2022-09-30 18:15:05
በቁርዓን ውስጥ የተጠቀሱት እንስሳዎች
وَٱلْخَيْلَ وَٱلْبِغَالَ وَٱلْحَمِيرَ لِتَرْكَبُوهَا
16:8 #ፈረሶችንም፣ #በቅሎዎችንም፣ አህዮችንም ልትቀመጡዋቸው…(#በቅሎ)
إِنَّ ٱللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تَذْبَحُوا۟ بَقَرَةًۭ ۖ -
2:67 «አላህ #ላምን እንድታርዱ ያዛችኋል»
۞ إِنَّ ٱللَّهَ لَا يَسْتَحْىِۦٓ أَن يَضْرِبَ مَثَلًۭا مَّا بَعُوضَةًۭ فَمَا فَوْقَهَا ۚ
2:26 አላህ ማንኛውንም ነገር ትንኝንም ኾነ (በትንሽነት ወይም በትልቅነት) ከበላይዋ የኾነንም ምሳሌ ለማድረግ አያፍርም፡፡(#ትንኝ)
أَفَلَا يَنظُرُونَ إِلَى ٱلْإِبِلِ كَيْفَ خُلِقَتْ
88:17 አይመለከቱምን? ወደ #ግመል እንዴት እነደተፈጠረች!
فَأَلْقَىٰ عَصَاهُ فَإِذَا هِىَ ثُعْبَانٌۭ مُّبِينٌۭ
7:107 በትሩንም ጣለ፡፡ እርስዋም ወዲያውኑ ግልጽ #እባብ ኾነች፡፡
كَأَنَّهُمْ جَرَادٌۭ مُّنتَشِرٌۭ
54:7 የተበተነ #አንበጣ መስለው ከመቃብሮቹ ይወጣሉ፡፡
إِنَّمَا حَرَّمَ عَلَيْكُمُ ٱلْمَيْتَةَ وَٱلدَّمَ وَلَحْمَ ٱلْخِنزِيرِ
2:173 በናንተ ላይ እርም ያደረገው በክትንና ደምን፣ የእሪያ(#አሳማ) ሥጋንም፣
فَلَمَّا عَتَوْا۟ عَن مَّا نُهُوا۟ عَنْهُ قُلْنَا لَهُمْ كُونُوا۟ قِرَدَةً خَٰسِـِٔينَ
7:166 ከእርሱም ከተከለከሉት ነገር በኮሩ ጊዜ ለእነሱ «ወረዶች #ዝንጀሮች ኹኑ አልን፤» (ኾኑም)፡፡
فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ ٱلطُّوفَانَ وَٱلْجَرَادَ وَٱلْقُمَّلَ وَٱلضَّفَادِعَ
7:133ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም ነቀዝንም #እንቁራሪቶችንም *በነሱ ላይ ላክን*
ثَمَٰنِيَةَ أَزْوَٰجٍۢ ۖ مِّنَ ٱلضَّأْنِ ٱثْنَيْنِ وَمِنَ ٱلْمَعْزِ ٱثْنَيْنِ ۗ
ስምንትን ዓይነቶች ከበግ ሁለትን (ወንድና ሴትን) #ከፍየልም ሁለትን (ፈጠረ)፡፡«
وَأَوْحَىٰ رَبُّكَ إِلَى ٱلنَّحْلِ
16:68 ጌታህም ወደ ንብ እንዲህ ሲል አሳወቀ…
وَتَفَقَّدَ ٱلطَّيْرَ فَقَالَ مَا لِىَ لَآ أَرَى ٱلْهُدْهُدَ
27:20 በራሪዎቹንም ተመለከተ፤ አለም #ሁድሁድን ለምን አላየውም!
فَأَرْسَلْنَا عَلَيْهِمُ ٱلطُّوفَانَ وَٱلْجَرَادَ وَٱلْقُمَّلَ وَٱلضَّفَادِعَ
7:133ወዲያም የወሃን ማጥለቅለቅ አንበጣንም ነቀዝንም #እንቁራሪቶችንም *በነሱ ላይ ላክን*
إِنَّ ٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ لَن يَخْلُقُوا۟ ذُبَابًۭا وَلَوِ ٱجْتَمَعُوا۟ لَهُۥ ۖ
22:73 እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸው (ጣዖታት) #ዝንብን ፈጽሞ አይፈጥሩም፡፡(ዝንብ)
كَمَثَلِ ٱلْحِمَارِ يَحْمِلُ أَسْفَارًۢا ۚ
62:5 ምሳሌ መጽሐፎችን እንደሚሸከም #አህያ ብጤ ነው፡፡(የቤት አህያ)
فَٱلْتَقَمَهُ ٱلْحُوتُ وَهُوَ مُلِيمٌۭ
37:142 እርሱም ተወቃሽ ሲሆን #ዐሳው ዋጠው፡፡
أَلَمْ تَرَ كَيْفَ فَعَلَ رَبُّكَ بِأَصْحَٰبِ ٱلْفِيلِ
105:1 #በዝሆኑ ባለቤቶች ጌታህ እንዴት እንደሠራ አላወቅህምን?
فَرَّتْ مِن قَسْوَرَةٍۭ
74:51 #ከአንበሳ የሸሹ፡፡
ۚ فَمَثَلُهُۥ كَمَثَلِ ٱلْكَلْبِ إِن تَحْمِلْ عَلَيْهِ يَلْهَثْ أَوْ تَتْرُكْهُ يَلْهَث ۚ
7:176 ብጤውም ብታባርረው ምላሱን አውጥቶ የሚያለከልክ እንደ ኾነ #ውሻ ነው፡፡
,
إِنَّ هَٰذَآ أَخِى لَهُۥ تِسْعٌۭ وَتِسْعُونَ نَعْجَةًۭ
38:23 ይህ ወንድሜ ነው፤ ለእርሱ ዘጠና ዘጠኝ ሴቶች #በጎች አሉት፡፡
حَتَّىٰٓ إِذَآ أَتَوْا۟ عَلَىٰ وَادِ ٱلنَّمْلِ
27:18 #በጉንዳንም ሸለቆ በመጡ ጊዜ
وَأَعِدُّوا۟ لَهُم مَّا ٱسْتَطَعْتُم مِّن قُوَّةٍۢ وَمِن رِّبَاطِ ٱلْخَيْلِ
8:60 ለእነሱም ከማንኛውም ኃይልና ከታጀቡ #ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ አዘጋጁላቸው።
ِۦ وَأَخَافُ أَن يَأْكُلَهُ ٱلذِّئْبُ
12:13 #ተኩላ ይበላዋል ብዬ እፈራለሁ» አላቸው፡፡
مَثَلُ ٱلَّذِينَ ٱتَّخَذُوا۟ مِن دُونِ ٱللَّهِ أَوْلِيَآءَ كَمَثَلِ ٱلْعَنكَبُوتِ ٱتَّخَذَتْ بَيْتًۭا ۖ
29:41 የእነዚያ ከአላህ ሌላ ረዳቶችን (ጣዖታትን) የያዙ ሰዎች ምሳሌ ቤትን እንደ ሠራች #ሸረሪት ብጤ ነው፡፡
ِ ۚ قَالَ يَٰوَيْلَتَىٰٓ أَعَجَزْتُ أَنْ أَكُونَ مِثْلَ هَٰذَا ٱلْغُرَابِ
5:31 «ወይ እኔ የወንድሜን ሬሳ እሸሽግ ዘንድ እንደዚህ #ቁራ ብጤ መኾን አቃተኝን» አለ፡፡ ከጸጸተኞችም ኾነ፡፡
كَأَنَّهُمْ حُمُرٌۭ مُّسْتَنفِرَةٌۭ
74:50 እነርሱ ልክ ደንባሪዎች የሜዳ #አህዮች ይመስላሉ፡፡
يَوْمَ يَكُونُ ٱلنَّاسُ كَٱلْفَرَاشِ ٱلْمَبْثُوثِ
101:4 ሰዎች እንደ ተበታተነ #ቢራቢሮ በሚኾኑበት ቀን፤
وَأَرْسَلَ عَلَيْهِمْ طَيْرًا أَبَابِيلَ
105:3በእነርሱም ላይ መንጎች የኾኑን #ዎፎች ላከ፡፡
https://t.me/furqan_school
https://t.me/furqan_school
1.0K viewsFurqan Online Quran, 15:15