Get Mystery Box with random crypto!

# ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ ! ካለፈው የሚመጣው በላጭ ነው!! እዋኛለሁ አለ ልኩን ያውቀዋል ወይ፣ አዟሪ | ሁስነል ኹሉቅ

# ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ !
ካለፈው የሚመጣው በላጭ ነው!!
እዋኛለሁ አለ ልኩን ያውቀዋል ወይ፣
አዟሪት ያለበት ባሕር አያውቅም ወይ!? ተብሏል።
አዎን በሕሩ መደዲሂ ለይሰ ለሁ ሀድዱን እንዳሉት ጥልቁንና ድካው የማይታወቀውን ባሕር ታንኳ ሳያዘጋጁ መሻገር አስምጦ ከመድረስ ያስቀራልና ደጉን ዋናተኛ ተከትለን ነው የምንቀዝፈው በታንኳው ተሳፍረን!
ሸህ ጫሊ
ሰባ ሽን ግርዶ በ‘ጁ ገለጠው፣
በኋላ መጥቶ ሁሉን በለጠው። አላሉም? እንኳን አምሳያ ቅጥያ ያልተገኘላቸው የኔ ነቢ ካለፈው ከሚመጣው፣ ሰማይ ካዬችው፣ ምድር ከያዘችው ሁሉ በላጭ ናቸው። ሲፋቸውም፣ እጣቸውም፣ ጌትዬው የዋለላቸውም ካለፈው ሁሉ የተሻለ ነው ኢላ የውሚል አኺር! "ወድዱሃ!" ብሎ ምሎ የሚጀምርበትን ምዕራፍ ዋናተኛው ሸኽ ሰዒድ ሱመያ ሲሻገሩት ብንከተላቸው ያገኘነውም ይሄንኑ ነው። "ማወድደዓከ ረብቡከ ወማ ቀላ!" ያለውን ጌታህ አልተወህም እያልን ስንፈስረው ኖረን ዳሩ ማዕናው ሌላም ዘውድ አለው። ያንተ ሹመት መሽሻር የሌለው የዳዒም ነው፣ መወደድህም ጥላቻ የማይመጣበት ነው፣ ሾሞሃል አትሻርም፣ ወዶሃል አትጥጠላም ነው ነገሩ አሉ። ሹመቱ የሆነው ለዓበድ የ‘ኛ ረሱል ነቢ ሙሐመድ ሙሐመድ! "ወለል አኺረቱ ኸይሩን ለከ ሚነል ዑላ!" ያለውን ደግሞ ዱንያ ላይ ካለው የመጪው ዓለም እድያ ላንተ የተሻለ ነው እያልን ስንደግም ኖረን ባለ ፈህሞቹ ሌላውንም ጌጥ ገለጥ ገለጥ እያደረጉ ውቡን ሸማ ደረቡልን። "ኢንነማ አነ ቃሲሙን ወሏሁ ዩዕጢ!" እንዳሉት ነው’ኮ። እኔ መልዕክቱን አሰራጫለሁ መርረዳቱን የሚሰጠው አላህ ነው ብለዋል። ሁሉ እኩል አይገባውም። አዎን የበለጠው ኸይር አኸራን ብቻ ጠባቂ አይደለም እዚሁ የታዬ የሚቀጥልም ነው። እኔ’ኮ ነብዬ ላይ ሳይደርስ፣ በዘመናቸው ሳይኖር የኸልቁ በተለይም የሐበሻ እንዲህ በፍቅር መንገብገብና የፍቅር አገላለፁ ሲርር መራቅ ይገርመኝ ነበር ለካስ ከነበረው የሚመጣው፣ አወል ከተባለው አኺሩ የሚበልጥበት መስመር ስላለ ነው!!
ሲዘረዝሩት ምን አሉ… ይሄ ሹመት ባንተ ተጀምሯል፣ እንቅስቃሴው ባንተ የሚያልቅም የሚቆምም አይደለም። በፈትሁል መካ ጊዜ እስልምና ጥቂት አካባቢዎችን ብቻ ነበር የደረሰው። ከዛ ግን ኤስያን አፍሪካን እንዲሁም መላውን ዓለም አዳረሰ። የሚመጣው ካለፈው ኸይር ነው። ነቢ ጌታቸውን ከተገናኙ በኋላ አቡበክር ቢተኩ ጀምዑል ቁርዓን ተገኘ። መሰብሰቡ ጠቀመ። ታቢዒይ ቢመጣ የተሻለ ኸይር መጣ። ወታቢዑ ታቢዒን ሆነ ዑለማ ቢመጣ "አልዬውመ አክመልቱ!" የሚለውን ሙላት እዬጠለቀ አንጀት የሚያርስ ሆነ። ተፍሲሩ፣ ፊቅሁ፣ ነህው፣ ሶርፉ በላጛው ቢጎርፍ የነቢን መንገድ አሳምሮ የሚያስቀጥል ሆነ። እነ ሀሰነል በስሪ በነቢም በሶሃባም ጊዜ የሌለ የዒልም ሰነድ እያቋቋሙ ሃቁን ከባጢል ጠበቁ፣ እነ አቡ ሀኒፋ ቁርዓንና ሃዲስ ላይ ተለይቶ ያልተቀመጠውን ዒልም ሁላ በአህካምና በክፍል እዬከፋፈሉ አደራጁ፣ እነ ኢማም ማሊክ እነ ሙዎጦዕን አበጅተው ለ‘ነ ሙስሊም ለ‘ነ ቡኻሪ አዳረሱ።
ጭማሪ የመሰለው ሁላ "ወለል አኺረቱ ኸይሩን ለከ ሚነል ዑላ!" ለሚለው መተግበሪያ እንዲሆን ከተሟላው ኑር ላይ ለዓይናማዎቹ የተገለጠ ነው። መልዕክታቸውን አድራሽ፣ አበጅ አሳማሪ አበዛላቸው ከአሳማሪዎች ያድርገንና፣ ካለፉ በኋላ የሚመጣውን እጣቸውን አስበለጠላቸው ካለፈው የሚመጣው እድላችን ይመርልንና!
# ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ !
አሏሑመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዱና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ ዓሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ

ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ


:¨·.·¨: ❀ ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄