Get Mystery Box with random crypto!

‘ ኢስቲግፋር ‘ የሰው ልጅ እና ስህተት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። ለዚ | ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል

‘ ኢስቲግፋር ‘

የሰው ልጅ እና ስህተት የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። ለዚያም ነው በመልእክተኛው ﷺ ንግግር ላይ እንደተጠቀሰው ሁሉም የሰው ዘር ከስህተት የፀዳ ሊሆን ይቅርና አብዝቶም የሚሳሳት ፍጡር ነው። ለዚህ ስህተተኛነቱ ደግሞ ላጲስ (ማጥፊያ) ያስፈልገዋል። #ኢስቲግፋር...
﴿وَبِالأَسْحَارِ هُمْ يَسْتَغْفِرُونَ﴾
"በሌሊቱ መጨረሻዎችም እነርሱ ምሕረትን ይለምናሉ፡፡"
﴿وَمَا كَانَ اللَّهُ مُعَذِّبَهُمْ وَهُمْ يَسْتَغْفِرُونَ﴾
"አላህም እነሱ ምህረትን የሚለምኑ ሲኾኑ የሚቀጣቸው አይደለም፡፡"

እነዚህ አንቀፆችሌሊት ተነስተው ምህረትን ለሚጠይቁ ሁሉ የብስራት ዜናዎች ናቸው። በዚያ ሰዎች ጭልጥ ባለ የእንቅልፍ ሰመመን ውስጥ በሰጠሙበትና በትንሹ ሞት ውስጥ ባሉበት ወቅት ብሎም ከተማው ሰጥ እረጭ በሚልበት በተረጋጋውና ሰኪና በተሞላበት ሌሊት ተነስቶ ኢስቲግፋር ማድረግ ምንኛ መታደል ነው።

ኢብኑል ቀዪም ረሒመሁሏህ ይላሉ : "አራት ነገራቶች ሪዝቅን (ሲሳይን) ያመጣሉ: ቂያመል ለይል (የሌሊት ሶላት) ፣ በሌሊቱ መጨረሻ አካባቢ ኢስቶግፋር ማብዛት ፣ ሶደቃን ለማውጣት መትጋት ፣ ከቀኑ መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ዚክር ማድረግ።"

ታዲያ ይህን በማብዛት አደራህን
"أستغفر الله العظيم الذي لا إله إلا هو الحي القيوم وأتوب إليه".
=
(ሙሀመድ ጁድ ፣ መስከረም 21/2015)
◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
ሌሎች ፅሁፎችና መልእክቶች እንዲደርስዎ የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/Muhammed_Jud