2022-10-05 18:30:25
‘የተግባር ሰው ሁን!’
አንድ ወጣት ሸይኹን እንዲህ ሲል ጠየቃቸው :
"#ደጃል ግንባሩ ላይ "كافر" (#ካፊር) የሚል የተፃፈበት ከሆነ አንድም ሰው ይከተለዋል ብዬ አላስብም።" አላቸው ፣
እሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱለት :
" አይ አንተ ልጅ #የሲጋራ ፓኬትምኮ "ሲጋራ ገዳይ ነው" የሚል ፅሁፍ ነበረው ፣ ነገር ግን ብዙ ሰው ያጨሰዋል!!!"
አዎ ፣ ጉዳዩ አንድን ነገር ከመስማትህ ወይም ከማየትህ አይደለም። ይልቁንስ ከሰማኸውና ካየኸው ነገር ፍሬ ነገርን ወደ ሂወትህ ማስገባትህና ተግባር ላይ ማዋልህ እንጅ። ብዙ ጊዜ ዳዕዋ ሰምተን ይሆናል ፣ ብዙ ምክሮችን አዳምጠን ይሆናል ፣ አንዳንድ ምክሮችማ በዙ ጊዜ እስኪደጋገሙብን ድረስ አጣጥመናቸዋል። ግን ከነዚያ ምክሮች ፣ ግሳፄዎች ምን ተጠቀምን? ምን አተርፍን? ራሳችንን እንጠይቅ!!
መስጂድ ሂደህ ካልሰገድክ አዛን መስማትህ ምን ፋይዳ አለው ፣ ህይወትህና ሁለመናህ ካላረከው ቁርኣንን ብዙ ጊዜ ማንበብህ ምን ትርጉም አለው ፣ ካልተመከርክባቸው በተለያየ ጊዜ ሚዲያ ላይ የምታያቸው ምክሮችና ተግሳፆች ምን ትርፍ አላቸው።
አሏህ ሰምተው ፣ አይተው የማይመከሩና የማይተገብሩትን ሲገስፅ እንዲህ ይላል:
لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُونَ
"
ለእነርሱ በርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፡፡ ለእነሱም በሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው፡፡ ለእነሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው፡፡ እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው።"
መስማት ፣ መመልከት ፣ ማንበብ... መዳረሻ መሰላል እንጅ የመጨረሻ ግብ ሊሆኑ አይችሉም ፣ እንግዲያውስ መተግበር እንጅ
علم بلا عمل كالشجر بلا ثمر
እውቀት ያለ ተግባር
ዛፍ ያለ ፍሬ ፣ እንደሚባለው።
ሙሀመድ ጁድ
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
https://t.me/Muhammed_Jud
490 viewsMohammed Jud, 15:30