጠየቀ።
ከኋላ ያስቀመጡትን የጦር አዛዡን ምግብ አቀረቡለት። ከፍቶ ሲመለከትም
የደረቀ ዳቦ እና ትንሽዬ ወተት ሁኖ አገኘው። ከሊፋው ዑመር ረዐ ከፊቱ
የቀረበውን የጦር አዛዡን እና የሰራዊቱን ምግቦች እየተመለከተ ተንሰቀሰቀ።
ወደ ጦር አዛዡ እየተመለከተ እንዲህም አለው፦‹‹ነቢ ሰዐወ የዚህ ኡማ ባለ
አደራ ነህ ብለው በሰየሙህ ግዜ ዕውነት ተናገሩ።››



  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄
2.9K viewsSulle man ثايهن, 18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 20:57:10 #ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ !
ጉዴን እማዋዬው አለኝታዬ ነቢ!
ነቢ ከጌትዬው መግባቢያ ቋንቋዬ፣ አስታራቂዬ፣ ወደ እልፍኝ
አዳራሹ እጄን ይዘው የሚያስገቡኝ አሳላፊዬ፣ ወደምፈልገው
መዳረሻዬ መንገዴ መንሃጄ ቂብላዬ ፊርቃዬ ጀምዓዬ ሶላቴ
የሁለት ዓለም ጀነቴ!
ለነቢ ያለኝ ፍቅር ሸርጡን ባይሞላም አውቀዋለሁ መዳኛዬ
ነው። ስማቸውን የማነሳበት ሶለዋትም ጭንቁን ሁሉ
ማለፊያዬ ነው። እማዋይሁ ነቢ ባዋዬንሁ ሁሉ አጚሱና
ያረሱለሏህ! አዛኙ ነቢ፣ ጋሻዬ ነብይ፣ ሁሌም ክፍት የሆነ
የምህረት በር፣ ሺሊላ ብሎ የሚመጣን ሲጠባበቅ ውሎ
የሚያድር ጠጀሳር ያወደው የሙሐባ ቀዬ፣ ከዓለም በሰፋው
መንደር በነቢ ጊቢ ተገኘን ሁሉ ይከወንልን ብለን፣ ፋይል
ከፍተን ወደ መሃል ዳኛው አሳልፉን አስወስኑልን አገር ይሻር
ብለን!
አዛ እንዲረግፍ ሽተናልና እንደዛ የዓረብ ገጠሬ
የማረፊያቸውን መዝጊያ ይዘን የሙጥኝ እንላለን። እንዲህ
ሆኖ ነበር… ጭንቅ ቢለው፣ ቢጨልምበት ከመዳኛው ጋር
ወንጀሉ ያራራቀው ቢመስለው ነቢ ያረፉበት መቃብር መጣና
"ያረሱለላህ በጣም ከባድ ወንጀል ፈፅሚያለሁ። ነገር ግን
አላህ
ﻭﻟﻮ ﺃﻧﻬﻢ ﺇﺫ ﻇﻠﻤﻮﺍ ﺃﻧﻔﺴﻬﻢ ﺟﺎﺀﻭﻙ ﻓﺎﺳﺘﻐﻔﺮﻭﺍ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺍﺳﺘﻐﻔﺮ
ﻟﻬﻢ ﺍﻟﺮﺳﻮﻝ ﻟﻮﺟﺪﻭﺍ ﺍﻟﻠﻪ ﺗﻮﺍﺑﺎ ﺭﺣﻴﻤﺎ
"እነሱም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ግዜ ወደ አንተ ቢመጡና
አላህን ምህረት በለመኑ መልዕክተኛውም ለነርሱ ምሕረትን
በለመነላቸው ኖሮ አላህን ጸጸትን ተቀባይ አዛኝ ሆኖ ባገኙት
ነበር።" ማለቱን ሰምቻለሁና አሁን የተገኘሁት ምህረት
እንዲጠይቁልኝ ለመንገር ነው።" አለና እያለቀሰ አንዲትን
ግጥም አነብንቦ በእምባ ወደመጣበት ተመለሰ።
ይሄንን ክስተት አል-ኡትቢ እዬተመለከቱ ነበር። እንግዳው
ሰውዬ ከሄደ በኋላ ጥልቅ እንቅልፍ ወሰዳቸው።
በህልማቸውም ረሱሉላህን ﷺ ተመለከቱ። እንዲህም
አሏቸው። "ይህንን ሰው አግኘውና አላህ እንደማረው
አበስረው!" አሏቸው።
ሃዬ ሃዬ ቢጃሂ ሰይዲል ሙርሰሊን ስማቸውን ጠርተን
ወንጀላችን ተሰርዞ፣ ሃጃችን ሞልቶ፣ ድልና ፈረጃ ለ‘ኛ ሁኖ፣
አይበጆ ተበጥሮ፣ ወገን አማን ሁኖ ይንጋ!
#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ
አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዱና ወመውላና
ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!


 


                             
                                
                                      
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ




  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄
3.8K viewsSulle man ثايهن, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 21:26:55 # ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ !
ካለፈው የሚመጣው በላጭ ነው!!
እዋኛለሁ አለ ልኩን ያውቀዋል ወይ፣
አዟሪት ያለበት ባሕር አያውቅም ወይ!? ተብሏል።
አዎን በሕሩ መደዲሂ ለይሰ ለሁ ሀድዱን እንዳሉት ጥልቁንና ድካው የማይታወቀውን ባሕር ታንኳ ሳያዘጋጁ መሻገር አስምጦ ከመድረስ ያስቀራልና ደጉን ዋናተኛ ተከትለን ነው የምንቀዝፈው በታንኳው ተሳፍረን!
ሸህ ጫሊ
ሰባ ሽን ግርዶ በ‘ጁ ገለጠው፣
በኋላ መጥቶ ሁሉን በለጠው። አላሉም? እንኳን አምሳያ ቅጥያ ያልተገኘላቸው የኔ ነቢ ካለፈው ከሚመጣው፣ ሰማይ ካዬችው፣ ምድር ከያዘችው ሁሉ በላጭ ናቸው። ሲፋቸውም፣ እጣቸውም፣ ጌትዬው የዋለላቸውም ካለፈው ሁሉ የተሻለ ነው ኢላ የውሚል አኺር! "ወድዱሃ!" ብሎ ምሎ የሚጀምርበትን ምዕራፍ ዋናተኛው ሸኽ ሰዒድ ሱመያ ሲሻገሩት ብንከተላቸው ያገኘነውም ይሄንኑ ነው። "ማወድደዓከ ረብቡከ ወማ ቀላ!" ያለውን ጌታህ አልተወህም እያልን ስንፈስረው ኖረን ዳሩ ማዕናው ሌላም ዘውድ አለው። ያንተ ሹመት መሽሻር የሌለው የዳዒም ነው፣ መወደድህም ጥላቻ የማይመጣበት ነው፣ ሾሞሃል አትሻርም፣ ወዶሃል አትጥጠላም ነው ነገሩ አሉ። ሹመቱ የሆነው ለዓበድ የ‘ኛ ረሱል ነቢ ሙሐመድ ሙሐመድ! "ወለል አኺረቱ ኸይሩን ለከ ሚነል ዑላ!" ያለውን ደግሞ ዱንያ ላይ ካለው የመጪው ዓለም እድያ ላንተ የተሻለ ነው እያልን ስንደግም ኖረን ባለ ፈህሞቹ ሌላውንም ጌጥ ገለጥ ገለጥ እያደረጉ ውቡን ሸማ ደረቡልን። "ኢንነማ አነ ቃሲሙን ወሏሁ ዩዕጢ!" እንዳሉት ነው’ኮ። እኔ መልዕክቱን አሰራጫለሁ መርረዳቱን የሚሰጠው አላህ ነው ብለዋል። ሁሉ እኩል አይገባውም። አዎን የበለጠው ኸይር አኸራን ብቻ ጠባቂ አይደለም እዚሁ የታዬ የሚቀጥልም ነው። እኔ’ኮ ነብዬ ላይ ሳይደርስ፣ በዘመናቸው ሳይኖር የኸልቁ በተለይም የሐበሻ እንዲህ በፍቅር መንገብገብና የፍቅር አገላለፁ ሲርር መራቅ ይገርመኝ ነበር ለካስ ከነበረው የሚመጣው፣ አወል ከተባለው አኺሩ የሚበልጥበት መስመር ስላለ ነው!!
ሲዘረዝሩት ምን አሉ… ይሄ ሹመት ባንተ ተጀምሯል፣ እንቅስቃሴው ባንተ የሚያልቅም የሚቆምም አይደለም። በፈትሁል መካ ጊዜ እስልምና ጥቂት አካባቢዎችን ብቻ ነበር የደረሰው። ከዛ ግን ኤስያን አፍሪካን እንዲሁም መላውን ዓለም አዳረሰ። የሚመጣው ካለፈው ኸይር ነው። ነቢ ጌታቸውን ከተገናኙ በኋላ አቡበክር ቢተኩ ጀምዑል ቁርዓን ተገኘ። መሰብሰቡ ጠቀመ። ታቢዒይ ቢመጣ የተሻለ ኸይር መጣ። ወታቢዑ ታቢዒን ሆነ ዑለማ ቢመጣ "አልዬውመ አክመልቱ!" የሚለውን ሙላት እዬጠለቀ አንጀት የሚያርስ ሆነ። ተፍሲሩ፣ ፊቅሁ፣ ነህው፣ ሶርፉ በላጛው ቢጎርፍ የነቢን መንገድ አሳምሮ የሚያስቀጥል ሆነ። እነ ሀሰነል በስሪ በነቢም በሶሃባም ጊዜ የሌለ የዒልም ሰነድ እያቋቋሙ ሃቁን ከባጢል ጠበቁ፣ እነ አቡ ሀኒፋ ቁርዓንና ሃዲስ ላይ ተለይቶ ያልተቀመጠውን ዒልም ሁላ በአህካምና በክፍል እዬከፋፈሉ አደራጁ፣ እነ ኢማም ማሊክ እነ ሙዎጦዕን አበጅተው ለ‘ነ ሙስሊም ለ‘ነ ቡኻሪ አዳረሱ።
ጭማሪ የመሰለው ሁላ "ወለል አኺረቱ ኸይሩን ለከ ሚነል ዑላ!" ለሚለው መተግበሪያ እንዲሆን ከተሟላው ኑር ላይ ለዓይናማዎቹ የተገለጠ ነው። መልዕክታቸውን አድራሽ፣ አበጅ አሳማሪ አበዛላቸው ከአሳማሪዎች ያድርገንና፣ ካለፉ በኋላ የሚመጣውን እጣቸውን አስበለጠላቸው ካለፈው የሚመጣው እድላችን ይመርልንና!
# ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ !
አሏሑመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዱና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ ዓሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ

ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ


:¨·.·¨: ❀ ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
2.4K viewsSulle man ثايهن, 18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-09 22:15:37 #ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ !
አንቱን የወደደ ያገኛል ወይ ጤና!?
ግርማቸው የሚያስፈራ ወዲህም ጨዋታ አዋቂ ወዝ
ያላቸው ሸኽ ናቸው፥ ታድያ አንዱ ደረሳ ሳዳቶቹ አምጠው
የወለዱትን፣ ያስጨነቃቸውን የነቢን ናፍቆት የተነፈሱበትን
መድህ ነቢን ሊያነሳበት ፈልጎ አጠገባቸው "እንዴት ነሁ?
"እንዴት ነሁ?" እያለ ይወዘወዛል። ይሄንን ያዩት ሸኹ "ኧረ
እሳቸው ደህና ናቸው ደሞ ነቢን እንዴት ነሁ ይላል እንዴ!?
ይልቅ ለራስህ ሁን!" አሉት በፈገግታ። እውነታቸውን እኮ
ነው የጅብሪል ወዳጅ፣ ያ’ላህ ባለሟል፣ ኑራቸው ዓለሙን
ቀድሞ የተኸለቀው፣ "ሰው ይመስላል እንጂ አይደለም እንደ
ሰው!" የተባሉት የኸልቁ ሁላ አሽረፍ ምን ሊሆኑ?
እንደው ማዲሁም መጠየቃቸው፣ እኛም መከተላችን
የናፍቆትና የስስት፣ ከሩሕ ጋር የማውጋት ቢሆን እንጂ ከቶ
ከውኑ ያደገደገላቸው፣ ምድርም እንደ እናታቸው ማህጸን
በምቾት ያቀፈቻቸው፣ እዚህም እዛም ሰላም የሆኑት ነብይ
ምንም ይገጥማቸዋል ተብሎ አይደለም!
አማን ኢማናቸው እንኳን ለራሳቸው ለሌላውም ቢተርፍ
ነው‘ኮ
አማን ነው ምንም የለበት፣
አማን ነው ምንም የለበት፣
ወረቴ ነቢ የዋሉበት። የተባለው። የኔ ነቢ ባለሁበት ሃድራ
ግቡ ስጠራሁ!
ለወትሮው "የሞተ ተጎዳ!" ነበር ፈሊጡ። ነቢ ወደ አኸራ
ሲሻገሩ ግን ያለው የቆመው ነው የተጎዳው! እኩሎቹ
ናፋቂዎች "ወዳጁን ገዳይ እንዳንቱም የለ" ይሏቸዋል፤
ገሚሶቹ ደግሞ
ነቢ ያንቱ ነገር ቸገረ ብልሀቱ፣
ወዳጅ እንደ ጠላት የምትገድሉበቱ። እያሉ መልስ
ስላጡለት እርሳቸውን በወደዱ ቁጥር ስለሚገረፉበት
የፍቅርና የናፍቆት አለንጋ ጉዳይ በግርምት ያዜማሉ
ያንጎራጉራሉ።
"እ‘ሱን የወደደ ያገኛል ወይ ጤና?" ብለው የሚጠይቁና
ውዴታቸው ጤና የነሳቸው፣ ሃሳብና ትዝታቸው ውሎና
አዳራቸው ሁሉ እርሳቸው ጋር የሆነባቸው የሆነላቸው
በርካቶች ናቸው።
ያንቱን ሙሐባ የቀመሰ ሰው፣
ዑምሩን ይፈጃል እንዳስለቀሰው። እያሉ በየኸልዋው ሲያነቡ
ውለው የሚያድሩትም አያሌ ናቸው!
አዎን ሸውቁ ያባክናል፤ እልፎችን ወግቷል ገድሏል
አይረካም ደግሞ ሌላውንም ይፈልጋል ሰይዱና ጫልይ
መደዱ ሰዶ እያበለጘኝ፣
አባቴን ገድሎ እኔን ፈለገኝ። እንዳሉት።
እንጂ እርሳቸውማ ምን ይሆናሉ? ምንስ አለባቸው?ያሉበት
ዳኢም አማን ነው ፊትም አሁንም ዛሬም ነገም። ዋ ለራሴ፣
ይብላኝ ለ’ኔ እንጂ! እንደው ቢጨነቁም ቢያስቡም እንኳን
ለ’ኛው ነው። ለነገሩ የተወዳጁ አማን ለወዳጁም
ስለሚተርፍ ነው
የቂያማ ለታ የውመል ፊራቂ፣
ሙላው ሲያለቅስ ይሆናል ሳቂ። የተባለው። ስለ ሙሒብ
"ዓዛብ አይገባም በሱ ሑርመት" ተብሏልምና አብሽሩ
እንደው አወዬ ነቢ አወዬ ነቢ እያሉ ዋይ ዋይ ነውውው!
የጅብሪል ወዳጅ ያ’ላህ ባለሟል ሰይዲ ጀማሉል ጀማል!
#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ !
አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሐቢቡና ወመውላና
ሙሐመድ!!


 


                             
                                
                                      
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ




  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄
1.8K viewsSulle man ثايهن, 19:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 18:33:27 በቀንና በሌሊት 1000 ሶለዋት ያለ ፤ከዱንያና
ከአኺራ ቅጣት ነፃ ይሆናል።የቀብር ጥየቃን በትክክል
ይመልሳል። የቂያማን ጭንቀት ይገላገላል።በቀንና
በሌሊት 500 ሶለዋት ያለ_᎓ ቀልቡ ላይ ድህነት
አይገባም።ወንጀሉ እንደ ጤዛ ይረግፋል። ደስተኝነትን
ይለገሳል። በቀንና በማታ 100 ሶለዋት ያለ ፤
ከኒፋቅ ነፃ ይሆናል። ቂያማ ላይ ከሹሃዳዎች ጋ
ይሆናል። መቶ የዱንያና የአኺራ ሃጃው ይስተካከላል።
በቀንና በማታ 10 ሶለዋት ያለ ___፤ ቀኑን በሙሉ
በአሏህ ጥበቃ ይውላል።የእርሱና የወላጆቹ ወንጀል
ይማራል።እነዚህ ለአብነት የተጠቀሱ ናቸው። ከዚህ
ያልጠቀስኰቸውን በጣም ብዙ ጥቅሞችንም
ይጎናፀፋል።
መልካም ኸሚስ።
አሏሁመሶሊ ወሰሊም አላ ሠይዲና
ወመውላና ሙሀመድ ፣ወአላ አሊ ሠይዲና ሙሀመድ

#በዱዓ_በርቱ_እኛንም_ አትርሱን!

መልካም_አዳር_ሰይዲን_ከማየት_ጋር

ጁሙዓቱን ሙባረካ

በቅንነት ለወዳጂወ ያስየላልፉ ሸር

https://telegram.me/yeresulnfkrmeglecha
207 viewsSulle man ثايهن, 15:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 20:03:31 # ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ !
ሳሙና አድርጎታል ስምኩን ለወንጀል!
"ሰይዲ በሀሳብ ነውጥ ዉስጥ ሆነው አይተናቸው ምን እንዳሳሰባቸው
ብንጠይቃቸው
‘መካ ዉስጥ ሰላምታ ያቀርብልኝ የነበረ ዛፍ ታዉሶኝ ነዉ’ አሉ፡፡" ብለው
ተናገሩ አቡ ሁረይራ። ይህን መልዕክት ያነበቡት ሸክ ኢማም ጁነይድም
"የዛፍን ሰላምታ ያስታወሰ ነብይ ያንተን ሶለዋት እንዴት ይዘነጋት?" ይላሉ
፡፡ አንድም ትሁን ችላ የማይሉት የህዝባቸዉን ሰላምታ መሆኑን ያወቀስ
እንዴት ሰላምታዉን ይነፍጋል???
አሁንም ቅድምም፣ ዛሬም ነገም አሏሁመ ሶሊ አላ ሀቢቢከ ኸይሪ
ኸልቂክ! አልፉ ሶላት ወሰላም አላ ነቢቢ…አልፉ ሶላት ወሰላም አላ
ነቢቢ ሰይዲ ያረሱለሏህ! ዝዝዘህ!

ሱፍያኑ ሰውሪይ ሲቆምም ሲሄድም ሲቀመጥም ሲነሳም የወለላዬን ስም
ካፉ የማይለይን፣ ሌላ ዚክር የሌለ እስኪመስል ድረስ በርሳቸው ላይ
ሰላምታ በማውረድ የተጠመደን አንድ ወጣት አይተው በመገረም
ሚስጥሩን ቢጠይቁት የሆነውን ጉድ ና ልንገርህማ ጓዴ!ወጣቱ
ሚስጥሩን ያጫወታቸው እሳቸው መሆናቸውን ሲያስረግጥ ነው። የፍቅር
ነገር ሁሉ አይገባውማ!!
ከአባቱ ጋር ለሃጅ ጉዞ እንደወጡ ጉልበቱ የተዳከመው አባት ያሰበበት
ሳይደርስ ታመመና ጠንቶበት ወደ አኸራ ተሻገረ። ያም ብቻ አይደለም፥
የሚያምር የነበረው ፊቱ ከመቅጽበት ጽልመት አጠላበት። በዛ ምድረ
በዳ ይህ መከራ የወደቀበት ወጣት የሚያደርገው ግራ ገብቶት አዝኖ
በተቀመጠበት ድንገተኛ እንቅልፍ ሸለብ አደረገው።

በህልሙም ግርማ ሞገስ ያለውና የሚያምር ሰው ወደ አባቱ ራስ
ተጠግቶ በኑር እጁ ድብስብስ እያደረገ የጠቆረውን ፊቱን በፊት
ከነበረውም ይበልጥ ሲያስውበው ተመለከተ። "ማነህ?" ብሎ ሲጠይቅ
ነው ሚስጥሩ የገባው።
"እኔ ሙሐመድ ነኝ
ወዳጅ የምረዳ አላህ አግዞኝ!" አሉት። የሟቹን ፊት ያጠቆረው ወንጀሉ
እንደነበረ ግና የማይካድ ሃቅ አንድ ውብ ሥራ እንዳለው እሱም ሶለዋት
እንደሆነ ነገሩት!ጠቃሚ አካውንት!! አክለውም "መጥቼም መርዳቴ
ለዚሁ ምላሽ ነው፤ ሶለዋት ላበዛ አማልደዋለሁ፤ ዋስም እሆነዋለሁ፤
ወንጀሉንም አስምራለሁ…"እያሉት ሳለ ቢባንን በህልሙ ያዬው እውን
ሆኖ የአባቱ ውበት ተመልሶ መጥቶ አገኘው። እንግዲህ ከዛን ቀን ጀምሮ
ነው ከሶለዋት ቦዝኖ የማያውቀው።

ሰይዲ ወያሰነዲ!ስምዎ በዱንያ ሹመት ማ’ረጌ ወዲያ ደግሞ ዓዛብን
መሻገሪያዬ ነው!መለከል መውት ሲመጣ፣ ስታጠብም፣ ስከፈንም
በለሕድም በሲራጥም ይረዳኛል!ሸፊዑል ሙዝኒቢን! "ምን እንኳን ባልረባ
ሥራ ባይኖረኝ!" እንዳሉት "በስሙ ተማሩ አቡና አደሙ" እንደተባለውም
ነብያት እንኳን ዋስትናዎን ፈልገው "አኳኋኔን አይተሽ እንድትነግሪልኝ!"
ብለው እናታችን አሚና ጋር መለስ ቀለስ እንዳሉት ሁሉ እኔም
ልመዝገብ፣ ባለሟል ልሁን!
# ሶሉ_ዓለል_ሃቢብ !
አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪከ ዓላ ሰይዱና ወመውላና ሙሐመድ!

https://telegram.me/yeresulnfkrmeglecha
2.3K viewsSulle man ثايهن, 17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 02:20:16 ነብዩ ( ﷺ ) እና ጅብሪል ( ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺴﻼﻡ )
አንድ ቀን ነብዩ ( ﷺ ) ጅብሪልን ( ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺴﻼﻡ ) ይህንን
ጥያቄ ጠየቁት…
ነብዩ፦ «በከፍተኛ ፍጥነት በረህ ታውቃለህ?»
ጅብሪል፦ «አዎ በአራት አጋጣሚዎች»
ነብዩ፦ «አራቱ አጋጣሚዎች ምን ነበሩ?»
ጅብሪል፦ «ለመጀመሪያ ጊዜ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በኒምሩድ
እሳት ውስጥ ሲገባ ነበር። በወቅቱ እኔ የአርሽ ዙፋን ላይ
ነበርኩ። እሳቱን እንዳበርድ አላህ አዘዘኝ። አርሹን ትቼ ሰባት
ሰማያትን በፍጥነት ወረድኩ።
ለሁለተኛ ጊዜ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ልጁን እስማኤልን በሚና
ሊሰዋው ሲል ነበር። ኢብራሂም (የእስማኤል አንገትን)
በቢላዋ ከመንካቱ በፊት አላህ ልጁን በበግ እንድተካ
አዘዘኝ።
ሦስተኛው የዩሱፍ ወንድሞች (ዩሱፍን) ወደ ጉድጓዱ
ውስጥ ሲጥሉት ነው። ዩሱፍን እንዳድን አላህ አዘዘኝ።
ዩሱፍ ወደ ጉድጓዱ ግርጌ ከመድረሱ በፊት በፍጥነት ሄጄ
ክንፌን ከስሩ አስቀመጥኩት።
…እና የመጨረሻው አንተ ያ ረሱለላህ ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም በኡሁድ ጦርነት ጥርስህን የተጎዳህበት ጊዜ
ነበር። አሏህ ደምህ መሬት ከመንካቱ በፊት እንዳቆመው
አዘዘኝ። ይህንን ባላደርግ ኖሮ ምንም አይነት ተክል ወይም
ዛፍ እስከ የውመል ቂያማ ድረስ መብቀል አይችልም ነበር።
ይህን ሰምቼ በፍጥነት ደምህን ከመንካቱ በፊት በክንፌ
አዳንኩት»
የቂን ይኑረን እንጂ አላህ (ሱ.ወ) መንገድ ሲጠፋን ሌላ
መንገድ ያዘጋጃል!
በዚህ በረመዳን የጀሊሉን ውዴታ የምናገኝበት እና
እቅዶቻችንን የምናሳካበት ወር ይሁን.... አሚን



ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ



:¨·.·¨: ❀ ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄
4.8K viewsSulle man ثايهن, 23:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-31 19:49:58 # ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ !
አሰላምዓለይኩም የጦይባው ሲራጅ፣ አንቱን የወደደ ዓይሹ ይደራጅ!
አሉ እነ ሸኽ ሙሐመድ ሲራጅ።
"ሙሐመድ ዓሚን" ታማኙ ሙሐመድ!
ይህ አጠራር የመካ ነዋሪዎች ትልቁን ሠው ይጠሩበት የነበረ አጠራር
ነው። የኔ ነብይ ሰማያዊውን መልእክት ከማምጣታቸውም ቀደም
ታማኝ፣ ዋሾና እምነት አጉዳይ ያልሆኑ፣ እንደ እኩዮቻቸው በዓለማዊ
ፈንጠዝያ የማይማልሉ ነበሩ። ይህንን ተፈጥሯቸውን አብጠርጥረው
የሚያዉቁት የአካባቢው ነዋሪዎች ታድያ ነቢን በሚግገባቸው ሥም
ነበር የሚጠሯቸው። ሙሐመዱል ዓሚን!
ሠዎች የያዙት መንገድ ጠማማም ይሁን ቅን ሥምህ ለመንገዳቸው
እንደሚጠቅም ካመኑ አልያም እንቅፋት ካልሆነባቸው አንተን
ለመቀበል ላያቅማሙ ይችላሉ። አልሆን ያላቸው ‘ለት ግን
የጨዋታውን ህግ ይቀይሩታል። በአለማወቅ በተሞላ ጭንቅላት ላይ
የድፍረትን ዘውድ በጫኑት የመካ ሙሽሪኮች ዘንድ የሆነውም ይኸው
ነበር። "ታማኙ ሙሐመድ" እያሉ ሲመሰክሩላቸው የነበሩት ነብይ
ጨለማቸውን በመለኮታዊው ብርሃን ሊገልጡ፣ የባጢል የእንቧይ
ካባቸውን በሀቅ ለመናድ ሲነሱ ከሽቶ የሚያውድ ሥማቸውን ጋዝ
ሊቀቡ ታተሩ። "እብድ፣ ዋሾ፣ ደጋሚ፣ ተረትና አፈታሪክ ተራኪ!"
የሚሉት አጠራሮች የምላሶቻቸው ቀለብ ሆኑ። ሐቁን የሚያውቀውን
ህሊናቸውን በድንቁርና ጨርቅ ሸፈኑት። አይገርምም!? ወዳጆቻቸው
ቀና ብለው ለማዬት የሚያፍሯቸውን፣ ጌትዬው ሠዎች ከርሳቸው ፊት
ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንኳን እንዳያወሩ የደነገገላቸውን፣ እኛ
ሶለዋታችን ራሱ አይመጥናቸውም ብለን የምንጨነቅላቸውን ነብይ
በኩራት የሚሳደብ፣ የሚዘልፍ፣ የሚያዋርድ ኸልቅ ነበር። ለዛውም
"በአላህ አምኛለሁ!" እያለ። ምን ታደርገዋለህ ነገሩ የአዘል ነው!
ጌትዬው ራሱ "አንተ ነብይ ሆይ" እያለ በሐያዕ ሸፈን አድርጎ እንጂ
ሥማቸውን ብዙም በቀጥታ አይጠራውም’ኮ! የደነደነው ደህኔሳ!?
ኻሊቁም መኽሉቁም የሳሳለትን ስብሥና ስብ ካልቀባሁ ይላል! መገን
ቀድርን አለማወቅ!
ጌትዬውማ መሸላለሙን ያውቅበታል!
ምግባራቸው ወርቅ ስለመሆኑ "ወኢንነከ ለዓላ ኹሉቂን ዓዚም!" አለ።
አዛኝ እንስፍስፍነታቸውን የራሱን ስም አውሶ "ቢል ሙዕሚኒነ ረዑፉን
ረሒም" ሲል ገለጸ። ስለመውወሳታቸው "ወረፈዕና ለከ ዚክረክ" አለን።
ከፍቷቸው አዝነው "ጌታዬ ትቶኝ ነው!" ብለው ባሰቡ ጊዜ ደግሞ ይህ
ፈጽሞ የማይታሰብ እንደሆነ አስረግጦ ካለፈው ሁሉ የሚመጣው
የበለጠ እንደሚሆንላቸው "ወለል አኺረቱ ኸይሩን ለከ ሚነል ዑላ!"
ብሎ ቃል ገባላቸው።
የከውሰርስ ብስራት እንዴት ይረሳል?
የኔ ውድ ነብይ ወንድ ልጅ ሲወልዱ ሁሌም ወዲያው ይሞትባቸው
ነበር። አንድ ቀን ታድያ በመካ ከተማ ሲዘዋወሩ አንድ ሙሽሪክ
ይመለከታቸውና "አንተ አብተር (ዘሩ የማይበረክትለት)" ብሎ
አፌዘባቸው። ዘርህን ካልተካህ እንደሞትክ ትረሳለህ። ባንተ ሥም
የሚጠራ ልጅ ስለሌለህ የሚያስታውስህም የለም። ነው አባባሉ። ነቢ
ይህን ሲሰሙ ሀዘን ከበባቸው። ወዳጃቸው ታድያ ፈጥኖ ደራሽ ነውና
"ኢንና አዕጦይናከልከውሰር" በምትለው አያ አበሰራቸው። ከውሰር
የተባለን የጀነት ጅረት ሰጥተንሃል። ካንተ ሌላ ማንም አይቀምሰውም።
በሚያፌዙብህ ነገር እንዳታዝን። አንተ ብቻ ለጌታህ ስገድ፣
እርድህንም በስሙ አድርግ፣ ለሚስኪንም ድረስ እንጂ አታስብ። ያ
ጭራሽ አንተን ‘ዘር የማይበረክትለት’ ብሎ የዘለፈህን ሰውዬማ እሱን
ራሱን ዘር አልባ አደርገዋለሁ። በዱንያም በአኸራም ስለሱ
የሚያወሳም እሱን የሚጠይቅም እንዳይኖር አድርጌ እተውልሃለሁ።
ተባሉ። የኔ ውድ ሠው ምንም እንኳን ወንድ ልጅ ባያገኙም በዚሁ
ሰበብ በጀነት ከውሰር ተሰጥቷቸዋል። ምንም እንኳን በስማቸው
የሚጥጠራ ወንድ ልጅ ባይኖራቸውም እልፍ አዕላፍ ወዳጆቻቸው
ልጆቻቸውን ሙሐመድ ብለው ሰይመውላቸዋል። ምድር ላይ ከኖሩበት
ዘመን አንስቶ አሁን ድረስ ቀን ማታ ሥማቸውን የሚጠራ ናፋቂ፣
ለመንገዳቸው ለፍቅራቸው የሚስሰዋ አያሌ ወዳጅ፣ ነቢ ነቢ እያለ
በሶለዋት የሚኖር እልፍ ተከታይ ተገኝቶላቸዋል። መውወሳታቸው
ከፍፍ ተደርጓል ቃሉም "ወረፈዕና ለከ ዚክረክ" ነውና!
ቁርዓን ያለፈውን የሚተርከው ክስተት ሁሉ ሊዑሊል አልባብ ትምህርት
ስላለው ነው። ወላሂ ወቢላህ እኔ ለስድብ ቀርቶ ለነርሱ ዱዓ
ለማድረግ የማፍር ነኝና የነቢ ወራሽ ዑለሞች ላይ ምላሱን
የሚሞርድን ሁሉ ከነዛ ሰዎች ለይቼ አላዬውም! ልብ አድርግ ወዳጁ
ላይ የወረወርከውን ጦር ቀልቦ ምላሹን የሚሰጥህ ራሱ ነው።
ወዳጆቹን በክፉ አይቶ ኺታሙ ያልከፋ ታገኝ እንደሆነ ዞር ዞር ብለህ
ተመልከት!
ሐይያ ዓለሶለዋት!
# ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ !
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ
ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!




                             
                                
                                      
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ




  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄
1.1K viewsZ, 16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ