2022-10-09 17:14:02
‘አራት (4)’
በዱንያም በአኼራም ስኬታማ ሰው መሆን ትፈልጋለህ – እንግዲያውስ አራት (4) ነገሮችን እድሜ ልክህን ፈፅሞ እንዳትተዋቸው
ሹክር : ፈጣሪህን ሁሌ ማመስገን እንዳትተው መጨመርን (በረካን) ትነፈጋለህና
{لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ}
ዚክር : አብዝተህ አሏህን ማስታወስን እንዳትተው የሱን ትውስታ (እሱ አንተን ማስታወሱን) ትከለከላለህና
{فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ}
ዱዐእ : አሏህን መለመንን እንዳትተው ኢስቲጃባን (ተቀባይነትን) ትነፈጋለህና
{ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ}
ኢስቲግ’ፋር : ለወንጀሎችህ ምህረትን መጠየቅ እንዳትተው ነጃ መሆንን (ከእሳት መዳንን) ትነፈጋለህ
{وَمَا كَانَ اللَّهُ مُعَذِّبَهُمْ وَهُمْ يَسْتَغْفِرُونَ}
አጂብ!... ምንኛ ያማሩና የተዋቡ ታላቅ የአሏህ ቃልኪዳኖች ናቸው!! እንጠቀምባቸው አህባቢ!!
አሏህ ሆይ አመስግነውህ ከጨመርክላቸው ፣ አስታውሰውህ ካወሳሀቸው ፣ ለምነውህ ከተሰጠሀቸው እና ምህረትን ጠይቀውህ ወንጀላቸውን ከማርካቸው ባሪያዎችህ አድርገን። አሏህ ሆይ አንተን በማስታወስ ፣ በማመስገንና አምልኮትህን በማሳመር ላይ አግዘን። አሚን
ሙሐመድ ጁድ
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
https://t.me/Muhammed_Jud
683 viewsMohammed Jud, 14:14