Get Mystery Box with random crypto!

ሰሓባዎች ሶርያ አካባቢ የጦር ዘመቻ ሂደው በነበረበት ወቅት በግዜው የነበረው ከሊፋ ዑመር ረዐ ሊጎ | ሁስነል ኹሉቅ

ሰሓባዎች ሶርያ አካባቢ የጦር ዘመቻ ሂደው በነበረበት ወቅት በግዜው የነበረው
ከሊፋ ዑመር ረዐ ሊጎበኛቸው ፈልጎ ከመዲና ወደ ሻም ተጓዘ።
እንደ አጋጣሚ ሆና የምሳ ሰአት ላይ ከሊፋው ከሰራዊቱ መገኛ ደርሶ አቀባበል
ተደረገለት። የጦሩ መሪ የነበረውም አባ ኡበይዳ ረዐ ከሊፋውን ለምሳ ይዞት ወደ
ድንኳኑ ወሰደው።
ከሊፋው እና የጦሩ መሪ ከድንኳኑ ስር ሁነው ምሳ አቅራቢዎቹን በመጠባበቅ ላይ
ሳሉ አቅራቢዎቹ ወደ ከሊፋው ጠጋ ብለው፦‹‹የሰራዊት ምሳ እናቅርብልህ ወይስ
የጦር አዛዡን›› ሲሉ ጠየቁት።
ከሊፋው ግራ በመጋባት፦‹‹እስቲ ሁለቱንም አምጡልኝ›› አላቸው።
ሁለቱንም አመጡለትና በመጀመርያ የሰራዊቱን ምግብ ከፊቱ አቀረቡለት።
ከሊፋው ከፊቱ የቀረበለትን የሰራዊቱን ምግብ ሲመለከት ስጋ፣ መረቅ፣ እና
አትክልት በስጋ ተፈርፍሮ ፍፁም ቅንጡ የሆነ ምግብ ተመለከተ።
ግራ እየተጋባ፦‹‹እስቲ የጦር አዛዡን ምግብ አምጡልኝ›› ብሎ ጠየቀ።
ከኋላ ያስቀመጡትን የጦር አዛዡን ምግብ አቀረቡለት። ከፍቶ ሲመለከትም
የደረቀ ዳቦ እና ትንሽዬ ወተት ሁኖ አገኘው። ከሊፋው ዑመር ረዐ ከፊቱ
የቀረበውን የጦር አዛዡን እና የሰራዊቱን ምግቦች እየተመለከተ ተንሰቀሰቀ።
ወደ ጦር አዛዡ እየተመለከተ እንዲህም አለው፦‹‹ነቢ ሰዐወ የዚህ ኡማ ባለ
አደራ ነህ ብለው በሰየሙህ ግዜ ዕውነት ተናገሩ።››



  
      
ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡

እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ
                  
                 
              
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ይ ላ ሉን!
·. Telegram Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha

@yeresulnfkrmeglecha

┄┄┉┉✽̶»̶̥ ✿ »̶̥✽̶┉┉┄┄