Get Mystery Box with random crypto!

# ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ ! አሰላምዓለይኩም የጦይባው ሲራጅ፣ አንቱን የወደደ ዓይሹ ይደራጅ! አሉ እነ | ሁስነል ኹሉቅ

# ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ !
አሰላምዓለይኩም የጦይባው ሲራጅ፣ አንቱን የወደደ ዓይሹ ይደራጅ!
አሉ እነ ሸኽ ሙሐመድ ሲራጅ።
"ሙሐመድ ዓሚን" ታማኙ ሙሐመድ!
ይህ አጠራር የመካ ነዋሪዎች ትልቁን ሠው ይጠሩበት የነበረ አጠራር
ነው። የኔ ነብይ ሰማያዊውን መልእክት ከማምጣታቸውም ቀደም
ታማኝ፣ ዋሾና እምነት አጉዳይ ያልሆኑ፣ እንደ እኩዮቻቸው በዓለማዊ
ፈንጠዝያ የማይማልሉ ነበሩ። ይህንን ተፈጥሯቸውን አብጠርጥረው
የሚያዉቁት የአካባቢው ነዋሪዎች ታድያ ነቢን በሚግገባቸው ሥም
ነበር የሚጠሯቸው። ሙሐመዱል ዓሚን!
ሠዎች የያዙት መንገድ ጠማማም ይሁን ቅን ሥምህ ለመንገዳቸው
እንደሚጠቅም ካመኑ አልያም እንቅፋት ካልሆነባቸው አንተን
ለመቀበል ላያቅማሙ ይችላሉ። አልሆን ያላቸው ‘ለት ግን
የጨዋታውን ህግ ይቀይሩታል። በአለማወቅ በተሞላ ጭንቅላት ላይ
የድፍረትን ዘውድ በጫኑት የመካ ሙሽሪኮች ዘንድ የሆነውም ይኸው
ነበር። "ታማኙ ሙሐመድ" እያሉ ሲመሰክሩላቸው የነበሩት ነብይ
ጨለማቸውን በመለኮታዊው ብርሃን ሊገልጡ፣ የባጢል የእንቧይ
ካባቸውን በሀቅ ለመናድ ሲነሱ ከሽቶ የሚያውድ ሥማቸውን ጋዝ
ሊቀቡ ታተሩ። "እብድ፣ ዋሾ፣ ደጋሚ፣ ተረትና አፈታሪክ ተራኪ!"
የሚሉት አጠራሮች የምላሶቻቸው ቀለብ ሆኑ። ሐቁን የሚያውቀውን
ህሊናቸውን በድንቁርና ጨርቅ ሸፈኑት። አይገርምም!? ወዳጆቻቸው
ቀና ብለው ለማዬት የሚያፍሯቸውን፣ ጌትዬው ሠዎች ከርሳቸው ፊት
ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንኳን እንዳያወሩ የደነገገላቸውን፣ እኛ
ሶለዋታችን ራሱ አይመጥናቸውም ብለን የምንጨነቅላቸውን ነብይ
በኩራት የሚሳደብ፣ የሚዘልፍ፣ የሚያዋርድ ኸልቅ ነበር። ለዛውም
"በአላህ አምኛለሁ!" እያለ። ምን ታደርገዋለህ ነገሩ የአዘል ነው!
ጌትዬው ራሱ "አንተ ነብይ ሆይ" እያለ በሐያዕ ሸፈን አድርጎ እንጂ
ሥማቸውን ብዙም በቀጥታ አይጠራውም’ኮ! የደነደነው ደህኔሳ!?
ኻሊቁም መኽሉቁም የሳሳለትን ስብሥና ስብ ካልቀባሁ ይላል! መገን
ቀድርን አለማወቅ!
ጌትዬውማ መሸላለሙን ያውቅበታል!
ምግባራቸው ወርቅ ስለመሆኑ "ወኢንነከ ለዓላ ኹሉቂን ዓዚም!" አለ።
አዛኝ እንስፍስፍነታቸውን የራሱን ስም አውሶ "ቢል ሙዕሚኒነ ረዑፉን
ረሒም" ሲል ገለጸ። ስለመውወሳታቸው "ወረፈዕና ለከ ዚክረክ" አለን።
ከፍቷቸው አዝነው "ጌታዬ ትቶኝ ነው!" ብለው ባሰቡ ጊዜ ደግሞ ይህ
ፈጽሞ የማይታሰብ እንደሆነ አስረግጦ ካለፈው ሁሉ የሚመጣው
የበለጠ እንደሚሆንላቸው "ወለል አኺረቱ ኸይሩን ለከ ሚነል ዑላ!"
ብሎ ቃል ገባላቸው።
የከውሰርስ ብስራት እንዴት ይረሳል?
የኔ ውድ ነብይ ወንድ ልጅ ሲወልዱ ሁሌም ወዲያው ይሞትባቸው
ነበር። አንድ ቀን ታድያ በመካ ከተማ ሲዘዋወሩ አንድ ሙሽሪክ
ይመለከታቸውና "አንተ አብተር (ዘሩ የማይበረክትለት)" ብሎ
አፌዘባቸው። ዘርህን ካልተካህ እንደሞትክ ትረሳለህ። ባንተ ሥም
የሚጠራ ልጅ ስለሌለህ የሚያስታውስህም የለም። ነው አባባሉ። ነቢ
ይህን ሲሰሙ ሀዘን ከበባቸው። ወዳጃቸው ታድያ ፈጥኖ ደራሽ ነውና
"ኢንና አዕጦይናከልከውሰር" በምትለው አያ አበሰራቸው። ከውሰር
የተባለን የጀነት ጅረት ሰጥተንሃል። ካንተ ሌላ ማንም አይቀምሰውም።
በሚያፌዙብህ ነገር እንዳታዝን። አንተ ብቻ ለጌታህ ስገድ፣
እርድህንም በስሙ አድርግ፣ ለሚስኪንም ድረስ እንጂ አታስብ። ያ
ጭራሽ አንተን ‘ዘር የማይበረክትለት’ ብሎ የዘለፈህን ሰውዬማ እሱን
ራሱን ዘር አልባ አደርገዋለሁ። በዱንያም በአኸራም ስለሱ
የሚያወሳም እሱን የሚጠይቅም እንዳይኖር አድርጌ እተውልሃለሁ።
ተባሉ። የኔ ውድ ሠው ምንም እንኳን ወንድ ልጅ ባያገኙም በዚሁ
ሰበብ በጀነት ከውሰር ተሰጥቷቸዋል። ምንም እንኳን በስማቸው
የሚጥጠራ ወንድ ልጅ ባይኖራቸውም እልፍ አዕላፍ ወዳጆቻቸው
ልጆቻቸውን ሙሐመድ ብለው ሰይመውላቸዋል። ምድር ላይ ከኖሩበት
ዘመን አንስቶ አሁን ድረስ ቀን ማታ ሥማቸውን የሚጠራ ናፋቂ፣
ለመንገዳቸው ለፍቅራቸው የሚስሰዋ አያሌ ወዳጅ፣ ነቢ ነቢ እያለ
በሶለዋት የሚኖር እልፍ ተከታይ ተገኝቶላቸዋል። መውወሳታቸው
ከፍፍ ተደርጓል ቃሉም "ወረፈዕና ለከ ዚክረክ" ነውና!
ቁርዓን ያለፈውን የሚተርከው ክስተት ሁሉ ሊዑሊል አልባብ ትምህርት
ስላለው ነው። ወላሂ ወቢላህ እኔ ለስድብ ቀርቶ ለነርሱ ዱዓ
ለማድረግ የማፍር ነኝና የነቢ ወራሽ ዑለሞች ላይ ምላሱን
የሚሞርድን ሁሉ ከነዛ ሰዎች ለይቼ አላዬውም! ልብ አድርግ ወዳጁ
ላይ የወረወርከውን ጦር ቀልቦ ምላሹን የሚሰጥህ ራሱ ነው።
ወዳጆቹን በክፉ አይቶ ኺታሙ ያልከፋ ታገኝ እንደሆነ ዞር ዞር ብለህ
ተመልከት!
ሐይያ ዓለሶለዋት!
# ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ !
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ
ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!




                             
                                
                                      
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ




  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄