Get Mystery Box with random crypto!

#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ ! አንቱን የወደደ ያገኛል ወይ ጤና!? ግርማቸው የሚያስፈራ ወዲህም ጨዋታ አዋ | ሁስነል ኹሉቅ

#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ !
አንቱን የወደደ ያገኛል ወይ ጤና!?
ግርማቸው የሚያስፈራ ወዲህም ጨዋታ አዋቂ ወዝ
ያላቸው ሸኽ ናቸው፥ ታድያ አንዱ ደረሳ ሳዳቶቹ አምጠው
የወለዱትን፣ ያስጨነቃቸውን የነቢን ናፍቆት የተነፈሱበትን
መድህ ነቢን ሊያነሳበት ፈልጎ አጠገባቸው "እንዴት ነሁ?
"እንዴት ነሁ?" እያለ ይወዘወዛል። ይሄንን ያዩት ሸኹ "ኧረ
እሳቸው ደህና ናቸው ደሞ ነቢን እንዴት ነሁ ይላል እንዴ!?
ይልቅ ለራስህ ሁን!" አሉት በፈገግታ። እውነታቸውን እኮ
ነው የጅብሪል ወዳጅ፣ ያ’ላህ ባለሟል፣ ኑራቸው ዓለሙን
ቀድሞ የተኸለቀው፣ "ሰው ይመስላል እንጂ አይደለም እንደ
ሰው!" የተባሉት የኸልቁ ሁላ አሽረፍ ምን ሊሆኑ?
እንደው ማዲሁም መጠየቃቸው፣ እኛም መከተላችን
የናፍቆትና የስስት፣ ከሩሕ ጋር የማውጋት ቢሆን እንጂ ከቶ
ከውኑ ያደገደገላቸው፣ ምድርም እንደ እናታቸው ማህጸን
በምቾት ያቀፈቻቸው፣ እዚህም እዛም ሰላም የሆኑት ነብይ
ምንም ይገጥማቸዋል ተብሎ አይደለም!
አማን ኢማናቸው እንኳን ለራሳቸው ለሌላውም ቢተርፍ
ነው‘ኮ
አማን ነው ምንም የለበት፣
አማን ነው ምንም የለበት፣
ወረቴ ነቢ የዋሉበት። የተባለው። የኔ ነቢ ባለሁበት ሃድራ
ግቡ ስጠራሁ!
ለወትሮው "የሞተ ተጎዳ!" ነበር ፈሊጡ። ነቢ ወደ አኸራ
ሲሻገሩ ግን ያለው የቆመው ነው የተጎዳው! እኩሎቹ
ናፋቂዎች "ወዳጁን ገዳይ እንዳንቱም የለ" ይሏቸዋል፤
ገሚሶቹ ደግሞ
ነቢ ያንቱ ነገር ቸገረ ብልሀቱ፣
ወዳጅ እንደ ጠላት የምትገድሉበቱ። እያሉ መልስ
ስላጡለት እርሳቸውን በወደዱ ቁጥር ስለሚገረፉበት
የፍቅርና የናፍቆት አለንጋ ጉዳይ በግርምት ያዜማሉ
ያንጎራጉራሉ።
"እ‘ሱን የወደደ ያገኛል ወይ ጤና?" ብለው የሚጠይቁና
ውዴታቸው ጤና የነሳቸው፣ ሃሳብና ትዝታቸው ውሎና
አዳራቸው ሁሉ እርሳቸው ጋር የሆነባቸው የሆነላቸው
በርካቶች ናቸው።
ያንቱን ሙሐባ የቀመሰ ሰው፣
ዑምሩን ይፈጃል እንዳስለቀሰው። እያሉ በየኸልዋው ሲያነቡ
ውለው የሚያድሩትም አያሌ ናቸው!
አዎን ሸውቁ ያባክናል፤ እልፎችን ወግቷል ገድሏል
አይረካም ደግሞ ሌላውንም ይፈልጋል ሰይዱና ጫልይ
መደዱ ሰዶ እያበለጘኝ፣
አባቴን ገድሎ እኔን ፈለገኝ። እንዳሉት።
እንጂ እርሳቸውማ ምን ይሆናሉ? ምንስ አለባቸው?ያሉበት
ዳኢም አማን ነው ፊትም አሁንም ዛሬም ነገም። ዋ ለራሴ፣
ይብላኝ ለ’ኔ እንጂ! እንደው ቢጨነቁም ቢያስቡም እንኳን
ለ’ኛው ነው። ለነገሩ የተወዳጁ አማን ለወዳጁም
ስለሚተርፍ ነው
የቂያማ ለታ የውመል ፊራቂ፣
ሙላው ሲያለቅስ ይሆናል ሳቂ። የተባለው። ስለ ሙሒብ
"ዓዛብ አይገባም በሱ ሑርመት" ተብሏልምና አብሽሩ
እንደው አወዬ ነቢ አወዬ ነቢ እያሉ ዋይ ዋይ ነውውው!
የጅብሪል ወዳጅ ያ’ላህ ባለሟል ሰይዲ ጀማሉል ጀማል!
#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ !
አላሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሐቢቡና ወመውላና
ሙሐመድ!!


 


                             
                                
                                      
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ




  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄