2022-03-10 19:28:09
# ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ !
መውላና ጀላሉዲን ሩሚ "ነፍስ አእምሮ የማይረዳውን ለመስማት የራሷ ጆሮ ተሰጥቷታል።"
ይላሉ። አዎን አንዳንድ ከአእምሮ በላይ የሆኑ ነገሮች አሉ፥ ነፍሶች ብቻ ተጠቃቅሰው
የሚግባቡባቸው። አንዳንድ የፍቅር ወጎች አሉ። ጥልቅ የሆኑ፣ የአንደበት ቋንቋ ችሎ
የማይገልጻቸው፣ በነፍስ ባሕር ውስጥ ታልመው እዛው የሚፍፈቱ! የተወዳጁ ነብይ
አፍቃሪዎች ነገርም እንደዚህ ነው የሚሆንብኝ። ከስሌት ይርቅብኛል፤ ማስተንተን
ከምችለው ይገዝፍብኛል፤ ከአድማስም ከጎራም ይሻገርብኛል።
እስኪ የአንድ ወዳጃቸውን ጥግ የደረሰና በታማኝነት ያሸበረቀ የጉድ ፍቅር ላሳያችሁና
እናንተው ፍረዱኝ!
አብደሏህ ኢብን ኹዛፋ አስሰሃሚ ረ.ዓ ነቢ ለመልእክት አድራሽነት የመረጡት ታማኝ
ባለሟል ነበር። አንዴ ወደ ፐርሽያው ንጉስ ደብዳቤ አስይዘው ላኩት። በሥፍራው
እንደደረሰም ንጉሱ ደብዳቤውን ከአብደሏህ እንዲቀበል ከታዛዥ አሽከሮቹ አንዱን ላከበት።
ይህ ታድያ ለአብደሏህ የማይሆን ነገር ነበር። ፈርጠም ብሎ "አይሆንም" አለ። ምክንያቱም
ነቢ ያዘዙት ደብዳቤውን በቀጥታ ለንጉሱ እንዲሰጥ ስለነበረ በመሃል አገናኝ መግባቱን
አልወደደውም። የረሱሉሏህን ቃል ማጉደል ነው አለ። የነቢ ትእዛዝ ከሚሸራረፍ ምንም
ቢቀር የሚመርጥ ሠው ነበር። ንጉሱ ይሄ በራሱ አበሳጭቶታል። ደብዳቤው በአላህ ስም፣
ከአላህ መልእክተኛ ተብሎ መነበብ ሲጀምር ደግሞ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣና
ቀዳደደው። የኔ ነቢ ንጉሱ የላኩትን ደብዳቤ በእብሪት መቅደዱን ሲሰሙ ለወዳጃቸው
አንሾካሾኩ። ዘውዱ ይነቀል! በአዘል የተፈረደበት ውልግድ ነውና ጭራሽ ነቢን ይዘው
እንዲያመጡለትም ወታደሮች ልኮ ነበር። የተላኩት ወታደሮች መዲና ሲደርሱ የኔ ወልይ፣
ትልቁ ሠው ጌታቸው ያሳወቃቸውን እንዲህ አሳወቋቸው። እብሪተኛው ሠው በራሱ ልጅ
መገደሉን አረዷቸው። የማይንነካ ነክቶ ተላሰ። ኪስራ ከሰረ!መገን አብደሏህ ይህ ሁሉ
በእርሱ ሰበብ ነው’ኮ!
በነቢ ፍቅርና ታማኝነት የታነጸው አብደሏህ ነገር ቀጥሏል። በአስራ ዘጠነኛው ዓ.ሒ
ኸሊፋው ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ረ.ዓ አብደሏህን ከባልደረቦቹ ጋር ወደ ሮማ ይልኩታል።
እዛ ደግሞ ሄርኩለስ አብደሏህን እምነቱን እንዲቀይር በውድም በግድም በበዛ ስቃይም
ሞከረው። ዓይኑ እያዬ ከባልደረቦቹ አንዱን የፈላ ውሃ ውስጥ ከተተው። ብቻውን ባለበት
ውበቷ ፈታኝ የተባለ ሴት ላከበት። እስኪደክማት ሞከረች። የጌታውና የነቢ ፍቅር ከለላ
ሆነው። ወታደሮቹ እሱን ዒላማ አድርገው ዙሪያውን ቀስት እዬወረወሩ እንዲያስፈራሩት
አደረገ። አንዱም ማስፈራሪያ ሊሰራለት አልቻለም። ሄርኩለስ ሌላኛውን ባልደረባውን
አጠገቡ ሲገሽረው ሲያይ ግን አብደሏህ ማልቀስ ጀመረ። ንጉሱ ደስ አለው። ያሸነፈ
መሰለው። አብደሏህ ግና የእንባ ዘለላዎቹ ከፍርሃት የመነጩ እንዳልሆኑ አሳወቀ።
ያስለቀሰው ነቢ ላመጡት መልእክት ቢሞት እንኳን የሚሞተው አንዴ ብቻ መሆኑ ነበር።
እናም እንድ ሽህ ነፍስ ኖሮት እያንዳንዷን ነፍሱን በነቢ መንገድ ቢሰዋ ደስታው መሆኑን
ገለፀ። ሄርኩለስ በፅናቱ፣ በጀግንነቱ፣ ላመነበት ሟች በመሆኑ እጅጉን ተደምሟል። እናም
ለውዱ አብደሏህ አንድ የመጨረሻ ምርጫ አቀረበለት። "ግንባሬን ሳመኝና በነፃ
ልልቀቅህ!" አለው። "አንድ ሠው ለራሱ የወደደውን ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ
አላመነም!" ያሉት ነብይ ወዳጅ የሆነው አብደሏህ ታድያ ሁሉንም ባልደረቦቹን ካልለቀቀ
ምኞቱ እንደማይሰምር አስረግጦ ነገረው። በመጨረሻም ሄርኩለስ እጅ ሰጠ። አብደሏህም
ቃሉን ፈፀመ።
አብደሏህና ባልደረቦቹ ነፃ ሆነው ወደ መነሻቸው ሲመለሱ የአብደሏህ ገድል በምድሪቷ
ቀድሞ ናኝቷል። ያኔ ኸሊፋ ዑመር እያንዳንዱ ሙስሊም የአብደሏህን ግንባር እንዲስም
አዘዙና ከራሳቸው ጀመሩ። በነቢ ኑር ያበራውን፣ ለጌታው እንጂ ለማንም ዝቅ ያላለውን
ግንባሩን ሳሙት። እንዴት ያለ ነብይ…እንዴት ያሉ ወዳጆች!!
ሐይያ ዓለሶለዋት!
# ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ !
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ
ወሰለም!
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡
እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
:¨·.·¨: ❀ ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄
664 viewsSulle man ثايهن, 16:28